ኤርትራውያን ስድተኞች በኢትዮጵያ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ለመማር በብዛት ተመዝግበዋል
በሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች በአገሪቱ ውስጥ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ለመማር የተመዘገቡ መሆናቸው የተባበሩት መንግስታት የስድተኞች ጉዳይ ፅህፈት ቤት አሰታውቀዋል።
በተባበሩት መንግስታት የስድተኞች ጉዳይ ፅህፈት ቤት ገለፃ መሰረት በአሁን ጊዜ 196350 የሚሆኑ ስደተኞች በኢትዮጵያ በተለያዩ የትምህርት ደረጃዎች ለመማር ተመዝግበዋል። ከ60 ፐርስንት በላይ /126000/ የሚሆኑ ስድተኞች በአንደኛና በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በመከታተል ሲሆኑ፤ 3000 ስድተኞች ደግሞ በኮሌጅና ዩኒቨርስቲ ደረጃዎች ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ መሆናቸውን የተባበሩት መንግስታት የስድተኞች ጉዳይ ፅህፈት ቤት አስገነዝበዋል። ከ30 ፐርሰንት በላይ የሚሆኑ ስደተኞች በህፃናት መንከባከብያ ወይም መውአለ ህፃናት የተመዘገቡ ናቸው።
በዚህ አመት ጥር ወር 2017 እና 2018 እ.ኤ.አ ከአስሩ ሰባት ( 7/10) የሚሆኑ በስደተኞች ካምፕና ከካምፕ ውጭ የሚገኙ ስድተኞች ልጆች የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ለመከታተል በመደበኛ ትምህርት መመዝገባቸውን የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ፅፈት ቤት ዘግበዋል።
በቅርቡ አመታት ኢትዮጵያ ስደተኞች ህይወታቸውን እንዲያሻሽሉና ወደ አውሮፓ የሚደረገውን ስደት ለመግታት ስደተኞች የተለያዩ መብቶች እንዲያገኙ ፈቅዳለች። በጥር ወር 2019 እ.ኤ.አ የኢትዮጵያ ፓርላማ አንድ ሚልዮን የሚሆኑ ስድተኞች ከካምፕ ውጭ እንዲኖሩ የሚያስችል አዲስ ሕግ አፅድቃለች። አዲስ ሕግ ስድተኞች አንደኛ ደረጃ ትምህርት፣ የስራ ፍቃድና ፋይናንሳዊ አገልግሎቶች ለምሳሌ የባንክ አገልግሎት እንዲያገኙ ያደርጋል። የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ዋና ኮሚሽነር ፍሊፓ ግራንድ “ኢትዮጵያ ያፀደቀችውን አዲስ ሕግ በአፍሪቃ ከበለጡ ተራማጅ የስድተኛ ፖሊስዎች መካከል አንዱ ነው” በማለት ያላቸውን አድናቆት ገልፀዋል።
ኢትዮጵያ ስደተኞችን በመቀበል በአፍሪካ በሁለተኛ ደረጃ የምትገኝ ሆና ስደተኞችን በበለጠ ከህብረተሰቡ ጋር እንዲቀላቀሉ ለማድረግ እየተጋች እንደምትገኝ የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ፅህፈት ቤት አስገነዝበዋል። ለምሳሌ በህዳር 2017 እ.ኤ .አ የኢትዮጵያ መንግስት ስድተኞችን ከህብረተሰቡ ጋር እንዲቀላቀሉና መሰረታዊ የሆኑትን ማህበራዊ አገልግሎቶችና ኢኮኖሚያዊ ጠቄሜታዎችን እንዲያገኙ ለማድረግ ሁሉን አቀፍ የስደተኞች መመርያ በስራ ላይ እንዲውል አድርገዋል። በታህሳስ 2018 እ.ኤ.አ ኢትዮጵያ ስደተኞችን ከህብረተሰቡ እንዲቀላቀሉ ለማድረግ በአገሪቱ የሚገኙትን ሁሉም 27 የስድተኞች ካምፕ በሚቀጥሉት 10 አመታት ውስጥ እንደምትዘጋ አስታውቃለች።
በተጨማሪም ኢትዮጵያ በአገሪቱ የሚገኙትን ስድተኞች ህይወታቸውን ወይ ኑሮአቸውን እንዲሻሸል ለማድረግ ከአውሮፓ መንግስታት ጋር እየሰራች ትገኛለች።ለምሳሌ በ2018 እ.ኤ.አ መጨረሻዎቹ ኢትይጵያ ከይናይትድ ኪንግደም ጋር የ115 ሚልዮን የዩናይትድ ኪንግዶም ፓውንድ ስምምነት አድርጋለች። ይህን ስምምነት 100000 የስራ ዕድሎችን በኢትዮጵያ ለመፍጠር የሚያስችል ሆኖ ከዚሁ 30 በመቶ የሚሆነውን ደግሞ ለስድተኞች የሚሰጥ ድርሻ የተመደበ በጀት ነው።
TMP – 24/05/2019
ፎቶ ክረዲት: ኒውይስዋል / ሽተር ስቶክ .ኮም
በኢትዮጵያ የሚገኙ ኤርትራውያን ስደተኞች በብዛት የትምህርት እድል እያገኙ ናቸው።
ፅሑፉን ያካፍሉ