በየመን የሚገኙ ያለረዳት መውጫ ያጡ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ወደ አገራቸው ለመመለስ ይፈልጋሉ
ከ60 በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ሰደተኞች 37 ሴቶችን ጨምሮ በጦርነት በታመሰችው የመን ውስጥ መውጫ ያጡና ታስረው የሚገኙት በአገሪቱ ባለው አስጊ/አሳሳቢ ሁኔታ ምክንያት ወደ አገራቸው ለመመለስ እንደሚፈልጉ የአከባቢ ሚድያ ዘግቧል።
ስደተኖቹ ወደ ሳውዲ ዓረብያ ለመደረስ ባደረጉት ያልተሳካ ሙከራ በተይዝ ደቡባዊ ክፍለ ሃገር እስር ቤት ውስጥ ተይዘው ይገኛሉ።
ዐብዲ ያሲን እድሪስ የተባለው ኢትዮጵያዊ ስደተኛ ከመጋቢት 2019 እ.ኤ.አ ጀምሮ በእስር ቤት ውስጥ ተይዘው እንደሚገኙ ተናግሯል። ወደ ሳውዲ ዓረብያ ከመድረሳቸው በፊት በባለስልጣኖች ተይዘዋል። እድሪስ እርሱና ሌሎች ስደተኞች ድህንነታቸው ተጠብቆ ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ እገዛ እንደሚያስፈልጋቸው ተናግሯል።
በየመን ስደተኞች እስር ቤቶች ውስጥ የሚገኘው ሁኔታ ሊቢያ ካለው ጋር ተመሳሳይ ነው። አካላዊና ወሲባዊ ጥቃት የተለመደ ክስተት መሆኑን ስደተኞቹ ተናግረዋል። ብዙ ስደተኞች አስገድዶ የመድፈር ወንጀሎች አካላዊና ስነ ልቦናዊ ጥቃት ሲፈፀም ማየታቸውና እንዲሁም ሌሎች መደብደባቸውና ምግብ እንዳያገኙ መከልከላቸውን ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ መንግስት ከአለም አቀፍ የስደተኞች ጉዳይ ድርጅት (IOM) ባገኘው እገዛና ከየመን ባለስልጣኖች ጋር በመተባበር በመቶ የሚቆጠሩ በየመን ይገኙ የነበሩትን ኢትዮጵያውያን ዋስትናው በተጠበቁ መንገድ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ሁኔታዎችን አመቻችቷል። ከህዳር 2018 እስከ ጥር 2019 እ.ኤ.አ ባለው ጊዜ ከ 700 በላይ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ወደ አገራቸው ተመልሰዋል። አለም አቀፍ የስደተኞች ጉዳይ ድርጅት (IOM) በ2019 እ.ኤ.አ መጨረሻ ላይ በፈቃዳቸው ወደ አገራቸው ለሚመለሱ 3000 ኢትዮጵያውን ስደተኞች ድጋፍ/እርዳታ ለማድረግ ማቀዱን አስታውቋል።
ምንም እንኳን በየመን ያለው ግጭት እየቀጠለ ቢሆንም ለአፍሪካ ቀንድ ባላት ቅርበትን ወደ አውሮጳ ለመድረስ መንገድ በመሆኗ ብዙ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ስደተኞች የመን ለመድረስ ሙከራ እያደረጉ ናቸው። ከዚህ ስደተኞች ወደ ሳውዲ ዓረቢያና ሌሎች የባህር ሰላጤ አገሮች ለመድረስ ወይም ወደ ሱዳን በመመለስ ወደ አውሮጳ ለመግባት ይቀጥላሉ። ሕገወጥ የሰው ልጅ አዘዋዋሪዎች ገንዘብ የምትከፍሉት ወደ ፈለጋችሁበት ቦታ ከደረሳችሁ በኃላ ነው የሚል የማተለያ ውል በማድረግ ስደተኞች ለአደጋ እንዲጋለጡ ያደርጋሉ። ምንም እንኳን አስከፊ አደጋዎች የሚከሰቱ ቢሆኑም 150 ሺ የሚሆኑ ስደተኞች ከዚህ 92% አብዛኛዎቹ ከኢትዮጵያና ጥቂት ቁጥር ያላቸው ኤርትራውያን በ2018 እ.ኤ.አ ብቻ ወደ አገሪቱ መድረሳቸውን አለም አቀፍ ስደተኞች ጉዳይ ድርጅት (IOM) ያምናል።
ብዙ ስደተኞች የመን ለመድረስ ህይወታቸውን ለአደጋ ያጋልጣሉ በየካቲት 2018 እ.ኤ.አ ሁለት ከአቅም በላይ የተጨናነቁ የስደተኞች ጀልባዎች ወደ የመን በማምራት ላይ እያሉ በጅቡቲ የባህር ጠረፍ በመስጠማቸው ቢያንስ 58 ሰዎች መሞታቸውን አለም አቀፍ የስደተኞች ጉዳይ ድርጅት (IOM) ዘግቧል።
TMP – 20/04/2019
ፅሑፉን ያካፍሉ