አንድ የድህንነት ጀልባ ባህር ላይ ወድቀው የነበሩ ስደተኞችን ካነሳ በኋላ እዛው እንዲቆይ ተደርገዋል
ጣልያን እና ማልታ: የጀርመን የባህር ድህንነት ጀልባ ወደ ወደባቸው እንዳይመጣ ከልክለዋል። ጀልባው ከሊብያ ተነስተው አውሮፓ ለመድረስ አስበው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ እና በምዕራባዊ የሊብያ ክፍል ወድቀው የተገኙ 64 ስደተኞችን ይዛ ነበር የሄደችው።
የሊብያ ባለስልጣናት አደጋው ካጋጠመ በኋላ ተደውሎላቸው መልስ ባለመስጠታቸው ምክንያት አላን ኩርዲ የተባለውን የባህር የደህንነት አካል አይተዋቸዋል። እነዚህ 10 ሴቶች፣ አምስት ህፃናት እና አንድ ጨቅላ ህፃን የሚገኙባቸው 64 ስደተኞች የሊብያ የባህር ግዛት በሆነችው ዝዋራ በምትባል ከትሪፖሊ በስተ ምዕራብ በሚገኘው አከባቢ አድኖዋቸዋል።
የ “ሲ አይ” የተባለ ተቋም ቃል አቀባይ ካርሎቴ ዊብል “ቱንዝያ እና ሊብያ በፍፁም መልስ ሊሰጡ አልቻሉም። ጣልያን እና ማልታ ደግሞ የእነሱ ሀላፊነት እንዳልሆነ እና ወደ እነሱ የውሃ ግዛት መግባት እንደማንችል ነግረውናል።” ብለዋል። አላን ኩርዲ የተባለ ስም የተሰጠው ይህ ተቋም የሁለት አመት ዕድሜው ሲርያዊ ህፃን በ2015 ሜዲትራንያን ባህር መሞቱን ተከትሎ ነው።
እሮብ ቀን የሊብያ የባህር ጠረፍ ጥበቃ ቃል አቀባይ የሆኑት ጀነራል አዩብ ቃሴም በበጎ ተግባር የተሰማሩ ተቋማት የሊብያ የውሃ አካል መንካት እንደሌለባቸው አስጠንቅቀዋል። “እኛ ክብር የምያስፈልገን መንግስታዊ ተቋም ነን። የሀገራችን ሉአላዊነት እየተደፈረ ባለበት ወቅት የአለም አቀፍ ህግ በሚለው መንገድ ህጋዊ እርምጃ ለመውሰድ እንገደዳለን።” ሲሉም አክለዋል። “እነዚህ በጎ አድራጊ ድርጅቶች ሉአላዊነታችን እየደፈሩ እንዲሁም ስማችን ጥላሸት እየቀቡ ናቸው ያሉት።” ብለዋል።
የጣልያኑ የሀገው ውስጥ ሚኒስተር ማቲው ሳሊቪኒ “ይህ በጀርመን ሀገር ውስጥ የተመዘገበ ተቋም–የጀርመን በጎ አድራጊ ተቋም–የጀርመን ጀልባ ባለቤት የሆነውና ከሀምቡርግ የመጣው ካፕቴን–የተሻለ የሚሆነው ወደመጣበት ወደ ሀምቡርግ መሄድን ነው።” ብለዋል። እሳቸው ጨምረው እንደገለፁት ራሳቸው የፃፉት “ወደ ጣልያኑ የባህር ግዛት ውስጥ እንዳትገባ!” የሚል መልእክት ልከውለት ነበር።
ይሁንና ”ሲ አይ” እንደሚለው ከሆነ ወደ ጀርመን የሚወስደውን መንገድ እስከ አራት ሳምንታት ሊፈጅ ይችላል። ይህ ደግሞ ለሁሉም የሚበቃ በቂ ምግብና ውሃ በሌለበት ሁኔታ አስቸጋሪ ሆነዋል።
የፈረንሳይ የሀገው ውስጥ ሚኒስትር ክሪስቶፌ ካስታነር “ጀልባዋ የት ማረፍ አለባት በሚል ዙርያ አንዳንድ አለመስማማቶች” እንደነበሩ ግልፅ አድርጓል። ይሁን እንጂ ተቋሙ ፈረንሳይ ስደተኞች በመቀበል ዙርያ ያለባት ቅድመ ዝጉጀነት እና የእርዳታ መንፈስ ከሌላው የከፋ ነው ብለው እንደማያምኑ ማረጋገጥ ይገባቸው እንደነበር አውስተዋል።
ሌሎች 91 ሰዎች የጫኑ ሁለት ጀልባዎችም አደጋ ገጥመዋቸው በተደጋጋሚ ደውለው የምያነሳ እንዳጡ ታውቀዋል። ይሁንና አሁን ጀልባዎቹ የት እንዳሉ የሚነግር “አዲስ ዜና የለም።” ብለዋል።
TMP – 11/04/2019
Photo: ሲ አይ / ትዊተር. ይህ የስድስት አመት ዕድሜው ልጅ ማኑኤል ይባላል። በ “ሲአይ” መርከቡ በአላን ኩርዲ በህይወት ከተረፉት 64 ስደተኞች አንዱ ነው። የዚህ ቨዝል ስም አላን ኩርዲ የተባለበት ምክንያት ስሙ አላን ኩርዲ የሆነውን ሶርያዊ የሁለት አመቱ ህፃን በ2015 በሜዲትራንያን ባህር ውስጥ መሞቱን ተከትሎ ነው።
ፅሑፉን ያካፍሉ