ሊብያ ውስጥ ስደተኞች ለትርፍ ሲባል ታግቷል ከባህር ውስጥ ይልቅ በየብስ ጉዞ ህይወታቸው የሚያልፉ ስደተኞች ይበዛሉ። በሁለቱም አገሮች መካከል ያለው ድንበር የተዘጋ ቢሆንም ኤርትራውያን አሁንም ወደ ኢትዮጵያ መሸሻቸውን አላቋረጡም ጣልያን ፤- በባህር ላይ ተገኝተው ወደ ሊብያ እንዲመለሱ በሚገደዱ ስደተኞች ላይ ከሊብያ ጋር የነበራት ስምምነት አድሳለች ኢትዮጵያ ፤ ለስደተኞችና ለዜጋዋ እኩል እድል የተረጋገጠባት አገር

ጦርነት ባደቀቃት የመን ውስጥ ስደተኞች በአስጊ ሁኔታ ላይ ናቸው

የመን የሰብአዊ ቀውስ በበረ ታባትና ጦርነት ያደቀቃት ብትሆንም ወደ የመን የሚገቡት ስደተኞች ቁጥር በጣም ማሻቀቡ ተገለፀ። የአለም የስደተኞች ድርጅት (አይ..ኤም) እንደገመተው ከሆነ በዚህ ዓመት 2018 / መጨረሻ ወደ 150,000 (አንድ መቶ ሓምሳ ) ስደተኞች የመን ይገባሉ የሚል ግምት እንዳለና ይህም ካለፈው ዓመት ሲነፃፀር ወደ 50% እንደሚሆን ነው።

የአብዛኛዎቹ ስደተኞች በየመን በኩል ተጉዘው ወደ ገልፍ ስቴትስ (የገልፍ ሃገሮች በመግባት) የተሻለ  የስራ እድል ለማግኘት እንደሆነ ነው። ነገር ግን በየመን የሚካሄደው የርስ በርስ ጦርነት እቅዳቸው እንዳጨናገፉባቸውና ለብዝበዛና ለእንግልት ተጋላጭ እንዳደረጓቸው ይገልፃሉ።

መሓመድ አብዲከር የአለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት የኦፕሬሽንና ድንገተኛ ደራሽ ስራዎች ሃላፊ ጦርነት በበዛበት የመን ስደተኞች ክፉኛ የመታገት ሁኔታ እያጋጠማቸው መሆኑ ገልፀዋል። እነዚህ ስደተኞች የሚመኙት (የሚያልሙት) ጥሩ የኑሮ ሁኔታ ለራሳቸውና ለቤተሰቦቻቸው ጭምር ስራ ይፈልጋሉ ደህንነትና አዲስ እድል ነው። በተቃራው ግን በመንገዳቸው ስቃይ ሰቆቃና እንግልት እንዲሁም ህገወጥ የሰዎች ዝውውር ነው። አብዛኛዎቹ የመን የሚገቡት ስደተኞች የሚያጋጥማቸው እገታ ስቃይና እንግልት እንዲሁም አደጋ ነው። የአለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት አይ..ኤም እንደሚያመለክተው ከሆነ የመን ከሚገቡት 5 ስደተኞች አንዱ ህፃን ከእድሜ በታች ሲሆን አብዛኛዎቹም አሳዳጊ (ወላጅ) የሌላቸው መሆኑናቸው ነው።

ወደ ገልፍ (ባህረ ስላጤ) አገሮች የሚደረገው የስደት ጉዞ በአሁኑ ሰዓት የተጨናነቀ (ስራ የበዛባት የጉዞ መስመር) መሆኑና በተለይም ከሜዲተራንያን ይልቅ ስራ የበዛበትና የተጨናነቀ ነው። ምንም እንኳን ስደተኞች ወደ ባህር ሰላጤ ለመሄድ የመን ለመድረስ ቢቀናቸውም የሚያጋጥማቸው ግን አደጋና ስቃይ መሆኑ ታውቋል። የርስ በርስ ጦርነት ከተቀሰቀሰ 2014 / .. ጀምሮ ሃገሪቱ በተፋላሚ ቡዱኖች ምክንያት የሃገሪትዋ ዜጎች ለረሃብ ተጋልጠዋል።  

2018 / ወደ የመን ከተሰደዱት መካከል 92% የሚሆኑት ከኢትዮጵያ ሲሆን በህገወጥ ደላሎች እንደተታለሉ የአለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት ቃል አቀባይ ጆልሚልማን ገልፀዋል። ደላሎች ለስደተኞች የሚያታልሉበት መንገድም የየመን ባለስልጣናት በጦርነት ላይ በስራ ስለተጠመዱ የድንበር ቁጥጥሩ እስከዚህም ነው ስለዚህ በቀላሉ ትገባላችሁ በማለት ያታልሏቸዋል። ነገር ግን ለስደተኞች የሚያጋጥማቸው ያልጠበቁት ነገር ነው ሲሉ ሚልማን ይገልፃሉ። የፈንጅ ወረዳዎች ማለፍ የግድ ነው የተኩስ ለውውጥም እንደዚሁ አለ።

2017 / ወደ 3000 (ሶስት ) ገደማ ስደተኞች ታግተው ከአለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት ወደ ሃገራቸው ለመመለስ ትብብር እንደተደረገላቸው ነው።

TMP – 20/12/2018

ፎቶ፦ኣሌክሳንድራ ፋዚና/ .ኤን.ኤች..ር።  ስደተኞች ከሶማልያ ወደ የመን የሚጓጓዛቸውን ጀልባ በመጠባበቅ ላይ ላሉ የሚያሳይ ምስል ነው።