ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

ሰለሳ ሁለት በግብፅ ተይዘው የነበሩ ኢትዮጵያውያን ህገ ወጥ ስደተኞች ጁን 11 ላይ ወደ ሀገራቸው እንደተመለሱ አለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ዘግበዋል።

የግብፁ ፕረዚደንት ዓብደል ፈታሕ ዓልሲሲ ለስደተኞቹ ምህረት ያደረጉት አዲሱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብዪ አሕመድ ግብፅን በጎበኙበት ወቅት ነው።

ስደተኞቹ የታገቱት ግብፅን አቋርጠው ወደ አውሮፓ ለመሄድ ሲሞክሩ ነው።

በርካታ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ከሀገር ለመውጣት በምያደርጉት ጥረት እንደ ግብፅ ባሉ ትራንዚት ሀገራት ውስጥ ይታገታሉ።

እነዚህ ስደተኞች በአለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት አማካኝነት የተመለሱ ሲሆን የአውሮፓ ህብረት የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል። የገንዘብ ድጋፉ የተሰጠው ስደተኞቹ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ትራንስፖርት እና ተያያዥ ወጪዎች ለመሸፈን ነው።

አለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በመተባበር ከስደት ተመላሾቹ ሀገራቸው ላይ ወደ ስራ ለማሰማራት የምያስችል ኢኮኖምያዊ፣ ማህበራዊ እና ስነ ልቦናዊ ድጋፍ እንደምያደርግ ተገልፀዋል።

EU-IOM joint initiative የተቀረፀው ልማትን መሰረት ያደረገ የስደተኞች የስራ ትስስር እውን ለማድረግ ነው። በመሆኑም ከ1,100 በላይ ከቻድ፣ ጅቡቲ፣ ኬንያ፣ ሊብያ፣ማላዊ፣ ሞዛምቢክ፣ ማላዊ፣ ኒጀር፣ ሰማልያ-ቦሳሶ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ሱዳን፣ ታንዛንያ፣ የመን እና ዛምብያ የተመለሱ ስደተኞች ጁላይ 2017 ላይ ተመሳሳይ ድጋፍ እንድያገኙ ተደርገዋል።

በተያያዘ ዜና ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ ወደ 1,700 የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ከየመን ተመልሰዋል። በጁን መጀመርያ ላይ 361 ስደተኞች በኢትዮጵያ ኤምባሲ እና አለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት የጋራ ትብብር ወደ ሀገራቸው ገብተዋል። ከተመላሾቹ የመን ላይ ባለ ጦርነት ምክንያት ከየመን የመጡትም ይጉኘበታል።

ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ከስደት ከሚመለሱባቸው ምክንያቶች አንዱ በትራንዚት ሀገራት ላይ ያሉ የፀጥታ ችግሮች ተጠቃሽ ነው።

TMP – 27/07/2018

ፎቶ: ኣይኦኤም፤ ከግብፅ የተመለሱ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በትራንዚት ላይ እያሉ