የጣልያን ‘ፋር ራይት’ መንግስት የደህንነት መርከብ በጣልያን ምድር ላይ እንዳታርፍ ከለከለ

ፖስተር፡ በጣልያኑ ሊግ ፓርቲ አዘጋጅነት በተካሄደው ሰልፍ “ጣልያን ትቅደም” የሚለው ፅሁፍ ይታያል፤ ፒዛ ዲል ዱሞ፤ ሚላን፤ ጣልያን 24 ፌብራሪ 2018

የጣልያን ፋርራይት የሀገር ውስጥ ሚኒስትር ማቲው ሳሊቪኒ ስደተኞችን የጫነች የደህንነት መርከብ በጣልያን ምድርላይ እንዳታርፍ መከልከላቸው ተከትሎ በሰጡት መግለጫ ይህ ተግባር ለሀገራቸው ትልቅ ድል መሆኑ ገልፀዋል። “ባህር ላይ በሞት አፋፍ ያሉ ሰዎች ማዳን ስራችን ነው። ይሁን እንጂ ጣልያንን ወደ የስደተኞች ካምፕ መቀየር ግን አይቻልም።” ብለዋል ሳሊቪኒ።

123 ለብቻ የነበሩ እንዲሁም ሰባት እርጉዝ ሴቶች የሚገኙባቸው 629 ስደተኞችን የጫነች ጀልባ ጣልያን እና ማልታ መሬታቸው ላይ እንዳታርፍ በመከልከላቸው ምክንያት ከ ጁን 10 ጀምረው ጀልባዋ ላይ እንደቆዩ ታውቀዋል።

የፀረ ስደተኞች ሊግ ፓርቲ ሊቀመንበር የሆኑት ሳሊቪኒ ይህች ስደተኞችን የየዛች መርከብ በሀገራቸው ወደቦች ላይ እንዳታርፍ ከልክለው በምትኩ ወደ ማልታ እንዲሄዱ ማድረጋቸው ተነግረዋል። ማልታም በበኩልዋ በጣልያን በኩል የሚመጡት ስደተኞች የመቀበል ኋላፊነት ያላት ጣልያን ናት በማለት ጀልባዋ የማልታ ወደቦች ላይ እንዳታርፍ አድርጋለች።

የፈረንሳይ እና ጀርመን መንግስታት እንዲሁም የአውሮፓ ህብረት እና የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኤጀንሲ፤ ጣልያን እና ማልታ ጀልባዋ በወደቦቻቸው ላይ በማሳረፍ የሰብአዊ እርዳታ ስራ እንዲሰሩ ጥሪ እያቀረቡ ባሉበት ወቅት ባልታሰበ ሁኔታ የስፔን መንግስት ያቺ ጀልባ በሀገሩ ወደብ ላይ እንድታርፍ ፈቃድ መስጠቱም ታውቀዋል። “የሰብኣዊ እርዳታ እና የባሀር ወደብ ዕድል በመስጠት እነዚህ የባህር ላይ መከራዎች ማቃለል ግዴታችን ነው።” ብለዋል የስፔኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼስ።

የድህንነት ጀልባዋ ከመጣን በላይ መጫንዋ በዛ ላይ ደግሞ ወደ ስፔን ለመድረስ የአራት ቀናት ጉዞ ስለሚጠብቃት ጉዞው አደገኛ ነበር። ጣልያን ሁለት ጀልባዎች በመስጠት ጫናው እንዲቃለል አድርጋ ወደ ስፔን ሸኝታቸዋለች።

‘ዶክተርስ ዊዝኣውት ቦርደርስ’ እንዳሉት ምግብ እና የመጠጥ ውሃ በማለቁ ብዙ ስደተኞች የጤና እከል ገጥመዋቸዋል። ሳምባቸው ውሃ የሞላ እንዳሉ እንዲሁም በባህሩ ጨዋማ ውሃ ምክንያት የውስጥ የሰውነት አካል የመቃጠልን ጉዳት የደረሰባቸው እንዳሉ ገልፀዋል።

“ጣልያን ከአሁን በኋላ አንገትዋ የምትደፋበት ምንክያት የለም። አቋምዋ የምያስለውጣት ነገርም የለም።” ብለዋል ሳሊቪኒ። ጀልበዋ ከዳነች ከአንድ ቀን በኋላ ባወጡት መግለጫ ደግሞ “ሀገሪቱ ከደቡብ በሚመጣባት አደጋ እየተጠቃች ነው።” ብለዋል። ደቡብ የሚሉት ያሉ ከአፍሪካ ከሰሃራ በታች የሚመጡትን ስደተኞች ማለታቸው ነው። በዚህም የኔቶ ሀይል እጁ እንድያስገባ ጥሪ አቅርበዋል።

ባለፉት አምስት ዐመታት ብቻ ከ600,000 በላይ አፍሪካውያን ስደተኞች የጣልያን ምድር ረግጠዋል። እንደሚገመተውም ከእነዚህ ስደተኞች ወደ 500,000 የሚጠጉ ስደተኞች አሁምን በሀገሪቱ ውስጥ ይኖራሉ።

የስደት ጉዳይ በቅርብ ጊዜ በወርሀ ማርች በጣልያን በተካሄደው ምርጫ የሊግ ፓርቲ ዘመቻ ቁልፍ ነጥብ ሆነዋል።

TMP – 04/08/2018