ጣልያን የሉባትን ስደተኞች ወደ ሊብያ እንደምትመልሳቸው አስጠነቀቀች!
ጣልያን ያሉባትን 180 ስደተኞች ሌላ ሌላ የአውሮፓ ሀገራት ካልወሰድዋቸው ወደ ሊብያ ልትመልሳቸው መሆንዋን አስጠነቀቀች።
በአውሮፓ ህር ስር የምትሰራ የጣልያን ሀገር የባህር ጠረፍ ጀልባ የሆነቸው ዲሲቶይ በሜዲትራንያን ባህር ውስጥ ኦገስት 16 ላይ ያዳነቻቸው 117 ስደተኞች ወደ ጣልያን እንዳይገቡ አስጠነቅቃለች።
ጣልያን እነዚህ በሞት ሽረት ውስጥ የነበሩ ስደተኞች በማልታ ባህር ግዛት ውስጥ የተገኙ መሆናቸው እና ማልታ የኔ ሀላፊነት አደለም በማለት ስደተኞቹን መቀበል አልቻለችም በማለት ክስ ታቀርባለች።
የማልታው ጠቅላይ ሚኒስትር የሆኑት ጆሴፍ ሙስካት በበኩላቸው ያቺ ስደተኞች የየዛች መርከብ በማልታ ባህር ስታልፍ ድጋፍ ያስፈልጋት እንደሆነ በማልታ የፀጥታ ሀይሎች ተጠይቃ አልፈልግም ብላ እንዳለፈች ተናግረዋል።
“ስደተኞቹ ድጋፍ እንድያገኙ ተፈልጎ ሲጠየቁ በፍፁም አይሆንም በማለት ወደ መጨረሻ የጉዛአቸው መዳረሻ ማለትም ወደ ጣልያን ቀጥለዋል።” ነው ያሉት።
ሙስካት በመግለጫቸው ለሰብአዊነት ሲባል መርከብዋ እስከመጨረሻ እንደተከታተልዋት ተናግራዋል።
የማልታ የሀገር ውስጥ ጉዳዮች ሚኒስትር ሚኪኤል ፋሩጋ በቲዊተር ገፃቸው እንደፃፉት ከሆነ የጣልያኑ መርከብ ሆን ብሎ ነው ከማልታ የባህር ላይ ግዛት ስደተኞቹን የመለሳቸው። ወደ ጣልያን የባህር ግዛት እንዳይገቡ አስበው ከአርሲሲ (Rescue Coordination Centre) ሳይነገጋገሩ ነው የመለስዋቸው።” ብለዋል ሚኒስትሩ።
“አንድ መርከብ ወይም ጀልባ በነፃነት በሚቀዝፍበት ጊዜ እጅ ማስገባት የማዳን ስራ መስራት ተብሎ መወሰድ የለበትም።” ብለዋል ፋሩጋ።
ፋሩጋ በፅሁፋቸው “በአሁን ሰዐት መርከቧ ላምፕዱሳ በተባለው የጣልያን ጠረፍ አከባቢ ትገኛለች።” ጨምረውም “ብቸኛው መፍትሄ” ስደተኞቹ በላምፑድሳ ወደብ ላይ ወይም ደግሞ ሌላ የጣልያን ወደብ ላይ እንድያርፉ ማድረግ መሆኑን ተናግረዋል።
“አሁንም ጣልያን ጉዳዩ ህይወት ከማዳን አንፃር የምታየው ከሆነ ስደተኞቹ ላምፑድሳ ላይ ማረፍ አለባቸው” ብለዋል ሚኒስትር ፋሩጋ።
ይሄንን የማልታ ድምፅ ተከትለው መግለጫ የሰጡት የጣልያን የትራንስፖርት ሚኒስትሩ ዳኒሎ ቶኒነሊ የሀገራቸው የሰብአዊነት ስራ አማኳሽተዋል። አክለውም ማልታ ቅጣት ሊጣልባት ይገባል ብለዋል።
ታንዮኒ በቲዊተር ገፃቸው “የመርከብዋ ተግባር የምያሳየው ጣልያን ህይወት ለማዳን ስትሯሯጥ የሚገፉዋትን መከላከል ነው።” ብለዋል።
“የማልታ ተግባር ይቅርታ የማስፈልገው እና ቅጣት ሊጣልበት የሚገባ ነው።” ብለዋል በፅሑፋቸው።
ቶኒነሊ በፅሑፋቸው “የአውሮፓ ህብረት ወደቦች መክፈት ረገድ አንድ እርምጃ ወደፊት መሄድ የምያስችል ስራ መስራት ይጠበቅበታል። አለበለዝያ ግን እዛው ውስጥ መቆየት የምያስችል ምክንያት አይኖርም።” ብለዋል። .
ይህ ሁነት ካጋጠመ ሶስት ቀን በኋላ የጣልያኑ የሀገር ውስጥ ሚኒስትር ማቲው ሳሊቪኒ ለአውሮፓውያን ሀገራት ማስጠንቀቅያ አስተላልፈዋል። .
“የአውሮፓ ሀገራት ወይ ጣልያንን በሚታይ መልኩ ማገዝ አለባቸው። ይህ ድጋፍ አሁን ፖርት ላይ ካሉት 180 ስደተኞችን መጀመር አለበት። አለበለዝያ ግን ጣልያን የደላሎች ቢዝነስ በዘላቂነት መስበር የሚያስችል መፍትሄ ያለችውን ከማድረግ አትቆጠብም።” በማለት ማስፈራርያ አዘል መልእክት አስተላልፈዋል።
TMP – 06/09/2018
ፎቶ: ፋቶ ኳቲዲኖ፤ ጣልያናዊ ፓትሮል ሽፕ
ፅሑፉን ያካፍሉ