“በጥሩ ሁኔታ ላይ ነን”: ኤርትራውያን ስደተኞች በኢትዮጵያ ትምህርት ቤቶች እና ዩኒቨርስቲዎች ገብተው የመማር ዕድል አላቸው።

ኤርትራውያን ስደተኞች በአሁን ሰዓት በተለያዩ የኢትዮጵያ ትምህርት ቤቶች እና ዩኒቨርስቲዎች ገብተው የመማር ዕድል እያገኙ ነው። ይህ እንደ አንድ በኢትዮጵያ እየተከናወነ ያለ በስደተኞች ማቋቆምያ ፒሊሲ እና ህግ ማሻሸያ   ተደርጎ የሚወሰድ ሲሆን በኢትዮጵያ የሚገኙ በሺዎች የሚቆጠሩ ኤርትራውያን ህፃናት እና ወጣቶች ያቋረጡትን ትምህርት እንዲቀጥሉ የምያስችል ነው።  

ጃንዋሪ 17 ቀን 2019 የኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ኤርትራውያን ስደተኞች የትምህርት ዕድል፣ የመኖር፣ የመስራት እና ከካምፖች ውጭ የመንቀሳቀስ መብቶችን ጨምሮ አዲስ አሰራር ማፅደቁ ይታወሳል።

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ኤጀንሲ (ዩኤንኤችሲአር) የኢትዮጵያ ተወካይ ክሌሜንቲኔ አው ናክዋታ ሳላሚ ይሄንን ውሳኔ ያማኳሹት ሲሆንኢትዮጰያ ለአፍሪካውያን ሀገራት ብቻ ሳይሆን ለመላው አለም በምሳሌነት የሚጠቀስ ውሳኔ አስተላልፋለች።ብለዋል።

እንደ ኤጀንሲው ሪፖርት ከሆነ 2017 እና 2018 ብቻ 10 ዕድሜአቸው ለትምህርት የደረሰ ስደተኛ ህፃናት 7 የትምህርት ዕድል አግኘተዋል። በሀገሪቱ ከተከፈቱት ተመሳሳይ አገልግሎት የሚሰጡ ትምህርት ቤቶች አንዱ ማይዓይኒ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ነው።

ዩኤንኤችሲአር ማይክ ለተባለ አንድ ኤርትራዊ ተማሪ ያለውን ተመኩሮ ጠይቆት እንደዘገበው ማይክእንጫወታለን። ጎን ለጎን ተቀምጠን እንማራለን። የክፍል ጓደኞቼ ስደተኞችም አሉ። ስደተኛ ያልሆኑም አሉ። ይህ ግድ አይሰጠንም። በሰላም ነው የምንኖረው።ብለዋል።

ማይክ ጨምሮየትምህርት ዕድል በማግኘቴ በጣም ደስተኛ ነኝ። ምክንያቱም ህልሜን ጋሃድ ለማድረግ ይረዳኛልብለዋል።

የማይ ዓይኒ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 235 ስደተኞችን በነፃ እያስተማረ ያለ ትምህር ቤት ሲሆን 383   የአከባቢው ህፃናት እና ወጣቶች ይማሩበታል። ተማሪዎቹ ነፃ የትምህርት መሳሪያዎች፣ መፅሐፍት እና ስቴሽነሪዎች እንደሚሰጣቸው ለማወቅ ተችለዋል። 

በዕድሜ የላቁ ስደተኞችን ከኢትዮጵያ የትምህርት ስርዓት ተጠቃሚዎች ናቸው። ለድጋፍ ሰጪ ድርጅቶች ምስጋና ይሁንና በስኮላርሽፕ ፕሮግራሞች ድጋፍ  2017 እስከ 2019 ባለው ጊዜ ውስጥ 3,100 በላይ ስደተኞች ኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኙ የተላለዩ ዩኒቨርስቲዎች የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸው እየተከታተሉ መሆናቸው  ታውቀዋል።

ነክዋታ ሳላሚ በበኩላቸው በኢትዮጵያ 900,000 በላይ ስደተኞች የትምህርት ዕድል እንድያገኙ ለማስቻል ተጨማሪ ድጋፍ  እየጠየቁ ነው።

እሳቸው: “የተቀናጀ የስደተኞችን የማቋቋም ስራ ስኬታማ ለማድረግ ከግል ሴክተሩ እንዲሁም ከልማት አጋሮች ተጨማሪ ድጋፍ ያስፈልጋል። ይህ ድጋፍ በስራ ዕድል ፈጠራ ዙርያ ስደተኞቹ እና ያሉበትን አከባቢ ለመጥቀም የምያስችል ነው።ብለዋል። 

TMP – 19/04/2019

ፎቶ ክሬዲት: አንድረዚጅ ኩቢክ/ ሻተርስቶክ

የፎቶ መግለጫ: ወጣት ተማሪ የትምህርት ክፍል ውስጥ፤ አክሱም፡ ሰሜናዊ ኢትዮጵያ። ማርች 22 ቀን 2019.