ዴንማርክ ስደተኞችን በተላላፊ በሽታ የተለከፉት እንስሳት ይሚመረመሩባት ወደ ነበረችው ደሴት ልታጓጓዝ ነው

ከዴንማርክ ራቅ ብላ የምትገኝ ትንሿ ሊንድሆልም የተባለች ደሴት የእንስሳት የህክምና ምርመራ ተደርጎ ተላላፊ በሽታ ስለተገኘባት የማይፈልጉትን ስደተኞች ማቆያ እንምትሆን ታውቋል።

የቀኝ አክራሪ የዳኒሽ ህዝቦች የፓርቲ (ዲፒፒ) የማእከላዊው የዴንማርክ መንግስት ታህሳስ 07/2018 / .. ስደተኞችን ለማቆም እንደሚፈልግና በመቶዎች የሚቆጠሩ ጥገኝነት የጠየቁና ጥያቄያአቸው ውድቅ የሆነባቸው እዛው ደሴት ውስጥ እንደሚያሰፍሯቸው አስታውቋል።

በደሴቲቱ 17 ካሬ ሜትር የሚገኙ መገልገያዎች ህንፃዎች ቤተሙከራዎች ሰፈሮችና የሞቱት እንስሳት ማቆያዎች ሲሆን 2021 / .. እነዚህ የአገልግሎት ስፍራዎች ለስደተኞች የሚሆኑ መኖሪያዎች እንደሚተኩ እቅድ ማውጣቱ  ታውቋል።

እቅዱ የደሴቲቱ ነዋሪዎች በቀን 1.20 የአሜሪካ ዶላር እንደሚሰጣቸውና ይህንንም ገንዘብ ከባለስለጣናት ጋር ካልተባበሩ ሊቀር እንደሚችል ገልፀዋል።

ደሴቷ ለስደተኞች ማቆያ ባትሆንም የዲፒፒ የሰደተኞች ጉዳይ ቃል አቀባይ የሆኑት ማርቲን ሄንሪክሰን ለሲ.ኤን.ኤን እንደገለፁት ስደተኞቹ የተቻለዉን ያህል እዛው እንደዲቆዩና ረዘም ላሉት ጊዜያት የምናቆያቸው ከሆነም እንደዛ እናደርጋለን ብለዋል።

ስደተኞችን በደሴቲቱ ለማቆየት መንግስት ስደተኞቹ በየቀኑ በግዴታ እየመጡ እንዲመዘገቡና እነሱን የሚጓጉዙ ጀልባዎችም እንደተዘጋጁ ገልፀው የጀልባዎቹ የመጓጓዣ ክፍያም በጣም ውድና አልፎ አልፎ እንደሚደረግ ተናግረዋል። ቃል አቀባዩ ምናልባት የማያስፈልግ እንቅስቃሴ (ረብሻ) ካጋጠመ ፖሊሶች እስር ቤቶችና የጥበቃ ስደተኞችም እንደሚመደቡ ጨምረው ገልፀዋል።

ይህንን እቅድ የተዘጋጀው ዴንማርክ ለስደተኞች የማትመች መዳረሻ ሃገር ለማድረግ መሆኑ የዴንማርክ የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች ሃላፊ ኢንገር ስቶችበርግ በማህበራዊ ድህረ ገፃቸው በመፃፍ የተወሰኑ ሰዎች አይፈልጉም እንደማይፈልጉም ማወቅ አለባቸው ብለዋል።

ሄንሪክስን ይህንን አስመልክተው ሲገልፁ የኛ ተስፋ ከዴንማርክ ውጭ ያሉትን ሰዎች እንዲረዱት የምንፈልገው ቢኖር ዴንማርክ ለስደተኞች ተመራጭ ሃገር አለመሆንዋና ለጥገኝነት (ተገን) ጠያቂዎች በተለይም ጉዳት የሚያደርሱና ወንጀል የሚፈፅሙ ከሆነ ብለዋል።

አዲሱ እቅድ በዓለም አቀፍ ደረጃ ታቀውሞ ቢገጥመውም ገና በሃገሪቱ ፓርላማ መፅደቅ ይኖርበታል። የዳኒሽ የሰብአዊ መብት ኢንስቲትዩት ምክትል ዳይሬክተር ሉዊስሆልክ የመብት ጥሰት እንዳያጋጥም ድርጅታቸው ሁኔታውን በቅርበት እንደሚከታተል ገልፀዋል።

የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ኤጀንሲ ሃላፊ ሚሸል ባችሌት በጀኔቫ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ በእቅዱ ላይ ከፍተኛ ሰጋት እንዳለባቸው ገልፀዋል። እንዚህ ዓይነት ፖሊሲ ውጤቱ አይተነዋል፡፡ ይህንን ፖሊሲ መድገም የለብንም ሲሉም አስረድተዋል። ምክንያታቸውም ነፃነታቸውን ማሳጣት ማግለልና መጠየፍ ተጋላጭነታቸውን ያባብሰዋል ሲሉ ገልፀዋል።

ዴንማርክ በቅርቡ በስደተኞች ላይ ከረር ያለ አቋም (ፖሊሲ) ማውጣትዋ ይታወቃል። ለምሳሌ 2016 / የወርቅ ህግ የተባለ ፖሊሲ ማንኛውም በዴንማርክ ጥገኝነት ለመጠየቅ ካለው ሃብት ቀንሶ በገንዘብ ወይም በንብረት መልክ ለመንግስት ገቢ እንዲያደርግ የሚያስገድድ ህግ አውጥታለች።

TMP – 21/12/2018

ፎቶ፦ ስቲጅ ኣሌናስ/ ሻተርስቶክ። ሁለት የፖሊስ አባላት የስደተኞችን ወረቀቶች ሲመለከቱ ኮፐን ሃገን ዴንማርክ ሚያዝያ 2017 /

ስለ ስደት ማወቅ የምትፈልጉት ማነኛውም አይነት ጥያቄ በኢመይል አድራሻችን ልታገኙን ትችላላችሁ።

ጥያቄዎቻችሁ በኢመይል አድራሻችን ላኩልን። ባልደረቦቻችን በፍጥነት ይመልሱላቹኋል። ሁሉም የኢመይል መልእክት
ሚስጥራዊነቱ የተጠበቀ ነው።

ዓለም እየተጓዘ ነው

ዓለማችን በጉዞ ላይ ነው ያለችው። በሚልዮን የሚቆጠሩ ሕዝብ የ21ኛው ክፍለ ዘመን የስደት መከራ እየደረሰባቸው ይገኛል።

የስደት መረጃ፣ ከምንጩ፡ ከመዳረሻና መሸጋገሪያ መንግስታት እስከ ሕገ ወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች፣ መገናኛ ብዙሀን፣ ምሁራን እና የስደተኞች የመረጃ ሰንሰለት በተለያዩ ለስደተኞች የማያግዙ ዓላማዋች የተሞላ ነዉ።

ተጨማሪ ያንብቡ