የሱዳን የፀጥታ ሀይሎች በደቡባዊ ዳርፉር ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ህገ ወጥ የሰው ልጅ ነጋዴዎች በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን ተሰማ

ማርች 2/2019 ላይ የሱዳን የፀጥታ አካላት ህገ ወጥ ስደተኞችን ወደ ሊብያ ለመውሰድ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ህገ ወጥ የሰው ልጅ ነጋዴዎች በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገለፀ።  

የደቡባዊ ሱዳን መስተዳድር ሉቴናል ኮሌነል ነአም ከዲር እንደገለፁት የፀጥታ ሀይሉ አምስት በህገ ወጥ የሰው ልጅ ንግድ ሰራ ውስጥ የተሰማሩ ወንበዴዎች ተይዘዋል።  እነዚህ ወንበዴዎች የተያዙት 39 ሱዳናውያን ስደተኞች ወደ ሊብያ እየወሰዱ በነበሩበት ወቅት ነው። እነዚህ ወንበዴዎች መጨረሻቸው ምን ሆነ የሚል እስካሁን የወጣ መረጃ የለም።   

ሱዳን ራፒድ ሳፖርት ፎርስ    (RSF) በመባል የሚታወቅ የመንግስቱ ከፍተኛ የመከላከያ ተቋም ህገ ወጥ ስደትን ለመከላከል ከሱዳን ወደ ሊብያ የሚጓዙ ስደተኞች እና ወንበዴዎች   በመያዝ ስደተኞቹ ሆነ ወንበዴዎቹ ወደ ነበሩበት እንዲመለሱ እያደረገ  መጥተዋል።  

ተቋሙ በወርሀ ሴፕተምበር 2018 በማልሀ ከተማ በኩል ወደ ሊብያ በመግባት ላይ የነበሩ 154 ስደተኞችን በቁጥጥር ስር አውለዋል።   አብዛኛዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉ ህገ ወጥ ስደተኞች ሱዳናውያን ሲሆኑ በ22 እና 26 የዕድመ ክልል ውስጥ የሚገኙ መሆናቸውን ተገልፀዋል።  የተቋሙ የጋይዳንስና ሰርቪስ ዳይሪክተር ለሱዳን ኒውስ ኤጀንሲ እንደገለፁት የቅድመ ኦፕሬሽን ጥናታቸው እንድምያሳየው እነዚህ ወጣት ተጓዦች “የግብረ ሽበራ ተቋማት አባላት እና አደገኛ ተጓዦች”  ናቸው። ይህ ቡድን ከካርቱም ከተማ በቅርብ ርቀት ወደሚገኘው  ኢልጃሊ የተባለ የጦር ካምፕ እንዲወሰድ ተደርጓል።    

ሱዳን ከ2016 ጀምራ ህገ ወጥ ስደት ለመከላከል  ስትሰራ ቆይታለች። ይህ ተነሳሽነት የመጣው 37 የአውሮፓ ህብረት አባል ሃገራት እንዲሁም የአፍሪካ ሀገራት በ2014 ባደረጉት ስምምነት መሆኑ ተገልፀዋል። ይህ ፖለቲካዊ ትብብር በአፍሪካ ቀንድ እየታየ ያለው የሰው ልጅ ንግድ መስፋፋትና ህገ ወጥ ስደትን እንዲቆም ለማገዝ ነው።    

ጁላይ 2018 የሱዳን ፀረ ህገ ወጥ የሰው ልጅ ንግድ ኮሚቴ ካርቱም ከተማ ላይ ተገናኝቶ በአውሮፓ ህብረት የሚታገዝ ሀገራዊ የውንብድና ወንጀል መከላከል የምያስችል ስትራተጂ እንዲወጣ ተደርጓል።  በዚሁ ኮንፈረንስ ኢትዮጵያ፣ ጅቡቲ፣ ሶማልያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ዩጋንዳና ኬንያ የኮንፈረንሱ ተካፋዮች ነበሩ።

ይህ የአሁኑ ኦፕሬሽን የተሰራው ከጥቂት ቀናት በፊት 1,500 ሱዳናውያን ስደተኞች በሊብያ ታጂራ ከተማ ውስጥ ታስረው በርሀብ እየተሰቃዩ መሆናቸውና ማመፃቸው ከተሰማ በኋላ ነው።  አመፁ የተነሳው ያለ ፍርድ በመታሰራቸውና እና ለረጅም ጊዜ በማቆያ መቀመጣቸው ተከትሎ ነው ተብለዋል።   ዳባንጋ የተባለ የሬድዮ ጣብያ እንደዘገበው  በአሁን ሰዓት 221,500 ሱዳናውያን በሊብያ ይገኛሉ።   

2018 ሱዳን በመቶዎች የሚቆጠሩ የወንበዴዎች ሲሳይ ሊሆኑ የነበሩ ስደተኞች ታድጋለች። ከእነዚህ ለህገወጥ የሰው ልጅ ነጋዴዎች ሊሸጡ ታስበው በቁጥጥር ስር ውለው የነበሩ ስደተኞች አብዛኛዎቹ ኤርትራውያን መሆናቸውን ተነግረዋል።  

TMP – 12/03/2019 

ፎቶ: ክሊድዮ ቪድሪ/ ሻተርስቶክ. በሱዳን ሱሃራ የምትገኝ ቀበሌ