ቢያንስ ስምንት አፍሪካውያን ስደተኞች በየመን ምድር መሞታቸው ተሰማ

ቢያንስ ስምንት አፍሪካውያን ስደተኞች በጦርነት ውስጥ ባለችው የመን በግዝያዊ ካምፕ ውስጥ መሞታቸውን የአለም አቀፉ የስደተኞች ኤጀንኢ (አይኦኤም) ገለፀ።

ስምንቱ ስደተኞች የሞቱት በካምፑ ውስጥ በተከሰተው የውሃ ብክለት ምክንያት በተፈጠረው የዲሃርያ በሽታ መሆኑ ከካህልዶን ሆስፒታል የተገኘ መረጃ ያመላክታል። ይህ የሆነው መይ 1 ቀን 2019 ነው። አብዛኛዎቹ ኢትዮጵያውያን መሆናቸውንም ተነግረዋል።

በሺዎች ከሚቆጠሩ የመንን አቋርጠው ከሚሄዱት ስደተኞች ከፊሎቹ በሆኑት በእነዚህ ስደተኞች ያጋጠመ አደጋ ልቤን ክፉኛ ሰብሮታል። ይሄንን ስደተኞችን የማጎር አካሄድ ስህተት መሆኑ ለሀገሪቱ ባለስልጠናት ተናግረናል። ህገ ወጥ ስደተኞችን ሰብአዊ በሆነ መልኩ መያዝ እንዳለባቸው በተለያየ መንገድ ገልፀናል።ብለዋል በአለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት የኦፕሬሽን እና ኢመርጀንሲ ዳይሬክቴር የሆኑት ሞሃመድ አብዲኬር።

ከአፍሪካ ቀንድ የሚነሱ እና በጅቡቲ እና የመን አድርገው ወደ ገልፍ ሀገራት ለመድረስ በየመን እየተካሄደ ያለው አራት አመት ሙሉ የቀጠለ ጦርነት ሳይበግራቸው የሚጓዙ ስደተኞች አሁንም አሉ።

  እንደ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ገለፃ ከሆነ ወደ 150,000 የሚጠጉ ስደተኞች 2018 ብቻ የየመን ምድር ረግጠዋል። በከፍተኛ ውጥረት ያሉ የየመን ባለስልጣናት ይሄንን የስደተኞች ጉዞ ለማገት ብዙ መንገዶች እየተከተሉ ሲሆን በሀገሪቱ   የታገቱት ስደተኞች በአስር ሺዎች ይቆጣረሉ። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እንደሚገልፀው በጃንዋሪ ወር ወደ   3,000 የሚጠጉ ስደተኞች ወደ አዲስ አበባ ለመመለስ ተንቀሳቅሰዋል። አሁንም እየተመለሱ ያሉ ስደተኞች አሉ።

አንዳንድ በየመን ታግተው ያሉት ስደተኞች ባለስልጣናቱ ለመኖር አስቸጋሪ በሆነ ቦታ ላይ ናቸው እንዲታሰሩ አድርገዋቸው ያሉት። እነዚህ አሁን የሞቱት ስምንት ስደተኞች ከመሞታቸው በፊት ከሌሎች 1400 ስድተኞች ጋር ላህጅ በተባለው የሰራዊት ካምፕ ውስጥ ቆይተው ነበር። ካምፑ የሚገኘው በደቡባዊ ምዕራብ የየመን ክፍል ውስጥ ነው። ባለስልጣናቱ እንደሚሉት ባደረጉት ምርመራ ቢያንስ 200 ኤደብልዩዲ ኬዞች ማግኘት ችለዋል። 

በአጠቃላይ ሲታይ አይኦኤም እንደሚገልፀው ከሆነ 5,000 በላይ የአፍሪካ ቀንድ ስደተኞች በየመን በሚገኙት ኤደን፣ ላሃጅ እና አብያን የተባሉት ክልሎች በሚገኙት ሁለት ስታድየሞች እና የሚሊተሪ ካምፖች ታጉረው ይገኛሉ።  

አይኦኤም ባወጣው መግለጫ እንደገለፀውወይ ክፍት የሆኑት እና ለስደተኞች ማቆያ የሚሆኑት ስታድዮም መሰራት ነበረባቸው። አለበለዝያ ግን ለሳኒቴሽን ችግሮች እና ተላላፊ በሽታዎች በምያጋልጣቸው ቦታ መቀመጥ አልነበረባቸውም።ብለዋል። 

TMP – 08/05/2019

Photo credit: አናሳልሃጂ / ሻተርስቶክ

Photo caption: የየመን የጦርነት ቀጠና