ኤርትራውያን ስደተኞች ከሊብያ ወደ ኒጀር እንዲዘዋወሩ ተደረገ
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳዮች ፅ/ቤት እንደገለፀው በሊብያ ትሪፖሊ ከተማ የአየር ማረፍያ የተገኙ 159 ኤርትራውያን ስደተኞችና አሳይለም ጠያቂዎች ሌላ ቦታ እስኪፈለግላቸው ድረስ ወደ ኒያምኒ የትራንዚት ማእከል መወሰዳቸው ገለፀ። ይህ የሆነውም ፌቡራሪ 13/2019 መሆኑም ተገልፀዋል።
በዚሁ የፈረንጆች አመት የመጀመርያው ስደተኞችን ከቦታ የማዘዋወር ስራ የተጀመረው ጃንዋሪ 28 ላይ ሲሆን 130 ስደተኞች ከሊብያ ወደ ኒጀር እንዲንቀሳቀሱ ተደርጓል። በዚሁ አመት ሌሎች የሲርያ፣ ኤርትራና ሱዳን ስደተኞችና አሳይለም ጠያቂዎች ሌላ የሚቆዩበት ሀገር ፍለጋ ወደ ሮማንያ ሄደው እንዲቆዩ ተደርጓል።
ዩኤንኤችሲአር እንደዘገበው እነዚህ ስደተኞችና የአሳይለም ጥያቄ አቅራቢዎች በተለያዩ የሊብያ የስደተኛ ማቆያ ማእከላት በከፍተኛ ችግርና የጤና ቀውስ ውስጥ የነበሩ ናቸው።
አንገሶም የተባለ ኤርትራዊ ወጣት “ሊብያ ውስጥ መጀመርያ በህገ ወጥ የሰው ልጅ ነጋዴዎች ስር ከዛ በኋላም በሊብያ የተለያዩ ማቆያ ማእከላት ውስጥ ለአራት አመታት ያክል ጊዜ ስሰቃይ ቆይቻለሁ። ወርቃዊ የህይወቴ አካልም ተበልቻለሁ። ይሁንና ጸሎቴን የሰማ ፈጣሪ አግዞኝ አሁን አዲስ ህይወት ልጀምር ነው።” ብለዋል።
ይህ ስደተኞችን ወደ ሌላ ቦታ የማዘዋወር ስራ ከተጀመረ 2017 የፈረንጆች አመት ጀምሮ እስከአሁን በጠቅላላ 3,175 ስደተኞችን አዘዋውረዋል። ከዚህ ቁጥር 2491 ወደ ኒጀር ፣ 415 ወደ ጣልያን፣ እንዲሁም 269 ወደ ሮማንያ እንዲዘዋወሩ ተደርጓል። ከተዘዋወሩ የስደተኛ ቁጥር ረዳት የሌላቸው 148 ህፃናት ደግሞ ኒጀር ላይ አሉ።
“አብዛኛዎቹ ስደተኞች ሊታሰሩ የቻሉት በሊብያ የስደተኞች ህግ መሰረት በአጋጣሚ የተያዙ ናቸው።” ደሰምበር 2018 ላይ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሊብያ የሰብአዊ መብት አያያዝ አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ። መግለጫው ጨምሮ እንዳለው “የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ጨምሮ በፈታኝ ሁነት ውስጥ ያሉ የውጪ ሀገር ዜጎች የመጣ ሁሉ እያፈሱ የማሰር ሰለባዎች ናቸው።”
ብዙ ስደተኞች የሰው ልጅ እንዲኖርበት ተብሎ ባልተሰራና ከፍተኛ የፅዳትና ተያያዥ ችግር ያሉባቸው ማቆያ ማእከላት ውስጥ እንዲቆዩ በማድረግ ለከፍተኛ ችግር ይጋለጣሉ። የሊብያ ባለስልጣናት ወይም የተባበሩት መንግስታት አካላት ወደ ሌላ ቦታ እስክያዘዋዉሩዋቸው ድረስ እዛ እንዲቆዩ ይደረጋል።
አለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት በ2018 የፈረንጆች አመት 16,753 ስደተኞችን ከሊብያ ወደ 32 የአፍሪካና ኤስያ ሀገራት እንዲዘዋወሩ መደረጋቸው ገልፀዋል።
እስከ ፌቡራሪ 2019 ብቻ በድምር 56,588 አሳይለም ጠያቂዎችና ስደተኞች ሊብያ ላይ እየኖሩ እንዳሉ ዩኤንኤችሲአር ዘግበዋል። ከእነዚህ 4,194ቱ የተለየ ትኩረት የሚሹ ናቸው።
በ2018 መጨረሻ ቢያንስ 663,445 ስደተኞች በሊብያ ውስጥ እንዳሉ የታወቀ ሲሆን ከእነዚህ ስደተኞች 94%ቱ ከአፍሪካ ሀገራት የመጡ መሆናቸው የአለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ገልፀዋል።
TMP – 05/03/2019
ፎቶ ከሬዲት: አዲስሮን ቻሲን/ሻተርስቶክ
ፅሑፉን ያካፍሉ