ሕገወጥ ስደትን ለመግታት ያስችል የመጀመሪያው ቢሮ በኢትዮ- ኬንያ አዋሳኝ ድንበር ላይ ተከፈተ

የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (UNDP) እና የምስራቅ አፍሪካ በየነ መንግስታት የጋራ ልማት ባለስልጣን (IGAD) በጋራ በመሆን ሕገወጥ ስደትን ለመከላከል የሚያስችል በኢትዮኬንያ አዋሳኝ ድንበር ላይ የመጀመርያ ቢሮአቸውን ከፈቱ ይህ ቢሮ የአውሮፓ ህብረት የጋራ አዋሳኝ ድንበር ፕሮግራም አንዱ አካል ሲሆን ዓላማውም በአዋሳኝ ድንበር ከፍተኛ ትብብር ማድረግና ሕገወጥ ስደትን ለመከላከል እንዲቻል ነው።

ኢትዮጵያ በአውሮፓ ሆነ በሌሎች አገሮች ተሰደው የተረጋጋና እንዲሁም የተሻለ የኢኮኖሚ ዕድል ለማግኘት ለሚፈልጉ ኤርትራውያን ጥገኝነት ጠያቂዎችና ስደተኞች የመሻጋገሪያ ቦታ ነች።  አዲሱ ቢሮ የህገወጥ ስደት ዋናው መነሻ ምክንያት በማጥናትና መፍትሄ በመስጠት ስደተኞች በሕገወጥ መንገድ እንዳይሰደዱ ማድረግ ከፍተኛ እገዛ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።

ቢሮው በአዋሳኝ ድንበሮቹ ላይ የሚከሰተውን ግጭት አለመረጋጋት ህገወጥ  ስደትና መፈናቀል ምክንያቱን በማጥናት መፍትሄ እንዲያገኝ ያስችላልሲሉ በተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም የአፍሪካ አከባብያዊ አገልግሎት ማእከል (RSCA) የአዋሳኝ ድንበሮች የተቀናጀ ድጋፍ አስተባባሪ (SECCCI) ፕሮጀክት ማናጀር የሆኑት ማትዮ ፎቶንቲኒ ገልፀዋል። 

ይህ ቢሮ በሚያዝያ 3/2019 .. በደቡባዊ ኢትዮጵያ ሞያሌ በተባለች ድንበር ከተማ ላይ በይፋ ተከፍተዋል። ቢሮው ከአከባቢው አስተዳዳሪዎች ማህበረሰብ ሲቪልና  የግል አከላት ጋር በቅርብ ሆኖ በመስራት በኢትዮኬንያ   ዋሳኝ  ድንበር ያሉትን ህዝቦች የኑሮ ሁኔታን በማሻሻል ሕገወጥ ስደትን ለመግታት ይሰራል። 

የቢሮአችን መኖር የተቀናጀ ሰለማዊ ውጤታማ ማህበረ ኢኮኖሚያዊ ስራ በመስራት በአዋሳኝ ድንበር የሚገኙትን ህዝቦች ህጋዊ መንገድ የተሻለ  የገቢ ምንጮች /የኑሮ ሁኔታና የውሃ አጠቃቀም እንዲያገኙ ያስችላልበማለት ፎሮንቲኒ ተናግሯል።

ብዙ የአፍሪካ አገሮች ህገወጥ ስደት የሰው ልጅ ዝውውርና በአዋሳኝ ድንበሮች የሚፈፅሙትን ወንጀሎች ለመከላከል የጋራ ትብብሮችን በማጠናከር ላይ ይገኛሉ። ባለፈው ዓመት በወርሐ ነሓሴ ላይ ኢትዮጵያና ሱዳን በአዋሳኝ ድንበሮቻቸው ላይ ሕገወጥ የሰው ልጅ ዝውውርና ሽብርተኝነትን ለመዋጋት የተቀናጀ  ወታደራዊ ሃይል ለመመስረት ስምምነት ላይ ደርሰዋል። በህገወጥ መንገድ ወደ አውሮፓ ለመሰደድ የሚፈልጉ ኤርትራዊያን በሱዳን  በኩል የሚጓዙ ሲሆኑ ይህም ለህገወጥ የሰው ልጅ ዝውውር ተጠቂዎች እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል።

በአዋሳኝ ድንበሮች ላይ ያለውን የፀጥታና ትብብር ለማሻሻል የአውሮፓ ህብረት ከአፍሪካ  ህብረት ጋር አብረው በመስራት በአህጉሪቱ የሚታየውን የህገወጥ ስደት ዋናው ምክንያት ለማስቀረት የስራ ዕድሎችን  ለመፍጠር በመስራት ላይ ይገኛል።

TMP – 11/04/2019

ፎቶ hecke61 / Shutterstock.com / People at the African Market of Moyale in Ethiopia, 17. October 2012