ሊብያ ውስጥ ስደተኞች ለትርፍ ሲባል ታግቷል ከባህር ውስጥ ይልቅ በየብስ ጉዞ ህይወታቸው የሚያልፉ ስደተኞች ይበዛሉ። በሁለቱም አገሮች መካከል ያለው ድንበር የተዘጋ ቢሆንም ኤርትራውያን አሁንም ወደ ኢትዮጵያ መሸሻቸውን አላቋረጡም ጣልያን ፤- በባህር ላይ ተገኝተው ወደ ሊብያ እንዲመለሱ በሚገደዱ ስደተኞች ላይ ከሊብያ ጋር የነበራት ስምምነት አድሳለች ኢትዮጵያ ፤ ለስደተኞችና ለዜጋዋ እኩል እድል የተረጋገጠባት አገር

ከሊብያ ወደ ጣልያን በምያስኬድ የባህር መንገድ የህይወት አድን መርከቦች የሉም!

ከኦገስት 26 ጀምሮ መካከለኛው ሜዲትራንያን ባህር ጥሎ በወጣ የህይወት አድን መርከብ ምክንያት በሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች ከፍተኛ የሞት አደጋ ጥላ ስር እንዳሉ ዘ ጋርድያን ዘግበዋል።  

ለሰብአዊ ስራ ተብሎ የህይወት አድን መርከብ ሜዲትራንያን ባህር ላይ   ማኖር ከተጀመረ ከ2015 ወዲህ ረጅሙ ያለ መርከብ ይሄን ያክል ጊዜ መቆየት ለመጀመርያ ጊዜ መሆኑን ተነግረዋል።   በጣልያን ከመጣው  የቀኝ ዘመም መንግስት ፖሊሲ  በኋላ ግን በሀገሪቱ ወደቦች ሲንቀሳቀሱ የነበሩ  የህይወት አድን መርከቦች እና ኤንጂኦዎች ስራዎቻቸው እንደወትሮ ለመፈፀም ተቸግረዋል። ማልታም የጣልያን ውሳነ ተከትላ ከጣልያን ተገፍተው የሚመጡ መርከቦች ላለመቀበል ወደቦችዋ ለመዝጋት ተገድዳለች።  

በኤንጂኦዎች ከሚንቀሳቀሱ ጀልባዎች በተጨማሪም የሊብያ የባህር የፀጥታ አካላት  በሊብያ የጠረፍ ጠባቂዎች እየተጫኑ  ስደተኞችን ወደ ሰሜን አፍሪካ ለመመለስ ይወሰዳሉ። ይሄም በ2017 ከጣልያን ጋር በተደረገ ስምምነት መሰረት እየተደረገ ያለ ነው። ይሁንና ከመንገድ ተይዘው ወደ ሊብያ የሚወሰዱ ስደተኞች በሀገሪቱ ባሉ የስደተኛ ማቆያ ማእከላት ኢ ሰብአዊ በሆነ መንገድ እንደሚያዙ ይነገራል።   

ከአለም አቀፉ የስደተኞች ተቋም የተገኘ መረጃ እንደምያሳየው በ2017 ብቻ ጣልያን ሀገር መድረስ ከቻሉ 100, 319  ስደተኞች 2,383 ስደተኞች በባህር ጉዞ ላይ ለሞት ተዳርጓል። በ2018 ግን የህይወት አድን መርከቦች ወደ ስራ በመግባታቸው ምክንያት ከማልተስ እና ጣልያን ባለስልጣናት የሚደርሳቸው ግፊት ተቋቁመው 20, 319 ስደተኞች በሰላም የጣልያን ምድር የረገጡ ሲሆን የሞት አደጋው ከባለፈው አመት በተሻለ ወደ 1,500 ዝቅ ብለዋል።

እንደ የአይኦኤም መረጃ ከሆነ በሜዲትራንያን ባህር የምያጋጥም የሞት አደጋ ከባለፈው አመት የተሻለ ቢሆንም የሞት መቀነሱ ጣልያን ሃገር ከሚደርሱ ስደተኞች ቁጥር በንፅፅር ሲታይ በተለይም ባለው ጥቂት ወራት የተወሰነ ጭማሪ አሳይተዋል። በመሆኑም በተጠቀሰው አጭር ጊዜ የሞት አደጋው በሶስት እጥፍ ጨምረዋል።

