ጣልያን ዋናው የስደተኞች መቀበያ ማእከል ዘጋች
በአውሮጳ በትልቅነቱ ይታወቅ የነበረው በጣልያን ሲስሊ ደሴት ሚንዮ የሚገኘው የስድተኞች መቀበያ ማእከል በሐምሌ 9 እ.ኤ.አ በይፋ እንዲዘጋ ተደረገ፡፡
በ2014 እ.ኤ.አ ሚንዮ የስደተኞች ማእከል ቁጥራቸው ከ4000 በላይ የሆኑ ሰዎች ተጠልለውበት የነበረ ቦታ ነው፡፡ በዚህ የተዘጋው ማእከል ጉብኙት ያደረጉት በጣልያን የፀረ ስደተኞች አመለካከት ካለቸው ቀኝ ዘመም መሪዎች አንዱ የሆኑት ሚትዮ ሳልቪኒ ናቸው፡፡ ሳልቪኒ የሚንዮ ሰደተኞች ማእከል በመቃወም ማእከሉ የአፍሪካውያን ወንጀለኞች ስብስብ የሚጠለሉበትና የመንግስት ገንዘብ የሚያባክንበት ነው በማለት ተናግረዋል፡፡
“ይህ ለሲስላውያንና ለጣልያናውያን የሰጡሁዋቸው ተስፋ ነው፡፡ ቁጥሩ ቀስ በቀስ እስከ ዛሬ ድረስ የቀነሰው ዲሆን ወደ ባዶ እንዲወርድ አድርገዋል”ሲሉ ሳልቪኒ ለዘጋቢዎች ተናግረዋል።
ስደተኞቹ በካላብሪያ ክልል ወደ ሚገኘው ማእከል ተዟውረዋል። የስድተኞችና የጥገኝኘት ጠያቂዎች የወደፊት ሁኔታ “ ከዚህ ያነሰና ጥብቅ ቁጥጥር በሚደረግባቸው ማእከሎች ይሆናል” ሲሉ ሳልቪኒ ተናግረዋል።
እንደ አንሳር / ANSA/ የዜና ወኪል በዚህ ዓመት ሰኔ ወር በሚንዮ የሚገኘው ማእከል የመዘጋት ውሳኔ ያስታወቁት ሳልቪኒ ሲሆኑ ይህም የጥገኝነት ጠያቂዎች ቁጥር በ2018 እ.ኤ.አ ከ2,526 ወደ 152 በ2019 እ.ኤ.አ ከቀነሰ በሃላ ነው። ጣልያን ስደተኞች ለማዳን ወደ ወደቦችዋ የሚገቡትን መርከቦች በመከልከልዋ ምክንያት ትላልቆቹ የስድተኞች ማእከል መዘጋትን አስመልከተው ሲናገሩ “አሁን የሚንዮ ተራ ነው” ብለዋል።
ከጣልያን የውስጥ ጉዳይ ሚኒስተር በተገኘው አሀዝ መሰረት ጣልያን ህገ ወጥ ስደትን ለመግታት ባደረገችው ጠንካራ ትግል ምክንያት ወደ አገሪትዋ የሚገቡት ስደተኞች ቁጥር በጣም ቀንሰዋል። የአገሪቱ የውስጥ ጉዳይ ሚኒስተር ባወጣው አሀዝ በዚህ ዓመት 3,073 ስደተኞች ብቻ ወደ ጣልያን መግባታቸውን ያሳያል። ይህ በተመሳሳይ ግዜ አምና 17,000 ካቻማና 85,000 ከነበረው ቁጥር ጋር ሲነፃፀር እጅጉን ቀንሷል። በ2018 እ.ኤ.አ ወደ ጣልያን የባህር ዳርቻዎች የገቡት ስደተኞች ቁጥር ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር በ80 ፐርሰንት ቀንሷል። ሲል የህብረ ብሄር እቅድና ጥናት ማእከል (ISMU). አስታውቋል።
የጣልያን ወደቦች ለስደተኞች አድን ጃልባዎች ዝግ ሲሆኑ ባለፈው ወር የአገሪቱ ካብኔ ያለፍቃድ ወደ ጣልያን የሚገቡት ጀልባዎች ላይ 50,000 ዩሮ የሚደርስ ቅጣት እንዲጣልባቸው የሚያስችል ህግ እንዲፀድቅ አድርጓል።
ተጨማሪ ህግ ወጥ ስድተኞች እንዳይገቡ ለማድረግና የጣልያን ወደቦችን “ለመከላከል” መንግስታቸው ገንዘብ በመመደብ የባህር ጠረፍ ሃይልና የፖሊስ መርከቦችን እንዲሚያሰማሩ ሳልቪኒ ሐምሌ 8 ተናግረዋል። የሊብያ የባህር ጠረፍ ጠባቂዎች አስር የሞተር ጃልባዎች ከጣልያን እንደሚረከቡና ይህም ህግ ወጥ ስድተኞችን በባህር ላይ እያሉ ለመያዝ ያስችላል ብለዋል። አለም አቀፍ የስድተኞች ድርጅት (IOM) በ2019 እ.ኤ.አ ከ3,700 ስደተኞች በላይ በባህር ላይ እያሉ መያዛቸውና ወደ ሊብያ መመለሳቸውን ዘግቧል።
በሊብያ በመካሄድ ላይ ባሉት ግጭቶች ምክንያት ብዙ ስድተኞች በሜዲትሪያንያን ባህር በኩል ደህንነታቸው ባልተጠበቀ ጀልባዎች አደገኛ ጉዞ በማድረግ ወደ ጣልያን ለመግባት እንዲሞክሩ እያስገደዳቸው ነው። በሐምሌ 4, 2019 እ.ኤ.አ በወጣው ዘገባ መሰረት በማእከላዊ ሜዲትሪያንያን የ426 ስደተኞች ሞት ተመዝግበዋል።
TMP – 17/o7/2019
ፎቶ ክረዲት፡–ሲነበርግ/ሽተርስቶክሸ ኮም
የጣልያን የውስጥ ጉዳይ ሚኒስተር ህግ ወጥ ስድትን ለመዋጋት በግንባር ቀደም ተሰልፏል።
ፅሑፉን ያካፍሉ