ኢትዮጵያዊው ከስደት ተመላሽ ስለ ሕገወጥ አደገኝነት መግለጫ ሰጠ

በቅርቡ ብሩክ የተባለው ከስደት ተመላሽ ኢትዮጵያዊ ስለ ህገወጥ ስደት አደገኝነት ታሪኩን/በሱ የደረሰውን ሁኔታ በመንገር ሌሎች እንዲያውቁት አድርጓል።

ብሩክ በአለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት (IOM) እና የኬንያ የግል ዩኒቨርስቲ በጋራ በመሆን ባዘጋጁት ሶስተኛው የስደት ምክክር/ውይይት ከልኡካኑ ጋር ባደረገው ንግግር ደቡባዊ  መንገድ ተብሎ በሚጠራው ማለትም  ስደተኞች ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመድረስ /ለመሄድ የሚጠቀሙበት ቦታ ሲሆን በህገወጥ መንገድ ለመሰደድ በሚያደርገው ሙከራና የሚደርሱትን/የሚያጋጥሙትን አደጋዎች መግለጫ ሰጥቷል።

ብሩክ በደቡብ አፍሪካ አዲስ ህይወት ለመጀመር ተስፋ በማድረግ እንዴት ከኢትዮጵያ እንደወጣና ሆኖም ግን በዛምቢያ ተይዞ ለስድስት ዓመታት እስር ቤት መታሰሩን ይገልፃል።

ብሩክ ሶስተኛ ክፍል ያጠናቀቀ ሲሆን ወላጆቹ በህገወጥ መንገድ ወደ ደቡብ አፍሪካ እንዲሄድ ለማድረግ 3000 (ሶስት ) የሚሆን የአሜሪካን ዶላር ከዘመዶቻቸው ተበድረዋል። ብሩክ በህገወጥ የሰው ልጆች አዘዋዋሪዎች ወደ ደቡብ አፍሪካ የሚደረገው ጉዞ አስተማማኝና ህጋዊ ነው በማለት ሀሰተኛ መረጃ በመስጠት እንዳታለሉት ይናገራል።

ቪዛ እንደሚሰጠኝና ወደ ደቡብ አፍሪካ እንደሚወስደኝ ነግሮኛል በማለት ስለ ህገወጥ የሰውልጅ  አዘዋዋሪዎች ሁኔታ ብሩክ ተናግሯል።

ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመድረስ ባደረገው ሙከራ መጀመሪያ ወደ ኬንያ ከዚያም በታንዛንያና  ዛምቢያ በኩል ጉዞ አድርጓል ጉዞውም በጣም ከባድና  አብዛኛውን ጊዜ የሚደረገው በለሊት ሆኖ ጥቂት ምግብና ውሃ በማግኘት በእግር ወይም ድህንነቱ ባልተጠበቁና በታጨቁ የጭነት መኪኖች ነው በማለት ብሩክ ተናግሯል።

ብሩክ ከሌሎች ኢትዮጵያውያንና ኤስያውያን በመሆን በታንዛንያ በኩል ወደ ዛምቢያ ገብተው ከታሰሩት ሰዎች አንዱ ነው። የዛምቢያ ፍርድ ቤት 15 ዓመታት እስር የፈረደበት ሲሆን ለአለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት (IOM) ምስጋና ይግባውና 6 ዓመታት እስር በኋላ ተፈትቶ/ተለቆ ወደ አገሩ ተመልሷል። አለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት በችግር ላይ ያሉትና ታስረው የሚገኙትን ስደተኞች ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ በደቡባዊ መንገድ ከሚገኙ ከዋናዎቹ የመሻጋገርያ አገሮች መንግስታት ጋር በመሆን በጋራ እየሰራ ነው።

አብዛኛዎቹ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን በህገወጥ መንገድ ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመሄድ ለሕጋዊ ቪዛ በኬንያ ታንዛንያ ማላዊ ዛምቢያና ዚምባብዌ በኩል ይጓዛሉ። በዚህም  ምክንያት አበዛኛውን ጊዜ በነዚህ አገሮች እስር ቤት ይገባሉ።

ኢትዮጵያ ኬንያና ታንዛንያ በደቡባዊ መንገድ ሕገወጥ ስደተኞች ከአፍሪካ ቀንድ በመነሳት ወደ ደቡብ የሚያደርጉትን ጉዞ ለመቀነስ በአለም አቀፍ የሰደተኞች ድርጅት (IOM) በሚደረግላቸው እገዛ በጋራ በመሆን እየሰሩ ናቸው። ስምምነቶቹ ስደተኞችን ከማሰር ይልቅ ሌላ አማራጭ እንዲያገኙ ማድረግ ደህንነቱ ያልተጠበቁ ስደትን መግታትና ስደተኞችን በመመለስና ከህብረተሰቡ ጋር በመቀላቀል  ላይ ያሉትን ምርጥ ተሞክሮዎችን  በመለዋወጥ ላይ ያተከሩ ናቸው።

ብሩክ ወደ አገሩ ከገባ በኋላ ወላጆቹ ሞተው ወንደሞቹና እህቶቹ የነበረውን ንብረት ሸጠውና ተከፋፍለው  ስለቆዩት በችግር ላይ ወድቋል።

ሆኖም ግን ብሩክ ወደ አገሩ ከተመለሰ በኋላ ወዲያውኑ የአውሮፓ ህብረትና አለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት የጋራ እቅድ ከስደት ተመላሾችን ከህብረተሰቡ ጋር ለማቀላቀልና ኑሮአቸውን ለማሻሻል በሚያደርጉት እገዛ የመመዝገብ እድል እንዲያገኝ ተደርጓል። ይህም እገዛ ብሩክ በኢትዮጵያ ሁለት የፀጉር አስተካካይ ቤቶች እንዲከፍትና ለአራት ሰዎች  የስራ እድል እንዲያገኙ አስችሏል።

TMP – 28/05/2019

Photo credit: Shutterstock