የጣልያኑ ሳሊቪኒ ስደተኞችን በማስቆም ዙርያ ለመነጋገር ሊብያ ገቡ

የጣልያኑ የሀገር ውስጥ ሚኒስትር ማቲው ሳሊቪኒ ባህርን አቋርጠው አውሮፓ ለሚገቡ ስደተኞችን ለማስቆም የምያስችሉ ማእከላት በሊብያ ለማቋቋም በሚቻልባቸው ዕድሎች ከሊብያ መመሪዎች ባጋር ለመመከር ሊብያ ገብተዋል፡፡

“ሐሙስ፤ ጁን 28 በብራስለስ ከተማ ከሊብያ ባለ ስልጣናት ጋር ባደረግነው ስምምነት መሰረት በደቡባዊ የሊብያ ክፍል ሊብያን ሆነ ለጣልያንን ከስደተኞች ሸክም ለማዳን የምያስችል ስደተኞችን ለመቀበል እና ለመለየት ታስቦ ማእከል እንዲቋቋም ወስነናል፡፡” ብለዋል ሳሊቪኒ በትሪፖሊ የነበራው ቆይታ አስመልክተው ሲናገሩ፡፡

የሊብያው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አህመድ ማቲቅ በበኩላቸው “በሊብያ ድንብር አከባቢዎች ማእከላት የማቋቋም ሀሰብ በከፊል እንቃወመዋለን” ሲሉ ከሳሊቪኒ ጋር በሰጡት የጋራ መግለጫ ተናግረዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ “እንደዛ ማድረግ የሊብያ ህግ አይፈቅድም… ፕሮግራሙም የሊብያ ፕሮግራም መሆን አለበት። የአውሮፓ ሀገራት ተሳትፎም በዚህ ህግ ስር መሆን ይኖርበታል” ሲሉ ገልፀዋል።

ሳሊቪኒ የLibyan coastguard በጎ ተግባር በመልካምነቱ አንስተው ያመሰግኑ ሲሆን ጨምረው እንዳሉት “የመንግስት ስራ ተክተው ለመስራት የሚፈልጉ የበጎ አድራጎት ድርቶች ለመከላከል እና ህገ ወጥ ስደተኞችን ከለላ እንዳያገኙ ለማድረግ በሊብያን ባህር ታላቅ ሚና መጫወት የሚችሉ የሊብያ ባለስልጣናት ናቸው።”

ይህ ጉብኝት በአዲሱ የጣልያን መንግስት ባለስልጣናት እና በፀረ ስደተኞች ሊግ ሲካሄድ የመጀመርያው ሲሆን እንደ የድርጅቱ ሊቀመንበርም ሳሊቪኒ የሀገር ውስጥ ሚኒስትር ከሆኑ በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ የተደረገ ጉብኝት መሆኑን ታውቀዋል።

በዚህ ወር መጀመርያ አከባቢ 630 ስደተኞችን የጫነች ጀልባ በጣልያን ወደቦች ላይ እንዳታርፍ መከልከላቸው ይታወሳል። ጃልባይቱ በማልታ መንግስትም ማረፍያ ተከልክላ የጫነቻቸው ስደተኞች ስፔን እስክትደርስላቸው ድረስ ባህር ላይ መቆየታቸው ይታወሳል።

ጣልያን እና ማልታ ሌላ 234 ስደተኞችን የያዘች ተከታይ ጀልባ ወደቦቻቸው ላይ እንዳታርፍ ማድረጋቸው የሚታወቅ ሆኖ ስደተኞቹ በማልታ ባህር ዳርቻዎች ላይ ሲንገላቱ እንደቆዩ ይታወሳል።

“የአውሮፓ ህብረት የምያደርገው እናያለን። ምክንያቱም አሁንም ስደተኞችን የጫነች ጀልባ ወደብን ፍለጋ በማልታ ባህር ላይ ትኖር ይሆናል። እናም ደግመን የምንነግራችሁ ነገር ቢኖር በጣልያን ወደቦች ላይ የምታርፍ ጀልባ አትኖርም።” ነው ያሉት ሳሊቪኒ።

ሳሊቪኒ በፈረንሳይ እና ስፔን የቀረበላቸው ስደተኞች የአሳይለም ጥያቄአቸው እስኪታይድረስ በዝግ ማቆያ ማእከላት እንዲቆዩ የሚል ጥሪ ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ሳሊቪኒ በትዊተር ገፃቸው “ወደ ጣልያን መግባት? ይህ ለእኛ ለጣልያን እና ለሊብያ ችግር ነው። ምክንያቱም ይህ እንደ ጎርፍ የሚግተለተል የስደት ማዕበል የሚቆምበት ነጥብ የለምና። እናም የእኛ ምክረ ሀሳብ በደቡባዊ የሊብያ ክፍል ማቆያ ማእከላት እንዲገነቡ እና ትሪፖሊም እንደ ጣልያን ከመሆን እንድትድን ማድረግ ነው።”

“በሰው ንግድ ስራ ላይ የተሰማሩ ሰዎች ለማስቆም፣ ሌሎች ወንጀለኞችን ለመቆጣጠር እንዲሁም ሁሉም የሞት መንገዶች በቁጥጥር ስር ለማዋል ስደተኞችን ወደ ባህር አከባቢ ሳይደርሱ ማስቀረት መቻል ያስፈልጋል” ብለዋል ሳሊቪኒ በሌላ መግለጫቸው።

TMP – 02/08/2018

ፎቶ: ለፋር ራይት ፓርቲ እና ለመሪው ማቲው ሳሊቪኒ ድጋፍ የወጣ ሰለማዊ ሰልፍ፤ ሚላን፤ ጣልያን፤ 24 ፌብራሪ 2018