ጣልያን ስደተኞችን በማገድ ዙርያ ከሊብያ ጋር የነበራት ስምምነት አደሰች
ፎቶ: የጣልያኑ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢዘኖ ማቨሮ ሚላንሲ
ጣልያን እና ሊብያ የ 2008 friendship treaty በመባል የሚታወቀውን የጋራ ስምምነት ጁላይ 7 ላይ ማደሳቸው ታውቋል። ይህ ውል ስደተኞችን ወደ ሊብያ ጠረፍ ግዛቶች እንዲመለሱ የማድረግ ስምምነትም ይጨምራል።
የሊብያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሃመድ ሳይላ “የጣልያን እና ሊብያ የጓደኝነት ውል በመባል የሚታወቀውን የ2008 ስምምነት ልናድስ ነው።” ብለዋል። ይህ የተናገሩት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከጣልያኑ አቻቸው ትሪፖሊ ከተማ ላይ ባደረጉት የጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ነው።
“ዛሬ የጣልያኑ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ትሪፖሊን መጎብኘታቸው የሁለቱም ሀገራት ግኑኝነት የሚያጠናክር ነው” ብለዋል ሳይላ በበኩላቸው።
በተጨማሪም ሳይላ “የጣልያኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከሊብያ ጠቅላይ ሚኒስትር ፋይዝ ሳራጅ በጋራ ጥቅሞች ላይ በተለይም በሊብያ ደህንነት እና መረጋጋት ዙርያ ውይይት አድርገዋል” ብለዋል።
የጣልያኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሚላንሲ እንደገለፁት ስምምነቱ አንድ ወር የፈጀ ምክክር የተደረገበት ሲሆን “አስፈላጊ እና ተስፋ ሰጪ” ብለውታል። አክለውም “ይህ ጉብኝት በቀጣይነት ከሊብያ መንግስት ጋር ለሚደረገው ተከታታይ የትብብር ስራ እንደ መነሻ ይወሰዳል።” ብለዋል።
ሁለቱም ዲፕሎማቶች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ ሚላንሲ የምክክሩ አስፈላጊነት ሲናገሩ “የሊብያ ሰላም እና መረጋጋት አስፈላጊነት ለሪጅኑ እና ለሜዲትራንያን ከፍተኛ ስለሆነ የእኛም ሆነ የአውሮፓ ህብረት ቀልብ ይስባል።” ብለዋል።
የሊብያው ፕዚደንት መአሙር ጋዳሪ ከስልጣን ከመወገዳቸው ጋር በተያያዘ ፌቡራሪ 2011 ላይ ሊታደስ የነበረውን ስምምነት የተፈረመው በ2008 ነው። በጊዜው፤ ሊብያ ግዛትዋ እያቋረጡ ወደ አውሮፓ የሚገቡትን የስደተኞች ቁጥር እና ጣልያን ሲደርስባት የነበረው ጫና ከግምት ውስጥ በማስገባር 4.2 ቢልዮን ዩሮ ካሳ ለመስጠት ቃል ገብታ ነበር። ስምምነቱ ከጣልያን ለሚመለሱ ስደተኞችም ሊብያ ትቀበል ዘንድ የሚጠይቅ ነበር።
የስምምነቱ መሰረተ ሀሳብ የነበረው “ሁሉም ነገር እንዳለ ሆኖ ሁለቱም ሀገራት በሊብያ ድህንነት እና አንድነት ዙርያ እጅ ለእጅ ተያይዘው እንዲሰሩ የሚመክር ነበር” ብለዋል ሚላንሲ።
ሊብያ፤ “በስደተኞች አያያዝ ዙርያ ከጣልያን እና አውሮፓ ህብረት ሀላፊነት እና ግዴታ ትካፈላለች። ሲጀምርም በሊብያ፣ ጣልያን እንዲሁም አውሮፓ ህብረት የሚደረግ ትብብር የስደት ቀውስ በመቀነስ እና የሰው ልጅ ትራጀዲ በመከላከል ዙርያ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል።” ነው ያሉት ሚላንሲ።
የጣልያኑ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከሊብያ መንግስት ጋር ባደረጉት የስምምነት እደሳ የአውሮፓ ፓርላማ ፕረዚደንት አንቴንዮ ታጃኒ በህገ ወጥ የሰው ልጅ ንግድ ስራ የተሰማሩ አካላት “ብላክ ሊስት” ውስጥ እንዲገቡ እና ከአፍሪካ ወደ አውሮፓ የሚደረገውን ስደት እንዲቆም የምያስችል ስራ እንዲሰራ ጥሪ አቅርበዋል።
“በአፍሪካ እና አውሮፓ ፖሊስ እና የህግ አካላት በጋራ ለአንድ ዐላማ እንዲሰሩ ዋነኛዎቹ በህገ ወጥ የሰው ንግድ ስራ የተሰማሩ አካላት ብላክ ሊስት ውስጥ የማስገባት ስራ ማከናወን አለብን።” ብለዋል ታጂኒ ፤ ከሊብያው ጠቅላይ ሚኒስትር ተገናኝተው ከተመካከሩ በኋላ።
“በእነዚህ ወንጀለኛ ተቋማት ላይ እርምጃ ካልወሰድን ህገ ወጥ ስደትን የማስቆም ስራ ቀላል አይሆንም።” ሲሉም አክለው ተናግረዋል ታጂኒ።
TMP – 29/08/2018
ፅሑፉን ያካፍሉ