በሊብያ የስደተኞች ማእከል በፖሊስ እና ስደተኞች መካከል ግጭት ተነሳ

ዘገባዎች እንደምያሳዩት በሊብያ ትሪፖሊ በሚገኘው ታረቅ አልማታር የተባለውን የስደተኞች ማእከል ኤርትራውያን እና ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ከፖሊስ ጋር ባነሱት ጠብ ረብሻ ተፈጥረዋል። የጠቡ መነሻ ወደ ሌላ ቦታ አንዘዋወርም በሚል ነው። እንደዚህ ያሉበት ምክንያትም ወደ ህገወጥ ደላሎች አሳልፈው ይሰጡናል በሚል ነው ተብለዋል።  

ኦገስት 5 ላይ ወደ ዘማይግራንት ፕሮጀክት የመጣ የድምፅ መልእክት “ለህገ ወጥ ደላሎች አሳልፈው ሊሰጡን ሰለሆነ ድረሱልን” የሚል ነው።   

ኢትዮጵያዊው ስደተኛ እንደገለፀው ከሶስት ወራት በፊት ግብፅ የሚገኘው የሀገሩ ኤምባሲ ጉዳዩን በተመለከተ ሙሉ መረጃና የድረሱልን መልእክት አስተላልፈዋል። ፎቶአቸው እና ስማቸው በዝርዝር የላኩት እነዚህ ስደተኞች በኋላ ላይ ጉዳዩ በሊብያ መንግስት ዘንድ እንዲታይ እና ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ  በማሰብ ኤምባሲው ወደ ሊብያ መንግስት መልእክት እንደላከ ተነግሮዋቸዋል። ይሁንና  ከሊብያ መንግስት ሆነ ከኤምባሲው ምንም ዐይነት ምላሽ ሳይሰጣቸው ሶስት ወር ማለፉ ተናግረዋል።  

ቢቢሲ ትግርኛ (BBC Tigrinya ) እንደገዘገበው በስደተኞች ማቆያ ማእከሉ  አንድ ኤርትራዊ ስደተኛ በዐመፅ ከመወሰድ እንደተረፈ በስልክ እንደተነገረው ገልፀዋል።   

ይህ ዮናስ የተባለው ኤርትራዊው ስደተኛ እንደሚለው ከሆነ 1500 የሚጠጉ ኤርትራውያን፣ ኢትዮጵያውያን፣ ሶማልያውያን እና ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት የመጡ ስደተኞች በጣም በተጨናነቀ እና ንፋስ ማስገብያ በሌለበት ህንፃ ውስጥ ታጉረው ነው ያሉት። በዛ ላይ በቂ ምግብ እና ውሃ የለም።  በጣም ብዙ ስደተኞች በመታፈናቸው እና በቲቢ በሽታ ወደ ሞት ተዳርገዋል።  

ባለፉት አስር ቀናት ብቻ ሶስት ሰዎች ሞተዋል።” ብለዋል ለቢቢሲ በሰጠው ቃለ መጠይቅ።  

የጣልያን ሀገር ድረ በሆነው አቨንሪ ( Avvenire) የተባለውን ድረ  ገፅ የወጣው መረጃ እንደምያሳየው ኦገስት 5 ላይ የተነሳው ግጭት ፖሊስ ወደ ሌላ የማቆያ ማእከል ነው የምንወስዳችሁ በማለት ስደተኞቹን ሊሸጥዋቸው አስበው በመንቀሳቀሳቸው ነው።   

በመሆኑም አንድ ሶማልያዊ እና 19 ኤርትራውያን በመወሰዳቸው ምክንያት በማእከሉ የሚገኙት ስደተኞች ሁለት ብርድ ልብሶች በእሳት አቃጥለዋል። ግጭቱ ለማረጋጋት ፖሊስ በተጠቀመው አስለቃሽ ጋዝ እና ዱላ ምክንያትም ሶስት ስደተኞች ላይ ጉዳት ደርሰዋል።    

