ኢትዮጵያ ስደተኞች የሚጠቀሙበትን አዲስ የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ የአገልግሎት ማእከል ከፈተች
ኢትዮጵያ አዲስ የአገልግሎት ማእከል በመክፈት ስደተኞች የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ አገልግሎት ማለትም የልደትና የጋብቻ የመሳሰሉትን ምዝገባ እንዲያገኙ እያደረገች ነው፡፡´
ማእከሉ በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ፅ/ቤት ( UNHCR ) እና የተባበሩት መንግስታት የህፃናት እርዳታ ድርጅት ፅ/ቤት (UNICEF) የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ በመሆን በሰኔ 7 ቀን እ.ኤ.አ በምዕራብ ኢትዮጵያ በምበሲ የስደተኞች ካምፕ የተከፈተ ሲሆን ለስደተኞችና ለአከባቢው ማህበረሰብ አገልግሎት የሚሰጥ የመጀመርያ ማእከል ይሆናል፡፡ በአውሮጳ ህብረት የጥገኝነት ጉዳይና የስደትና የማዋሃድ እርዳታ (AMIF) በመታገዝ ስደተኞችን ለማዋሃድ በአገሪቱ ውስጥ በሚገኙ 26 የስደተኞች ካምፕ ተመሳሳይ ማእከሎች ይቃቃማሉ፡፡
ማእከሉ “ የሁሉም አገልግሎት ማእከል” ተብሎም የሚታወቅ ሲሆን ስደተኞችና የአከባቢው ማህበረሰብ ህጋዊ ሰነደዳቸውና ማስረጃዎቻቸው ለማስቀመጥ እንዲሁም ተጨማሪ የመታወቅያ ማስረጃዎች በማገረኘት በአገሪቱ በመንግስት በኩል የሚሰጡትን አገልግለቶች እንዲያገኙ ያሰችላቸዋል፡፡ ከ70000 በላይ የሚሆት በኢትዮጵያ የተወለዱ ህፃናት የልደት ሰርቲፊኬት እንድያገኙ ያደርጋለ ፡፡
“ የሁሉም አገልግሎት ማእከልና በሚሰጡ አገልግሎቶች የመንግስት ከካምፕ ውጭ ፓሊሲ ከካምፕ ውጭ ፖሊሲ፤ ከካምፕ ውጭ የሚኖሩና የሚሰሩ ቡዙ ስደተኞ የሚያገኙቱን አገልግሎቶች ለማመቻቸት የሚያሰችል ነው፡፡ ” በማለት በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ፅ/ቤት (UNHCR) ተወካይ ክለመንቴ ንክዌታ ሰላሚ ተናግረዋል፡፡
በቅርቡ ዓመታት ኢትዮጵያ ለስደተኞች የላቁ መብቶችን በመስጠት ኑሮአቸው እንዲሻሻል በማድረግ ወደ አውሮጳ የሚደረገውን ስደት ለመግታት እያገዘች ትገኛለች፡፡ ኢትዮጵያ በጥር ወር 2019 እ.አ.አ አዲስ ህግ በማፅደቅ 1 ሚልዮን ለሚሆኑ ስደተኞች ከካምፕ ውጭ የመኖርና የመስራት መብት እንዲኖራቸው አድርጋለች፡፡
ይህንን ውሳኔ በዩኒሴፍ የተደነቀ ሲሆን “ የዚህ ማእከል መክፈት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ህፃናት ስደተኞች የልደት ሰርቲፊኬት የማግኘት መብተቻቸውን እንዲገነዘቡ ያደርጋቸዋል፡፡ የልደት ሰርቲፊኬት አስፈላጊነት የማንነት ማስረጃ በመሆን ህፃናት ካለዕደሜ ጋብቻና የጉልበት ብዝበዛ እንዲታደጉ ያደርጋል፡፡ “ ሲሉ በኢትዮጵያ የዩኑሴፍ ተወካይ አደላ ክሆድር አስገንዝበዋል፡፡
“ ለስደተኞችና ለአከባው ማህበረሰብ በአንድ ማእከል አገልግሎት እንዲያገኝ ማድረግ የሁሉም አገልግሎት ማእከል ስደተኞችና የአካባቢው ማህበረሰብ የሚያገኘውን አገልግሎት ለማዋሀድ ጥሩ ጅምር ሲሆን የመጨረሻ ውጤትም አዲስ ህግን ተከትሎ ስደተኞችን ከህብረተሰቡ ጋር የሚያዋህድ ነው፡፡” ሲሉ በአሶሳ የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች የዞን ፅ/ቤት ሃላፊ አምደወርቅ የሃላወርቅ እንደዚህ ያሉ ማእከሎች ስደተኞች ከማህበረሰቡ ጋር ለማዋሃድ እንዴት እንደሚያፋጥኑ ከመግልጽ ባደረጉጽ ንግግር አሰገንዝቧል፡፡
ማእከሉ በዘመናዊ ዲጅታል ቴክኖሎጂ በመታገዝ የስደተኞች የማንነት ወይም የመታወቅያ ማስረጃዎች እንዲሁም ሌሎች የማህበራዊ ኩነቶች/ክንዋኔዎች የምስክር ወረቀቶች በአጭር ጊዜ ውስጥ ለመስጠት ያስችለዋል፡፡ በተጨማሪም ስደተኞችና የአከባቢው ማህበረሰብ የኢንተርኔት አገልግሎት ተጠቃሚዎች እንዲሆኑ ያደርጋል፡፡ ማእከሉ በጥቅምት ወር 2017 እ. አ. አ. ከተከፈተው የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ፕሮግራም አካል ነው፡፡
ኢትዮጵያ ከ900000 በላይ ስደተኞች ተቀብላ በማኖር ስደተኞቸና የአካባቢው ማህበረሰብ ራሳቸው እንዲችሉና ማህበራዊ አገልግሎቶች እንዲያገኙ ለማድረግ የሚያስችለውን አለም አቀፍ የስደተኞች ጉዳይ ስምምነት መሰረት አስፈላጊውን ጥረት በማድረግ ላይ ትገኛለች፡፡
TMP – 19/06/2019
ፎቶ : ARRA
Photo caption: በ2017 እ.ኤ.አ በወጣው መርሃ ግብር መሰረት የስደተኞች የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ተሰጥተዋል፡፡
ፅሑፉን ያካፍሉ