ከ500 በላይ የሚሆኑ ስደተኞች ባህር ውስጥ ከመርከብ እንዳይወርዱ ታግተዋል

በሜዲትራንያን ባህር መስመር ወደ አውሮፓ በሁለት የነብስ አድን ጀልባዎች ሲጓዙ የነበሩት ከ500 በላይ ስድተኞች ወደ አውሮፓ የመግብያ ፍቃድ የሚሰጣቸው አካል ባለመግኘቱ በባህር ላይ ታግተው ቀመዋል። የጣልያንና ማልታ መንግስታት ባህር ላይ በጀልባ ውስጥ እየተንሳፈፉ በቆሙት ስድተኞች ወደ ባህር ዳርቻ ተጠግተው እንዳይራገፉ አስፈላጊው ትብብር እንዲያገኙ ፍቃደኛ አይደሉም።

በስፓንሽና ፈረንሳይ የእርዳታ ድርጅት አመካኝነት የሚረዱት እነዚያ ሁለት ጀልባ ሙሉ ስደተኞች ባህር ላይ ከቆሙ( ከታገቱ) ሶስተኛ ሳምንታቸው አስቆጥረዋል።

እ.ኤ.አ ባለፈው ነሃሰ 13 የጣልያን የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስተር ማትዮ ሳልቫኒ ፤ ሁለት የነብስ አድን ጀልባዎች ወደ ወደባቸው እንዲገቡ አንፈቅድም ብለዋል። ማትዮ ሳልቫኒ  በፌስ ቡክ ገፃቸው “ እኔ በሚኒስተር መስርያ ቤቱ ውስጥ፤ እነዚህ በሁለት ግብረ ሰናይ(ስፔይንና ፈረንሳይ) ጀልባዎች የመጡት 500 ስደተኞች ወደ አገራችን ከመግባት እየተከላከልኩ ነው “ ብለዋል። ሚኒስትሩ እንደዛ ይበሉ እንጂ ጣልያን ከዛ በሃላ ትንሽ ልቧ በማራራት 27 ለአቅመ አዳም ያልደረሱና የሚታደጋቸው ላጡ ስደተኞች  ለምፓዳ በተባለ የወደብ ከተማ እንዲያርፉ ከ16 ቀናት ክልከላና ድርድር በሃላ በነሃሰ 17 ፈቅዳለች።

ቪኪንግ የተባለችና በሜዲትራንያን የምትንቀሳቀስው ሁለተኛዋ ነብስ አድን ጀልባ: በፈረንሳይ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ማለትም ድንበር የለሽ ሃኪሞች፣ ስኦኤስ የምትመራ ሲሆን፤ ከሰባት ወራት ስራ ማቆም በሃላ ስራ መጀመርዋ ይታወቃል። ይህች ጀልባ በአሁኑ ሰዓት በነሃሴ 9 ከባህር ላይ ያዳነቻቸውን 356 ስድተኞች እንደጫነች እዛው ሜዲትራንያን ባህር ውስጥ ቆማ ትገኛለች።

የነብስ አድን ግብረ ሃይሉ ጀልባ ውስጥ ያሉ ስደተኞች ወደ አደገኛው ቀጠና ሊብያ እንዲመለሱ አይፈልግም። የስደተኞቹ ሰብአዊ ሁኔታ ወደ ከፋ ደረጃ እየወረደ በመሆኑም የአውሮፓ አገሮች ችግሩ ሳይባባስ እንዲወስድዋቸው እያግባባ ይገኛል።

ባለፈው እሁድ የስፔይን መንግስት ባህር ውስጥ የቀሩት ስድተኞች ወደ አገሩ እንዲገቡ  ቢፈቅድም ፤ ስደተኞቹ ባሉበት አደገኛ ሁኔታ ተመልሰው ወደ ስፔይን ያለው ረጂም ጉዞ በህይወት ሊደርሱ እንደሚችሉ አረጋግጠዋል። የስፔይን መንግስት በጀልባዎቹ  ያለው ሁኔታ ሲገልፁ “ አደገኛ ሰብአዊ ቀውስ “ ብሎታል።

የተባበሩት መንግስታትም በዚህ ጉዳይ ላይ የገባው ሃሳብ ከመግለፅ አልተቆጠበም። የአለም ስድተኞች ኮምሽን ቃል አቀባይ ቻርሊ ያዚለይ ለአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ እንደገለፁት “ በባህር ውስጥ እንዲቆሙ የተገደዱት ስድተኞች በሚቀጥለው ሳምንት በሚነሳው ሃይለኛ ማእበል ወደ ከፋ ሰብአዊ ቀውስ ሳይገቡ በእስቸኳይ ወደብ ላይ መራገፍ  እንዲፈቀድላቸው አሳስበዋል። ቃል አቀባዩ “ ይህ ጉዳይ በጦርነት እና ሰብአዊ መብት ጥሰት እግር ምክንያት ከአገራቸው ለሚሸሹ ሰዎች ምን ያህል አይናችንን እንደጨፈንን የሚያሳይ ኢ ሰብአዊነት ነው” ብሎታል።

በነብስ አድን ጀልባዎቹ ባህር ላይ ያሉ ሰዎች አብዛኛዎቹ ከሱማልያ ፣ኢትዮፕያና ኤርትራ የመጡ ናቸውም ብለዋል።”  እነዚህ ሰዎች በአገሮቻቸው ላይ በጣም አደገኛ ነገር ባይገጥማቸው እንደዚህ በመርከብና ባህር ላይ ህይወታቸውን ለመገበር ተስፋ ባልቆረጡ”  ሲሉ ቃል አቀባዩ ስድተኞችን ገልፀዋቸዋል።

ይህ ወደ ወደብ አትራገፍም የሚል ክልከላ በአውሮፓ መንግስታት የቅኝ ክንፍ ፅንፈኞች በኩል የሚቀነቀን አቋም ነው። የጣልያንና የማልታ መንግስታት በሜዲትራንያን የሚደረግ የስደተኛ ከፍተኛ ማእበል ላይ ብዙም አይጨነቁም ሲሉ የተቀሩት  የአውሮፓ አገራትን ይወቅሳሉ። ሁለቱም አገራት በዚህ በኩል የሚደረግ ህገ ወጥ የስደተኛ ማእበል እንዲቆም በቀጣይነት ይሟገታሉ(ይሰራሉ።

ጣልያን ለህገ ወጥ መንገድ በሜዲትራንያን መስመር ለሚደረጉ ማናቸውም ስደተኞች ወደብዋን ከዘጋች ቆይታለች። በዚህ መስመር የነብስ አድን ጀልባዎች ዝውውር እንዲቆምም ህግ ያፀደቀች ሲሆን፤ በዚህ አይነት እንቅስቃሴዎች ለሚሰመሩ ጀልባዎች ደግሞ በባህር ግዛትዋ ከተገኘ 1 ሚልዮን የአመሪካ ዶላር ቅጣት ጥላለች።

TMP – 22/08/2019

ፎቶ፤– በቄሳር አበተ / ANSA

በሜዲትራንያን ባህር ከታገቱት ጀልባዎች አንዱ