ጀርመን: ወደ ሀገራቸው ለሚመለሱ ህገ ወጥ ስደተኞች የፋይናንስ ድጋፍ ትሰጣለች

የጀርመን መንግስት ወደ ሀገራቸው ለሚመለሱ በህገ ወጥ መንገድ ጀርመን የገቡ ስደተኞች ድጋፍ የሚውል ፋይናንሳዊ ድጋፍ ለመስጠት የምያስችል እንቅስቃሴ አድርጋለች።  “ሀገራችሁ። ተስፋችሁ። አሁኑኑ!” የሚል ፅሑፍ የተፃፈባቸው ከ 2 ሺ 5 መቶ በላይ ቢልቦርዶች 80 በምያክሉ የጀርመን ከተሞች ላይ ተተክለዋል።  

እነዚህ  ወደ ተስፋችሁ የሆነችው ሃገራችሁ ተመለሱ የሚል መልእክት የተፃፈባቸው  ቢልቦርዶች በተለያዩ ቋንቋዎች ማለትም በጀርመነኛ፣ እንግልዝኛ፣ ፋርሲ፣ ፈረንስኛ፣ ዓረብኛ፣ ራሻኛ እና ፓሽቶ ቋንቋዎች የተፃፉ ናቸው። እንዲሁም በቢልቦርዶቹ ላይ የአፍሪካ፣ መካከለኛ ምስራቅ፣ ኤስያ እና ምስራቃዊ  አውሮፓ ሃገራት ባንድራ እንዲታይ ተደርገዋል።  የጀርመን የሀገር ውስጥ ሚኒስትር ድረ ገፅ ያሰፈረው ፅሑፍ “ይህ እንቅስቃሴ በህጋዊ መንገድ ለሚኖሩ ስደተኞች አይመለከትም። ህጋዊ የሆነ የጀርመን ቆይታቸው ጥያቄ ውስጥ አይገባም” ይላል።   ይህ እንቅስቃሴ  በይፋ የተጀመረው መይ 2017 ሲሆን ዋና ዓላማው አድርጎ የተነሳው በህገ ወጥ መንገድ ጀርመን ሃገር ላይ የሚኖሩ ስደተኞች በገዛ ፈቃዳቸው ወደየ ሃገራቸው ይመለሱ ዘንድ ለማበረታታት ነው።  ይህ የመለለስ ኦፕሬሽን ከ 1000 በላይ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ምክር ሰጪ ማእከላት ተደራጅተው ተመላሾቹ  አማራጮችን እንድያገኙ  ሲደረግ  ቆይተዋል።

ይህ የመመለስ እንቅስቃሴ አሳይለም ለሚጠይቁ  ህገ ወጥ ስደተኞች ብቻ የተዘጋጀ ሳይሆን ጠይቀው ጥያቄአቸው በሂደት ላይ ላሉ፣ ተቀባይነት ላላገኙ እንዲሁም መመለስ ለሚፈልጉ ህጋዊ ስደተኞች እና የመብት ጥሰት ላጋጠማቸው ስደተኞችንም ጭምር ነው።    

በፈቃዳቸው ለመመለስ የወሰኑ ስደተኞች እንደ ዜግነታቸው እስከ 1200 ዩሮ እንዲሁም የአሳይለም ሂደታቸው ጨርሰው ግን ደግሞ መመለስ ለወሰኑ ደግሞ እስከ 800 ዩሮ ድጋፍ እየሰተጣቸው ይመለሳሉ ተብለዋል።   እንደየሁኔታው ደግሞ ለአንድ ቤተሰብ እስከ 3000 ዩሮ ለአንድ ሰው ደግሞ እስከ 1000 ዩሮ ድጋፍ እንደሚሰጣቸው ተገልፀዋል።   

በንፅፅር ሲታይ በፕሮግራሙ መሰረት  ከአፍጋኒስታን፣ ኤርትራ፣ ኢትዮጵያ፣ ጋምብያ፣ ጋና፣ ኢራን፣ ኢራቅ፣ ናይጄርያ እና ፓኪስታን የመጡ ስደተኞች ከሌሎች ከ35 በላይ የአውሮፓ፣ አፍሪካ እና ኤስያ ሃገራት የመጡ ስደተኞች የበለጠ  ፋይናንሳዊ ድጋፍ ያገኛሉ።  

TMP – 20/01/2019

ፎቶ ካፕሽን:የጀርመን የሃገር ውስጥ ሚኒስትር ያወጣው ስደተኞች ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ የምያበረታታ ቢልቦርድ   

ፎቶ ክሬዲት: አያ ኢብራሂም/ትዊተር