አዲስ የስደተኞች የግብአት ማእከል፡ በምስራቅ ሱዳን
አለም አቀፉ የስደተኞች ተቋም አይኦኤም እንደገለፀው ማርች 5 ቀን 2019 አዲስ የስደተኞች የግብአት ምንጭ በምስራቃዊ የሱዳን ክፍል ገዳሪፍ ከተማ ተከፍተዋል።
ይህ በምስራቅ አፍሪካ ከተከፈቱት ማእከላት የቅርቡ እንደሆነ የተነገረለት ማእከል ህገ ወጥ ስደተኞች የምያጋጥማቸው የመረጃ እጥረት የምያቃልል፣ ህክምናዊ ድጋፍ የሚሰጥ፣ ስነ ልቦናዊ ትብብር የምያደርግ እና በፈቃዳቸው መመለስ ለሚፈልጉም እንዲሁ ድጋፍ የሚሰጥ ማእከል መሆኑ ታውቀዋል።
ይህ ማእከል ለተለያየ ዓላማ ለሚሰደዱ ስደተኞች፣ በህገ ወጥ የሰው ልጅ ነጋዴዎች ግፍ ለተፈፀመባቸው አካላት፣ በስደት ዙርያ ስራ ለሚሰሩ አካላት ወዘተ ድጋፍ እንዲሰጥ ተደርጎ የተከፈተ ነው። ማእከሉ ስደተኞች በአስቸኳይ የምያስፈልግዋቸው ድጋፍ እና ክትትል እንድያገኙ ይረዳል። በሱዳን የመጀመርያው ተመሳሳይ ማእከል የተከፈተው በ2015 በካርቱም ከተማ ነበር።
ሱዳን ህገ ወጥ ስደተኞች የሚነሱባት፣ የሚተላለፉባት እና የሚቆዩባት ሀገር ናት። የገዳሪፍ ክልላዊ መንግስት የሀገሪቱ ምስራቃዊ ክፍል የሚይዝ ሲሆን ከኢትዮጵያ የሚዋሰን ነው። በመሆኑም ከአፍሪካ ቀንድ የተለያዩ ሀገራት የሚመጡ ስደተኞች ወደ ሰሜናዊ አፍሪካ በዛውም ወደ አውሮፓ ለመሄድ የሚጠቀሙበት መስመር ነው።
ከአፍሪካ ቀንድ ወደ አውሮፓም ሆነ ወደ አርብያን ገልፍ የሚሰደዱ ዜጎች ወደ ብዝበዛ እና የመብት ጥሰት ያላቸው ተጋላጭነት ከፍተኛ ነው።
የአይኦኤም ቺፍ ኦፍ ሚሽን ካትሪን ኖርቲንግ ማእከሉ ሲከፈት ተገኝተው “እኛ ከሀገሪቱ መንግስት በመሆን ስደተኞች ያላቸው ከፍተኛ ተጋላጭነት ለመቀነስ እና ድጋፍ እና አገልግሎት ለማግኘት በመስራታችን ዕድለኞች ነን።” ብለዋል ።
እነዚህ ማእከላት ህገ ወጥ ስደተኞች ትክክለኛ የስደት መረጃ እንድያገኙ፣ በስደት ሂደቱ ህይወታቸው አደጋ ላይ እንዳይጥሉ መደረግ ስላለባቸው ነገሮች ምክር እንድያገኙ እንዲሁም ስደተኞች በስደት ጉዞው ላይ ሊኖሩዋቸው ስለሚችሉ መብቶች እና ግዴታዎች ወዘተ ድጋፍ የሚሰጡ ናቸው።
TMP – 25/03/2019
ፎቶ: የቪጄ ጎደና/ሹተርስቶክ. ገዳሪፍ ሱዳን
ፅሑፉን ያካፍሉ