ስፐይን በስደተኛ ሞት ምክንያት ህገወጥ የሰው ልጅ አዘዋዋሪን በቁጥጥር ሰር አዋለች

ከሞሮኮ በመነሳት ወደ ስፐይን እያመራ በነበረው ጀልባ አንድ ስደተኛ በሞሞቱ ምክንያት ህገ ወጥ የሰው ልጅ አዘዋዋሪ በስፐይን ባለስልጣኖች ቁጥጥር ስር መዋሉን ኤልሙነዶ የተባለ የስፐይን ጋዜጣ ሐምሌ 16 ባወጣው ዘገባ አስታውቀዋል፡፡

የጊኒያን ዜግነት ያለው ህገወጥ የሰው ልጅ አዘዋዋሪ በተሰረቀ መጠጥ ምክንያት በተፈጠረው ጠብ ሆን ብሎ ሰደተኛን በማረዱ ምክንያት ክስ ቀርቦለታል፡፡ የጠቡም መነሻ ስደተኛው  መጠጥ በመጨረሹ ምክንያት ከህገ ወጥ የሰው ልጅ አዘዋዋሪ ቦርሳ ውስጥ በመወሰድ መሆኑን ታውቀዋል፡፡ ህገ ወጥ የሰው ልጅ አዘዋዋሪ ሁኔታውን ካወቀ በሃላ ጀልባው ላይ ከነበሩት 17 ስደተኞች ፊት በስደተኛው ላይ ጥቃት ፈፅመዋል፡፡

ስደተኞቹ ከአልቦራን ባህር ወደ ስፐይን ለመድረስ አደገኛ ጉዞ እያደረጉ ነበር፡፡ እያንዳንዱ ስደተኛ ለጉዞው 2500 ዩሮ መክፈሉን አልሙንዶ የተባለ የስፐይን ጋዜጣ አስታውቀዋል፡፡

ጀልባው በሐምሌ 5 በስደተኛ አድን መርከብ የታየ ሲሆን ሌሎች የተቀሩት 17 ስደተኞች ምንም ጉዳት ሳይደርስባቸው ለመዳን ችለዋል፡፡

ከአደጋው ከዳኑ ስደተኞች መካካል አንዱ “ አንገቱን ቆርጠው ወደ እብድ ተቀይዋል፡፡ “  በማለት ስለሁኔታው ለቀይ መስቀል ፍቃደኞች ተናግረዋል፡፡ አደጋው የዳኑ ስደተኞች በስፔን የስደተኞች ኮሚሽን በኩል በማላጋ መጠልያ ተወስደው የስነልቦና እርዳታ እየተደረገላቸው ነው፡፡

ጥቃቱን የተመለከቱት አብዛኛዎቹ ስደተኞች በአስከፊ የአእምሮ መዛባት እንዲሁም ለከፍተኛ ጭንቀትና እንቅልፍ እጦት ተጋልጠዋል፡፡ በማላጋ መቀበያ ማእከል ያሉት  ፍቃደኞች ” ከድርጊቱ ሳምንት በሃላ ብዙዎቹ እስከ ሁን ድረስ ለመተኛት አይቻሉም፡፡ ብዙዎቹ የስነ ልቦና እገዛ ያስፈልጋቸዋል:: ”   ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ኦማር ናጂ የተባሉ የሞሮኮ ሰብአዊ መብቶች ማህበር ፕረዚዳንት “  የታሰሩት ህገወጥ የሰው ልጅ አዘዋዋሪዎች ሰዎችን አደገኛ ጉዞ ለማድረግ የሚያታሉሉበትን ዜዴ  በአውሮጳ የተሸለ ህይወት እንደሚያገኙ ተስፋ በመስጠት በተለይም ለአደጋው ተጋላጭ የሆኑትን በአፍሪከ ከሰሃራ በታች ያሉት ሴቶች መሆናቸውን ድርጅታቸው መገንዘቡን ተናግረዋል፡፡”  ለአደጋው የተጋለጡ ስደተኞች ወደ ሞሮኮ የተጋዙ ሲሆን በጀልባ ወደ ስፔን ለመሻገር እስከ 3000 ዩሮ ለመክፈል እንደተገደዱ ናጂ ተናግረዋል፡፡ “ እንዲቆም ምልክት ሰጠነው የሞሮኮ ፖሊሶች በቁጥጥር ስር አዋሉት፡፡ መልሰውም በነፃ እንዲለቀቅ አደረጉ” ሲሉ ናጂ ተናግረዋል፡፡

ስፐይን ህገወጥ ስደትን ለመግተትና የህገወጥ የሰው ልጅ አዘዋዋሪዎች መረብ ለመበጣጠስ ከሞሮኮ ጋር በመሆን በቅርበት እየሰራች ትገኛለች፡፡ በሞሮኮ የውስጥ ጉዳይ ሚኒስተር የስደትና የድንበር ቁጥጥር ዳይሬክተር የሆኑት ካሊድ ዜሮውሊ በመጀመርያዎቹ 5 ወራት 2019 እ.ኤ.አ የሞሮኮ የባህር ጠረፍ ጠባቂዎች 25, 000 የሚሆኑ ህገወጥ የባህር ላይ የስደት ጉዞዎች ማክሸፋቸውን ለሮይተር ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም የሞሮኮ ባለስልጣኖች 50 የሚሆኑ የህገወጥ የሰው ልጅ አዘዋዋሪዎች ቡዱን ማፈራረሳቸውን ተናገረዋል፡፡

TMP – 26/07/2019

ፎቶ ፡- ኖማድ /ሹተርሰቶክ. ኮም

በአረሜናዊው አስደንጋጭ ድርጊት አእምሮአቸው የተረበሹ ስደተኞች በሰፔን የስደተኞች ኮሙሸን(CEAR). እርዳታ ተደርጎላቸዋል፡፡