አቫይነር በሌላ ዘገባው እንደገለፀው ሊብያ የተባበሩት መንግስታት ከፍተኛ ኮምሽን  (UNHCR) የስደተኞች ጉዳይ የማፋጠን ስራ በአግባቡ እና በተፈለገው ፍጥነት ባለማከናወንዋ እየተወቀሰች ነው። በተለይም ያልተመዘገቡ ስደተኞች ወደ ገበያ በማውረድ ረገድ ከፍተኛ ጥፋት እየፈፀመች መሆንዋንም አቫይነር ዘግበዋል።   

ከሊብያ የተገኙት የዜና ምንጮች እንደገለፁት ኦገስት 6 ላይ የአውሮፓ ህብረት ዲፕሎማት የሊብያ የስደተኞች ማቆያ ማእከላት እንዳይጎበኙ ተደርገዋል። እንደምክንያት የቀረበውም ሊብያ ስደተኞችን ለመቀለብ የምያስችል ድጋፍ በግዜው እያገኘች ስላልሆነች መሆኑን ተገልፀዋል፤ እንደ አቫየር ዘገባ።   

ኤርትራዊው ስደተኛ ዮናስ እንደሚለው ሀገሩ ኤርትራ ለቆ ወደ ኢትዮጵያ የገባው ከአራት አመታት በፊት ነው። ከዛም ወደ ሱዳን አምርተዋል። ከሱዳን ተነስቶ ሊብያ ለመድረስም 3500 ዶላር ከፍለዋል።  

ዮናስ እንደሚለው ሁለት ሳምንታት ከተጓዘ በኋላ ከሌሎች ስደተኞች ጋር በታጣቂ ሀይሎች ታግተዋል። 5 ሺ ዶላር ተጨማሪ ክፍያ ባለ መክፈሉ ምክንያትም ሶስት ጊዜ ተሽጠዋል።  ይሁንና ሌሎች ታጣቂዎች ሲያገኝዋቸው በተአምር አምልጠው እንደወጡ እና አሁን ወዳለበት የስደተኞች ማቆማ ማእከል እንደገቡ ይናገራል።  

ከዛ በኋላ ነበር ፖሊስ አስሮ አሁን ወዳለበት ታረቅ አልማታር የትሪፖሊው የስደተኞች ማእከል ያሰመጡት።   

በጣም ተስፋ ቆርጠናል። ብዙ ሰው ስለ ራስን ማጥፋት ነው የሚያወራው። ወደ ኤርትራ መመለስ አንፈልግም። አውሮፓ ደግሞ አትፈልገንም” ብለዋል አቫየር ያነጋገረው ሌላ ኤርትራዊ።  

TMP – 03/09/2018

ቪድዮ ካፕሽን: ይህ የቪድዮ ስእል የምያሳየው ኦገስት 5 ማታ ላይ በሊብያ በስደተኞች እና ፖሊስ መካከል የተፈጠረው ግጭት ሲሆን በሶሻል ሚድያ ሲንሸራሸር የነበረ ነው።    .  (https://web.facebook.com/abrham.fa/videos/1913840711993204/).

ስለ ስደት ማወቅ የምትፈልጉት ማነኛውም አይነት ጥያቄ በኢመይል አድራሻችን ልታገኙን ትችላላችሁ።

ጥያቄዎቻችሁ በኢመይል አድራሻችን ላኩልን። ባልደረቦቻችን በፍጥነት ይመልሱላቹኋል። ሁሉም የኢመይል መልእክት
ሚስጥራዊነቱ የተጠበቀ ነው።

ስደት አስበዋል? ለምክር አገልግሎት ይደውሉልን


ፈረንሳይ ውስጥ ከሆኑ

ዓለም እየተጓዘ ነው

ዓለማችን በጉዞ ላይ ነው ያለችው። በሚልዮን የሚቆጠሩ ሕዝብ የ21ኛው ክፍለ ዘመን የስደት መከራ እየደረሰባቸው ይገኛል።

የስደት መረጃ፣ ከምንጩ፡ ከመዳረሻና መሸጋገሪያ መንግስታት እስከ ሕገ ወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች፣ መገናኛ ብዙሀን፣ ምሁራን እና የስደተኞች የመረጃ ሰንሰለት በተለያዩ ለስደተኞች የማያግዙ ዓላማዋች የተሞላ ነዉ።

ተጨማሪ ያንብቡ