በዚህ ዓመት በሜዲትራንያን የስደተኞች ሞት ከሁለት ሺ እንደሚያልቅ ታውቃል

በኖቨምበር 2018 / .. 17 ስደተኞች በጉዞ ላይ እያሉ ከሞቱ በኃላ የተባበሩት መንግስታት ከፍተኛ የስደተኞች ኮምሽነር /.ኤን.ኤች..አር/በዚህ ዓመት በሜዲትራንያን ባህር ጉዞ የሟቾች ስደተኞች ቁጥር ከሁለት እንደሚበልጥ አስታውቋል፡፡

በግምት 105,000 /አንድ መቶ አምስት ሺህ/ የፖለቲካ ተገን ጠያቂዎች ወደ አውሮጳ እንደገቡና ይህም ከቅድመ 2014 / መቀነስ እያሳየ ሲሆን ባህር ውስጥ የሚሞቱትን ግን ጨምሯል፡፡ የሜዲትራንያን ባህር ለበርካታ ዓመታት በዓለም ውስጥ ስደተኞች በብዛት የሚሞቱበት የጉዞ መስመር /ቀጠና/ እንደሆነ ጨምረው ገልፀዋል፡፡ ይህም በዚህ ሁኔታ መቀጠል እንደሌለበት የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮምሽነር ቃል አቀባይ ቻርሊ ያዝሊ በኖቨምበር 2018 / .. ጄኔቫ ለስዊዘርላንድ ውስጥ ገለፀዋል፡፡ይህንን ሁኔታ ለማለቅም የተ.. የስደተኞች ኤጀንሲ አስቸኳይ እርምጃ እንዲወስድ በተደጋሚ ጥሪ አቅርቧል፡፡

ስፔይን 53,000 /አምሳ ሶስት / የሚበልጡ ስደተኞች በባህር ተጉዘው ከደረሱባት ሃገር ከፍተኛውን ስፍራ ይዛለች ይህም በግሪክና ጣልያን ካሉት በእጥፍ የሚሆን ማለት ነው፡፡ እንደ አለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት ዘገባ ከሆነ ከነዚህ ሁለት ሟቾች ግማሽ የሚሆኑት ወደ ጣልያን ባህር ጠረፍ ሲጓዙ እንደሆነ ታውቋል፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያትም በጣልያን የቀኝ ዘመም ፓርቲ ተመርጦ በስደተኞች ላይ አዲስ ማእቀብ /እገዳ/ በማስተላለፍና የነፍስ አድን ጀልባዎች በወደቦች አከባቢ 26 ነሓሴ 2018 / ጀምሮ ክልከላ በማድረጉ ምክንያት መሆኑ ታውቋል፡፡

ማንኛውም ጀልባ ለነፍስ ማዳን ስራ መሰማራት የሚችለው እርዳታ ለሚያስፈልጋው ሰዎች ብቻ መሆን እንዳበት ያዝሊ ገልፀዋል፡፡ የተ.. የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን የሚጨነቀው ለህጋዊ የአቅርቦት ውስንነት ለተጠለባቸው ብዙ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች /መያዶች/ መሆኑና ይህም የፍለጋና የአሰሳ ስራ አኳርየስን ጨምሮ እንደሚያካሄድ አስታውቋል፡፡ ለዚህም ቀደም ሲል ከተጠራቀመው ችግር ውጤትና በማእከላዊው ሜዲትራንያን በአሁን ጊዜ ምንም ዓይነት የነፍስ ማዳን ስራ የሚሰራ እንደሌለ ጨምረው ገልፀዋል፡፡

በሊቢያ የጠረፍ ጠባቂዎች የሚደረጉት ጥረቶች አመስግነዋል የተ.. የስደተኞች ኤጀንሲ ጥረቶቹ ተጠናክረው እንዲቀጥሉና በዓለም አቀፍ ውሃዎች ውስጥ የዳኑ ስደተኞች ዋስትና ወደ ሌለው ቦታ ወደ ሊቢያ መመለስ እንደሌለባቸው ገልፀዋል፡፡ አለም አቀፍ የውሃ አካል ሲባል 22.22 ኪሎ ሜትር ወይም 12 የባህር ማይልስ ከሊቢያ የባህር ጠረፍ ያለው ቦታ መሆኑ ታውቋል፡፡

TMP – 16/11/2018

ፎቶ፡– MOAS.eu.  በሜዲትራንያን የባህር ጠረፍ ሊቢያ በጭንቀት ላይ ያሉት ስደተኞችን የሚያሳይ ነው