ሩዋንዳ በሊብያ የታገቱ በመቶዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች አስተናግዳለሁ አለች

ወደ አውሮጳ ለመሻገር አስበው ሊብያ ከደረሱ በኋላ እዛው የታገቱና ማጎርያ ካምፖች ውስጥ የተጨናነቁ አፍሪካውያን ስደተኞች አሉ። እነዚህ ስደተኞች ላይ በሰዎች ከሚደርስባቸው የሰብአዊ መብት ገፈፋና ግፍ ባሻገር፤ ከምዕራባውያን አገራት በሚደርሰው የአየር ጥቃትም ሰለባዎች ናቸው። ከዚህ በመነሳት የስደተኞችን ህይወት ለመታደግ፤ ሩዋንዳ በመቶዎች የሚቆጠሩ ወገኖች በአገርዋ ማስተናገድ እንደምትፈልግ ገልፃለች። ሰብአዊ ቀውሱን ለመታደግ ከአፍሪካ ህብረትና ከአውሮጳ ህብረት በትብብር እሰራለሁ ያለችው ሩዋንዳ በመጀመርያ ዙር 500 ስደተኞችን ለመቀበል ተዘጋጅቻለሁ ብላለች።

በሊብያ የአየር ጥቃቱ እየበረታ ከመጣ በኋላ እዛ ቡታጅራ ማጎርያ ካምፕ የታጨቁቱን ስደተኞች የማዛወር ተነሳሽነት በርትቶ የቀጠለ ሲሆን፤ ሩዋንዳ የደረሰችበት በጎ ውሳኔም የዚህ ተነሳሽነት አካል ነው። ይሁን እንጂ ስደተኞችን የማዛወር ሁኔታው እስከአሁን ድረስ የቀን ሰሌዳ አልተያዘለትም። የሩዋንዳ የመንግስት ሚኒስተርና የምስራቅ አፍሪካ ማሕበረሰብ አምባሳደር አሊቨር ንዱሁንጊሪህ በጣምራ እንደገለፁት፤ ስደተኞች ከሊብያ ማጎርያ ካምፕ ማዛወር ተግባራዊ የሚወሰንበት ግዜ ላይ እየተወያዩ ነው።

አሊቨር እንደገለፁት “ 500 ስደተኞችን በፍጥነት ከሊብያ ወደ ሩዋንዳ ለማጓጓዝ  ከአውሮጳ፣ ከሊብያና ከሩዋንዳ መንግስታት በጣምራ እየተወያዩና እቅድ እያዘጋጀን ነውብለዋል።እስከሚጓጓዙ ድረስ በሊብያ ያሉበት ተጨባጭ ሁኔታ የሚታዘብ አንድ ቡዱንም እንልካለንብለዋል።

2017 ... ኤን ኤን ( CNN ) በሊብያ ትሪፖሊ ላይ ስደተኞች ለባርነት እየተሸጡ የሚያሳይ ፊልም ከለቀቀ በኋላ ሩዋንዳ 30000 ወገኖች ለመቀበል ቃል እንደገባች ይታወቃል።

የሩዋንዳው ፕረዚዳንት ፖል ካጋሚ በወቅቱበሊብያ ያየነው ሰብአዊ ሁኔታ አስደንጋጭ ነው። አእምሮን ይረብሻል። እኛ እዛ ከሰውነት ውጭ ሆነው ታግተው ለሚገኙ አፍሪካውያን ወንድሞቻችን ጥላ ከለላ ለመሆንና ለመተባበር እግጁ ነን። ወደ ሩዋንዳ ለመግባት ፍቃደኛ ለሆኑት ወንድሞቻችን ለመቀበል ዝግጁ ነንብለው ነበር።

ይሁንና ከሩዋንዳ ይልቅ ለስደተኞች ቅርብና ለግዚውም ቢሆን ጥላ ከለላ ሊሆን የቻለው ወደ ኒጀር ስደተኞች ለዛወሩ ችሏል። ኒጀር እስካሁን ድረስ በአስከፊ ሁኔታ ላይ የነበሩ 2900 ስደተኞች ከሊብያ ወደ አገርዋ አጓጉዛለች።

የስደተኞች ጫና የበዛባቸው የአውሮጳ አገራት፤ በሊብያ የሚገኙ ስደተኞች ወደ አገራቸውም ሆነ ወደ ሌላ የአፍሪካ አገራት እንዴት ማጓጓዝ እንደሚቻል እየዘየዱ ይገኛሉ።

የአውሮጳ ህብረትም ለዚያ ለአውሮጳ  አገራት ተነሳሽነት እንደሚደግፍና ከሊብያ ስደተኞችን የማጓጓዝ እንቅስቃሴ እንደሚያግዝ አረጋግጠዋል።

TMP – 29/08/2019

ፎቶ ክረዲት፤  euractiv.com

በአንድ የሊብያ ማጎርያ ካምፕ ውስጥ