ከስደት ተመላሹ ወደ አውሮፓ ያደረገው እጅግ አሰቃቂ ጉዞ
ሚራን ጋርዲ የኮርዲሽ ወጣት ስደተኛ ሲሆን ምንም እንካን አውሮፓ ለመድረስ ህይወቱ አደጋ ውስጥ ቢከትም ወደ ኩርዲስታን ለመመለስ ወስናል፡፡ የድተኞች ፕሮጀክት ሚራን ስለአደረገው አደገኛ ጉዞና ስለአውሮፓ የነበረውን ሕልም ለምን እንደተወ አነጋግሮታል፡፡
ሚራን የ20 ዓመት ወጣት እንደሌሌቹ ኩርዳውያንን በሕገ ወጥ የሰው ልጅ አዘዋዋሪዎች በኩል በሚሰጠው ያልተጨበጠ ተስፋና በቀጥታ የሐሰት ገለፃ በመማለል በነሓሴ 2015 እ.ኤ.አ ከኤርቤል ወደ ቱርክ በመጓዝ በጀርመን አገር ጥገኝነት ለመጠየቅ ወደ አውሮፓ ለመሰደድ ተገደል፡፡
ሚራን አውሮፓ ለመድረስ በተቀናጀ መንገድ ለሚንቀሳቀሱት ህገ ወጥ የሰው ልጅ አዘዋዋሪዎች ገንዘብ ከፍለዋል፡፡ ሁሉም ህገ ወጥ የሰው ልጅ አዘዋዋሪዎች የሚሰሩት ስራ በተቀናጀ እና በተወሳሰበ መንገድ ነው፡፡ እኔ ያገኘሁት ሰው በጀርመን አገር የሚኖር ነበር ።እርሱም በቱርክ ከሚገኙት በማገናኘት በቱርክ የተቀበሉን ደግሞ ቡልጋርያ ለሚገኘው በማስረከብ እርሱም በሰርቢያ ለሚገኘው ህገ ወጥ እንዳስረከባቸው ሚራን ይገልፃል፡፡
ሚራን ወደ አውሮፓ ያደረገውን አስቸጋሪ ጉዞ እንዲህ በማለት ይናገራል፡፡ ጀርመን ለመድረስ ሊገለፅ በማይችል መከራ ውስጥ አልፈናል፡፡
ሚራን በሓሰት ተስፋ በማማለል በአውቶቢስ ወደ አውሮፓ ለመድረስ እንደሚቻልና ይህም የጥቂት ሰዓታት ጉዞ እንደሚያስፈልግ ህገ ወጥ የሰው ልጆች አዘዋዋሪዎች እንደነገሩት ገልፀዋል፡፡ ሆኖም ግን ሀቁ እንደነገሩት አልነበረም፡፡
”ጀርመን ለመድረስ ከ50 ሰዓታት በላይ ተጉዘን በቆሻሻና ዝናብ ባለበት ሁኔታ በቡልጋሪያ ጫካዎች ተጓዝን፡፡ ሁለት ጊዜ በቡልጋርያ ፖሊሶች ተይዘን ተደብድበን ገንዘባችንን በመውሰድ ወደ ቱርክ ድንበር ኤድሪነ እንድንመለስ አደረጉን በማለት ይናገራል፡፡
ሚራን በመጨረሻም ጀርመን አገር በመግባት የጥገኝነት ማመልከቻ ያቀረበ ቢሆንም ህይወት አውሮፓ ውስጥ እንደጠበቀው ሆኖ አላገኘውም፡፡
እስከ 2015 እ.ኤ.አ በጀመርመን ውስጥ ይኖሩ የነበሩትን 9000 ኢራቃውያን በአለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት በፈቃደኝነት የመመለስ ፕሮግራም በመታገዝ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ተደርገል፡፡
አሁን ሚራን ትንሽ የቱሪዝም ቢዝነስ በኩርዲስታን ከፍተዋል፡፡ እርሱ በህገ ወጥ የሰው ልጅ አዘዋዋሪዎች የከፈለውን 7500 አሜሪካን ዶላር ለዚህ ቢዝነስ ማሻሻያ አውሎት ቢሆን ኖሮ ጥሩ ይሆን እንደነበር ለስደተኞች ፕሮጀክት ተናግረል፡፡ የገንዘብ ኪሳራ ቢያጋጥመውም ወደ ኩርዲስታን በመመለሱ ምክንያት ደስተኛ ነው፡፡
እዚህ ለመመለስና የተሻለ ተስፋ ለማግኘት ወሰንኩኝ ፣ ቤተሰቦቼም ናፈቁኝ ከእንግዲህ ወዲህ ብቻዬን ለመኖር አልችልም፡፡
TMP – 08/03/2019
ስድተኞች ወደ አውሮፓ ለመድረስኣያሌ አገሮች እንደ መተላለፊያ ይጠቀሙለታል
ቃለ ምልልሱን ያካሄደው ፋሒም ዳቫቶዛከሪን
ፅሑፉን ያካፍሉ