ከአንድ ሳምንት በፊት ከጣልያንዋ ወደብ ላምፑድሳ 24 ማይል ርቆ በሚገኝ የባህር አካል አንድ ህገ ወጥ ደላላ 14 ስደተኞች ይዞ ሲሄድ ዝም ብላችሁ አይታቹሁታል በሚል ስድስት ዓሳ አጥማጅ ቱኒዝያውያን ታስረዋል።  እንደ ዘ ጋርድያን ዘገባ ከሆነ የእነዚህ ዓሳ አጥማጅ የህግ አማካሪ አጥማጆቹ እንደ ማነኛውም የባህር ላይ ገጠመኝ ስደተኞቹን ህይወታቸው ለማትረፍ ወደ ጣልያን አከባቢ ተጠጉ ማለታቸው ምንም ማለት እንዳልሆነ አስረድተዋል።

ሮማ የኤንጂኦ አካላት የሊብያን ጠረፍ ታክከው ከምያደርጉት የባህር ህግ ጥሰት  መራቅ የምያስችላት መንገድ አስተካክላለች። በአሁን ሰዐት የንግድ መርከቦች እና ዓሳ አጥማጅ አካላት ብቻ ናቸው ያሉት። እንደውም አንዳንዶቹ ህይወታቸው አደጋ ላይ በመጣል ህጉን እንዲከበር ይጥራሉ።” ብለዋል በፓሎሮሞ ዩኒቨርስቲ የህግ ፕሮፌሰር የሆኑትን ፋለቪዮ ቫሳሎ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የአፍሪካ እና የአውሮፓ ህብረት ሚኒስትሮች ቪያና ላይ በስደት ዙርያ ባደረጉት የምክክር መድረክ የጣልያን አውስትራልያ ሚኒስትሮች በሚድትራንያን ባህር በሚደረገው ጉዞ እና በአሳይለም ጥየቃ ጉዳዮች ላይ መነሻ ሀሳብ ይዘው ቀርበዋል።  

በሜዲትራንያን  ባህር በኩል ወደ አውሮፓ በሚገቡ መርከቦች ላይ እርዳታ ያስፈልጋቸው እንደሆነ ለማረጋገጥ አስፈላጊ ፍተሻ እናደርጋለን” ብለዋል   የአውስትራልያው የሀገር ውስጥ ሚስትር ሀርበርት ኪክል   ከስብሰባው በኋላ በሰጡት መግለጫ።  

ወደ መርከብ ከገባህ በኋላ ደህና ትመስላለህ” ሲሉ የተናገሩት ኪክል አክለውም ፍተሻው አስፈላጊ መሆኑ በመግለፅ “ጥቂት ቀናት ብቻ የሚወስድ ነው።” ብለዋል። የአሳይለም ዕድላቸው ጠባብ የሆኑት አካላትም መግባት እንደማይፈቀድላቸው ገልፀዋል ሚኒስትሩ።  

ሰዎቹ አንዴ እግራቸው የአውሮፓን መሬት ከረገጡ መልሰህ ለማስወጣት በጣም ከባድ ስራ እና ውድ ነው።” ብለዋል ኪክል በመግለጫቸው።  

የአውስትራልያው የሀገር ውስጥ ሚኒስትር በበኩላቸው “አሳይለም መጠየቅ ያለበት ከአውሮፓ ህብረት ውጪ ከሆነ ብቻ እና ይሄም መፈፀም ያለበት ከአውሮፓ ህብረት ውጪ በሆነ አካል” እንደሆነ ያላቸው እምነት ገልፀዋል።   

የፎቶ ገለፃ: የሚታየው የፕሮአክቲቭ ኦፕን አርምስ መርከብ ሲሆን ጁላይ ወር ላይ የባርሴሎና ወደብ ትቶ ሲወጣ ሲሆን አሁን የጣልያን የእርዳታ እጅ ከመሰብሰብ ጋር በተያያዘ ወደቡ ላይ ትታያለች።  መርከብዋን የምያስተዳድር የኤንጂኦ አካል እንደሚለው ከሆነ መርከብዋ በተለይ በዊንተር ወቅት ከዚህ በላይ እዛ መቆየት አትችልም።