የጀርመን መንግስት አሳይለም ጠያቂዎች የመመለስን እና ክህሎት ያላቸው ስደተኞች የመቀበልን ሂደት ቀላል የሚያደርግ ህግ አፀደቀ።

የጀርመን መንግስት በሀገሪቱ ያለ የስደተኞች ሁኔታ በተሻለ መንገድ ለማስተዳደር የምያስችል አዲስ ህግ ማውጣቱ ተገለፀ።

ይህ አዲስ ህግ የአሳይለም ጥያቄአቸው ምላሽ ላላገኙ ስደተኞች ከባድ ቢሆንም ክህሎት ያላቸው ስደተኞች ግን ወደ ጀርመን እንዲገቡ እና በጀርመን የቅጥር ግዝያቸው እስክያልቅ ድረስ መስራት የሚችሉበት ዕድል የሚሰጥ ነው ተብለዋል።

ይህ አዲስ “”ጂርዶንቴሩክሄርገሰቲዝአልያምኦርደርሊ ሪተርን ለውበመባል የሚታወቅ አዲስ የስደተኞች ህግ ለፖሊስ እና በስደት ዙርያ ለሚሰሩ ባለስልጣናት ሰፋ ያለ ስልጣን እንዲያገኙ የምያግዝ ነው። እንዲሁም ወደ መጡበት መመለስ ያለባቸው ፈቃድ ያላገኙ ስደቶኞች በአግባቡ እና በተሳካ ሁኔታ ለመፈፀም የምያስችል ነው ተብለዋል። በፌቡራሪ 2019 መጨረሻ ወር አከባቢ 240,000 የአሳይለም ጥያቄ ተቀባይነት ያላገኙ ስደተኞች ወደ መጡበት የሚመሉሰበት ቀን በመጠባበቅ ላይ ነበሩ።

የሀገር ውስጥ ሚኒስትሩ ሆረስት ሴሆፈር እንዳሉት ተቀባይነት ያላገኙ ስደተኞች ወደመጡበት ለመመለስ አዲሱ ህግ አስፈላጊ ነው።   እሳቸውይህ አዲስ ህግ በእኛ የስደት ፖሊሲ ወሳኙ ነጥብ ነው።ብለዋል። ሚኒስትሩ አክለው እንዳሉትይህ አዲስ የስደት ህግ ሰብአዊነት እና ህግ የሚከበረብት አዲስ ማዕቀፍ ለመፍጠር የምያስችል ነው።

በአዲሱ ህግ መሰረት የአሳይለም ጥያቄአቸው ተቀባይነት ያላገኙ ስደተኞች በስደተኛ ማቆያ ማእከላት ሳይሆን በእስርቤቶች እንዲቆዩ የሚደነግግ ነው። በእርግጥ ሌላ ወንጀል ከሰሩ ስደተኞች በጋራ አይደለም የሚታሰሩት። ይሁንና ሰነዶቻቸው በስርዓት ለመያዝ እንዲቻል በእስር ይቆያሉ፤ በህጉ መሰረት። ባለ የቦታ ማነስ ምክንያት ከሚፈጠር መጨናነቅ ለመዳንም ነው በእስር የሚቆዩት።

ክህሎት ላላቸው ስደተኞች ግን በጀርመን ያለ የስራ ዕድል ተጠቃሚ የሚሆኑበት ዕድል የምያሰፋ ህግ ነው። በጀርመን ያለ የስራ ዕድል ሲጠቀሙ ከማነኛውም የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገር ዜግነት ማግኘት አለማግኘታቸው ትልቅ ጉዳይ አይሆንም። ስለሆነም ክህሎት ያላቸው እና ጀርመን የምትፈልገው ሙያ ያላቸው ስደተኞች በሀገሪቱ ለስራ ፍለጋ ስድስት ወር ይፈቀድላቸዋል። ይህ የሚፈቀድላቸው ግን ስራ እስክያገኙ ድረስ በፋይናንስ ራሳቸው የሚችሉ ከሆነ ብቻ ነው። ይህ በእንዲህ እንዳለ ጀርመነኛ ቋንቋ የሚናገር፣ የወንጀል ሪኮርድ የሌለው፣ የተወሰነ ክህሎት ያለው ወይም ለመማር ፈቃደኛ የሆነ በጀርመን የመቆየት ዕድል ሰፋ ይላል።

TMP – 14/06/2019

Photo credit: ጀሱስ ፈርናንዴዝ   / ሻተርስቶክ

ኑንቲንግ፤ ጀርመን: ስደተኞች በስትሮቤሪ ማሳ ላይ የወቅቱ ስራ ሲሰሩ