የአፍሪካ ቀንድ ስደተኞች ወደ ሀገር ቤታቸው ይመለሱ ዘንድ ተጨማሪ ድጋፍ እየተደረገላቸው ነው

የአፍሪካ ቀንድ ህገ ወጥ ስደተኞች ወደ ሀገር ቤት እንዲመለሱ ፈቃደኛ ከሆኑ ተጨማሪ ድጋፍ ሊደረግላቸው መሆኑ ተገለፁ። መይ 2019 ላይ አለም አቀፉ የስደተኞች ተቋም አይኦኤም እንዳለው የአውሮፓ ህብረት ለዚሁ ዓላማ ሲባል 18 ሚልዮን ዩሮ ተጨማሪ ድጋፍ ለመስጠት ፈቃደኛ ነው።

ይህ አዲስ ድጋፍ የአውሮፓ ህብረት ከአይኦኤም ጋር በጋራ በያዙት እቅድ ድጋፍ ለማድረግ ከተበጀተ 43 ሚልዮን ዩሮ የተወሰደ መሆኑ ለማወቅ ተችለዋል። ይህ ፕሮግራም ስደተኞች ከሚነሱበት አከባቢ ጀምሮ ለምያጋጥማቸው የህይወት ፈተና ድጋፍ ለማድረግ ያለመ ነው። ዋነኛ ትኩረቱ ደግሞ ኢትዮጵያ፣ ጅቡቲ፣ ሶማልያ እና ሱዳን ላይ እንደምያደርግ ተገልፀዋል። ይህ የተመረጠበት ምክንያትም በአፍሪካ ከፍተኛው የህገ ወጥ ስደት ፍሰት የሚታይበት ዞን ስለሆነ ነው።

እስካሁን ድረስ በመቶዎች የሚቆጠሩ በስደት ዙርያ የሚሰሩ ባለሙያዎች ህገ ወጥ የሰው ልጅ ደላሎችን በመቆጣጠር ዙርያ ስልጠና ወስደዋል። እንዲሁም 12,000 በላይ በህገ ወጥ የሰው ልጅ ደላሎች አደጋ የደረሰባቸው እና ተጋላጭነት ያላቸው ስደተኞች በዚሁ ፕሮግራም ድጋፍ አግኝተዋል።

ይህ ፕሮግራም ስደተኞች ድህንነታቸው እና ክብራቸው ተጠብቆ ወደ ሀገር ቤታቸው እንዲመለሱ አልሞ የሚንቀሳቀስ ነው። ይህ ብቻ ሳይሆን ስደተኞች በሀገር ቤት ያለ የስራ ዕድል ውስጥ እንዲሳተፉ እና አዲስ ህይወት እንዲጀምሩ የበኩሉን ያበረክታል።

አብዛኛው በዚህ ዞን የሚሰራ ስራ 100 ሚልዮን በላይ የህዝብ ብዛት ባላት ኢትዮጵያ ውስጥ የሚከወን ይሆናል።  አፕሪል 2018 ላይ ወደ ሀገር ቤት እንዲመለሱ ድጋፍ ከተደረገላቸው 3,804 ስደተኞች አብዛኛዎቹ በጅቡቲ በኩል ወደ የመን በዛም ወደ ገልፍ ሀገራት የተሰደዱ ኢትዮጵያውያን መሆናቸው ይታወሳል። አዲስ ተመላሾቹ ኢትዮጵያ ውስጥ የስራ ፈጠራ ስልጠና እንዲሰጣቸው ጥያቄ ማቅረባቸው ይታወሳል። በመሆኑም ወደ 700 የሚጠጉ ስደተኞች ካፊቴርያ፣ ሱቆች፣ የእንጨት እና የብረት ስራዎች እንዲሁም የከተማ እርሻ ስራዎች መክፈት የምያስችላቸው ስልጠና ወስደዋል።

2018 ላይ የተደረገፈ ድጋፍ 2,300 ኢትዮያውያን የታገዙበት ሲሆን ከእነዚህ ደግሞ 1,672 የስነ ልቦና ድጋፍ የተደረገላቸው ናቸው። 2,000 ስደተኞች ደግሞ የህክምና ድጋፍ እንዲሁም የትምህርት ዕድል ተሰጥተዋቸዋል።

TMP – 14/06/2019

Photo credit: ምብራንድ85 / ሻተርስቶክ

Photo caption: አንድ ዛፍ በጅቡቲ በረሀ ላይ። በመተዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ህገ ወጥ ስደተኞች በእግር በጅቡቲ በኩ ወደ የመን ይጓዛሉ።