ስደተኞችን ያልተገባ ክፍያ እንዲከፍሉ አፍኖ ለመውሰድ የሞከረ የወንበዴች ቡድን በስፔን ፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋለ፡፡

የስፔን የፀጥታ ሀይል በግንቦት 17 ስደተኞችን አፍኖ በመውሰድ ያልተገባ ክፍያ በማስከፈል የተጠረጠረ የወንበዴዎች ቡድን ቁጥጥር ስር እንዳዋለ ገለፀ፡፡ ስደተኞቹ ከሞሮኮ የሄዱ መሆናቸውን ታውቀዋል፡፡

እንደ የስፔኑ ፖሊስ ገለፃ እነዚህ ወንጀለኞች አራት የሞሮኮ ዜግነት ያላቸው ወንበዴዎች እና አንድ ስፔናዊ እንስት የምትገኝበት ቡድን ሲሆን ማንን እንዴት አፍነው መውሰድ እንዳለባቸው ከለዩ በሁዋላ በካምፖ ዲ ጊብራተላር መርከብ ሲጠብቁ ነው የተያዙት፡፡

ቡድኑ አዲሶቹ ስድተኞች ስፔን ሀገር ላይ ከቤተሰቦቻቸው ሊያገናኝዋቸው እንደሚችሉ በመንገር አታልለው በመውሰድ የሊባጃድላ ጎረቤት ወደሆነችው መንደር በመውሰድ አንድ ቤት ውስጥ ዘግተውባቸዉ ነበር፡፡

በተጨማሪም የኣከባቢው ፖሊስ እንደገለፀው አፋኝ ቡድኑ የስደተኞችን ተንቀሳቃሽ ስልኮች በመውሰድ ወደ ቤተ ሰቦቻቸው እየደወሉ ገንዘብ እንዲልኩላቸው አድርገዋቸዋል፡፡ ይህ ገንዘብ የተፈገለገው በነፃ እንዲለቅዋቸው በማለት መሆኑም ፖሊሱ አብራተዋል፡፡

ስደተኞቹ በደረበሰባቸው አስገዳጅ ሁኔታ አፋኞቹን ወደ ቤተሰቦቻው በማገናኘት እንደ የቤተሰቡ የፋይናንስ ኣቅም ሁኔታ ከ5 መቶ እስከ 2 ሺ ዩሮ ገንዘብ እንዲልኩላቸው አድርገዋል፡፡

ይሄንን ሁኔታ ከአከባቢው የፀጥታ ሀይሎች በደረሰው መረጃ መሰረት ቀድሞ የተገነዘበ የስፔን ፖሊስ የምርመራ ስራው የጀመረው ባለፈው ዐመት 2017 ላይ ነው፡፡

በመሆኑም ሶስቱ ወንዶች እና አንድ ሴት ከመሮኮ እንዲሁም አንድ ሴት ከስፔን የምትገኝበት ቡድን በስፔን ሀገር ህጋዊ የመኖርያ ፈቃድ ያላቸው ሲሆኑ በሰሩት ወንጀል በቁጥጥር ስር ለመዋል ችለዋል፡፡

ቡድኑ የስራ ክፍፍል የነበረው ሲሆን ወንዶቹ ስደተኞችን በተለያዩ የማታለል ሴራዎች አፍነው ቀድሞ ወደ ተዘጋጀው ቦታ መውሰድ ሴቶቹ ደግሞ ስደተኞቹን የሚፈለግባቸው የፋይናንስ ጥያቄዎች እንዲመልሱ ያደርጋሉ፡፡

እስካሁን ስንት ስደተኞች በተመሳሳይ የማፈን አደጋ ውስጥ እንደወደቁ ያልታወቀ ሲሆን ፖሊስ ግን ተመሳሳይ የፖሊስ ምርመራ እና ጥናት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡ በመሆኑም በተመሳሳይ የወንጀል ስራ የተሰማሩ ብዱኖች ሊያዙ እንደሚችሉ ተገምተዋል፡፡

TMP – 27/06/2018

የስፔን የባህር ጠረፍ መርከብ በአልገሲራስ ወደብ ኣከባቢ፤ ግንቦት 2/2017