የፈረንሳይ የባህር ላይ ጥበቃ ሀይሎች የእንግሊዝ ቻናል አልፈው ለመሄድ የሞከሩ ዘጠኝ ስደተኞችን በቁጥጥር ስር አውለዋል።

መይ እሁድ 19 ቀን 2019 ዘጠኝ ስደተኞች በመያዝ በእንግሊዝ ቻናል በኩል ወደ እንግሊዝ በመሄድ ላይ የነበረ ትንሽ ጀልባ በቁጥጥር ስር ውላለች። አንድ ህፃን የሚገኝባቸው እነዚህ ስምንት ሰዎች ራሳቸው ኢራናውያን እንደሆኑ የገለፁ ሲሆን ወደ ፈረንሳይ እንዲመለሱ ተደርጓል።

የፈረንሳዩ ፓትሮል ይሄንን ስደተኛ የያዘ ጀልባ በቁጥጥር ስር ያዋለው ከካሊስ ወደብ 25 ኪሎሜትር ርቀት ነው። ስደተኞቹ ተይዘው ወደቡ አከባቢ ወደሚገኙ ባለስልጣናት ተወስደዋል። ህፃኑ ስደተኛ በሚልድ ሃይፎቶርምያ በሽታ ተይዞ እየተሰቃዩ ነበርም ተብለዋል።

በአከባቢው የጥበቃ ፓትሮል የወጣ መግለጫ እንዳለውየቻናሉ አካላት እና ሰሜናዊ ባህር በጣም በተጨናነቀው እና ለሰው ህይወት አደጋ በምያስከትለው የእንግሊዝ ቻናል ስደተኞች እንዳያልፉ አስጠንቅቀው ነበር።

አደጋው እና ስጋቱ እንዳለ ሆኖ ኦክተበር 2018 ጀምሮ የእንግሊዝ ቻናልን አቋርጦ የሚሄድ የስደተኛ ቁጥር እየጨመረ መጥተዋል። ያሉት ችግሮች ከባድ የመርከብ ትራፊክ እና የውሃ ሙቀት ይገኙበታል። ስደተኞቸ በትላልቅ የጭነት መኪኖች ወደ እንግሊዝ ለመድረስ ቱንብ ቻነልን እንደሚጠቀሙም ተነግረዋል።

ወደ እንግሊዝ በህገ ወጥ መንገድ ለመሄድ አስበው የሚንቀሳቀሱ ሰዎች መጨረሻ ላይ ለህገ ወጥ ደላሎች የሚከፍሉት ገንዘብ  የትየሌለ ነው። በቅርቡ ከእንግሊዝ ብሄራዊ የወንጀል ኤጀንሲ የወጣ ዘገባ እንደምያሳየው በካሊስ እና በሌሎች ካምፖች የተደራጀ የወንጀል ስራ የሚሰሩ አካላት ተበራክተዋል። እነዚህ ቡድኖች በጭንቅ ውስጥ ካሉት ስደተኞች ገንዘብ የሚወስዱ ናቸው። እነዚህ የተቸገሩ ስደተኞች እንግሊዝ እናደርሳቹኋለን ለሚልዋቸው ህገ ወጥ ስደተኞች እስከ 13,000 የእንግሊዝ ፓውድን ይከፍላሉ።

ሪፖርቱ እንደሚያሳየው የወሰን ጥበቃ ሀይሎች ወደ እንግሊዝ ሊገቡ በሚንቀሳቀሱ ስደተኞች ላይ ከፍተኛ ቁጥጥር እያደረገ ነው። ይህእንግሊዝ፣ ፈረንሳይ እና ቤልጅየም   ስደተኞች መንገድ ላይ እያሉ  መያዝን የሚመለከት የገቡትን ቃል ኪዳን አንድ አካል ነው።ተብለዋል።

በዱብሊን ሬጉሌሽን መሰረት አንድ ስደተኛ አሳይለም መጠየቅ ያለበት ለመጀመርያ ጊዜ እግሩ በረገጠበት አውሮፓዊ ሀገር መሆኑ ይደነግጋል። ከጃንዋሪ ጀምሮ እንግሊዝ   30 በላይ ስደተኞች ወደ ፈረንሳይ   ወይም ወደ ሌላ የአውሮፓ ህብረት ሀገር መልሳለች።

እንግሊዝ በእንግሊዝ ቻናል ያለ የስደት ፍሰት ከፍተኛ ቁጥጥር እያደረገች መሆና የሚታወቅ ሆኖ ከዛም ባለፈ ህገ ወጥ የሰው ልጅ ደላሎች ላይ ከፍተኛ ቁጥጥር እያደረገች ትገኛለች። ከቅርብ ወራት ወዲህ ህገ ወጥ ስደት በመምራት ስራ ላይ በተሰማሩ ህገ ወጥ የሰው ልጅ ደላሎች ላይ የእስር ቅጣት እየተጣለባቸው መጥተዋል፤ እንደ የእንግሊዙ ብሄራዊ የወንጀል ኤጀንሲ።  

TMP – 03/06/2019

Photo credit: የፈረንሳይ የወደብ ጥበቃ (ጀንደርማሪ ማሪታይም)

Photo caption: የፈረንሳይ የወደብ ጥበቃ ሀይል ዘጠኝ ኢራናውያን ስደተኞች ባዳነበትበኬፕ ግሪስ  ኔዝ መይ 19 ቀን 2019.