ሊብያ: በጦር አውድማ ውስጥ በመሆንዋ ምክንያት ስደተኞች እየተጎዱ ነው

የካሊፋ ሃፍታር ወተሃደሮች  ከትሪፖሊ ወደ ደቡብ 25 ኪሜ ርቀት  የሚገኘውን ቃሳር ቢን ጋህሺር የተባለውን የስደተኞች ማቆያ ማእከል በቁጥጥር ስር አውለዋል። ይህ የሆነውአፕሪል 23 ቀን 2019 ነው። ወተሃደሮቹ እስረኞቹ ላይ ከፍተኛ  ጉዳት ማድረሳቸውን የተነገረ ሲሆን ቢያንስ 10 ስደተኞች ላይ የአካል ጉዳት ደርሰዋል፤ አልጀዚራ እንደዘገበው።

ሌሎች ዘገባዎች እንደለፁት ደግሞ ጉዳት የደረሰባቸው የስደተኞች ቁጥር ከዚህ በላይ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል። ሙስቶፋ ኢልመሲ የተባለውን የሊብያ መንግስት ወተሃደራዊ ኦፕሬሽን ቃል አቀባይ እንዳለው የሃፍታር ወተሃደሮች ስድስት ስደተኞች መግደላቸው እና 11 ስደተኞችን የአካል ጉዳት እንዳደረሱባቸው ገልፀዋል።

እንደ የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኤጀንሲ፤ ዩኤንኤችሲአር ገለፃ ከሆነ በማእከሉ ወደ 728 የሚጠጉ   ስደተኞች የነበሩ ሲሆን ከእነዚህ ስደተኞች 100 በላይ የሚሆኑት ሴቶች እንዲሁም 50 በላይ ልጆች መሆናቸው ተነግረዋል።

በአሁኑ ሰዓት ማእከሉ እያወደሙት ነው…. በቀጥታ እየመቱን ይገኛሉ።ብለዋል አንድ ኤርትራዊ ስደተኛ ከአልጀዚራ ጋር በነበረው ቆይታ።ሜዲካል ድጋፍም ያስፈልገናል። ክፉኛ የተጎዱ ሰዎ አብረውን አሉ።ሲልም አክለዋል።

አለም አቀፉ የስደተኞች ተቋም፤ አይኦኤም ስደተኞቹ ከማእከሉ ለማስወጣት ላይ ታች ሲል የነበረ ቢሆንም እንደ የተባበሩት መንግስታት ዘገባ ግና 3,600 በላይ ስደተኞች አሁንም በጦር አውድማው ውስጥ አሉ።

የተባበሩት መንግስታት ባወጣው መግለጫበስደተኛ ማቆያ ማእከላቱ ያለ ሁኔታ በጣም አስፈሪ ነው። ዘበኞች ጥለዋቸው እየሄዱ ነው። ስደተኞች በተዘጉ ማእከላት ውስጥ ናቸው ያሉት።ብለዋል።

አቡ ሰሊም በተባለ የስደተኞች ማቆያ ማእከል እየኖረ ያለ አንድ ኤርትራዊ ስደተኛወዴት መሄድ እንዳለብን አናቅም። ያለ ጥበቃ ነው ያለነው ማለት ይቻላል። ሁለት ብቻ ናቸው ያሉ፤ እነሱም ይሄዳሉ። ጦርነቱ ወደ እኛ እየተቃረበ ነው እየመጣ ያለው።ብለዋል።

የተባበሩት መንግስታት እንደገለፀው ከሆነ ከአፕሪል 5 ቀን ጀምሮ እስካሁን ቢያንስ 264 ሰዎች የተገደሉ ሲሆን 1,266 ሰዎች በላይ ደግሞ ቆስለዋል። በጦርነቱ ምክንያት 32,000 በላይ ንፁሃን ዜጎች ተፈናቅለዋል ነው የተባለው።

የአለም አቀፉ የስደተኞች ተቋም የሊብያ ሚሽን ሀላፊ ኦቶማን በልበሲ እንደገለፀው በአደጋው አጣዳፊነት በጣም ተጨንቀዋል። በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በየቀኑ ከአደጋው ለማምጥ ይጓዛሉ። 3,000 በላይ ስደተኞችም በከፍተኛ ስጋት ውስጥ ወድቀዋል። በመሆኑም በትሪፖሊ ውስጥ እየተፈጠረ ያለ አደጋ አፋጣኝ ድጋፍ ይፈልጋል።ሲል ሲል ገልፀዋል

TMP – 03/05/2019

Photo credit: ስርድያን ራንዶጆልቪክ/ሻተርስቶክ