የአውሮፓ ህብረት አዲስ ፕሮግራም የስራ ዕድል ከፍ ለማድረግና ስደትን ለመግታት ለወጣት ስራ ፈጣሪዎች የገንዘብ እርዳታ እያደረገ ነው
የአውሮፓ ህብረት አዲስ ፕሮግራም ወደ ውጭ የሚደረገውን ስደት ለመግታት በአፍሪካ ወጣት ስራ ፈጣሪዎች ሴቶች ላይ ያተኮረ የገንዘብ እገዛ በማድረግ ላይ ይገኛል።
የአውሮፓ ህብረት አነስተኛ ብድሮችና ዋስትና ፕሮግራም የአደጋ ተካፋይነት አገልግሎት ድርጅት የውጭ ኢንቨስትመንት እቅድ (EIP) አካል ሆኖ ለአፍሪካ ወጣት ስራ ፈጣሪዎች ያላቸውን አነስተኛ ቢዝነስ ለማሳደግ እድል ይሰጣል። በዚህ ፐሮግራም በተሻለ መንገድ ለአነስተኛ ቢዝነሶች ለማገዝና የስራ እድል ለመፍጠር 4.2 ሚልዮን ዩሮ ለአፍሪካ ባንኮች መድቧል። በአፍሪካ ያሉት የአከባቢው ባንኮች ለአፍሪካ ወጣቶች ለተወሰነ ዓላማ የሚውለውን ብድርና ፋይናንሳዊ ውጤቶች ለዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ፣ ለአደጋ የተጋለጡና በግጭት የሚገኙ አገሮች ለማስተዳደር ያስችለዋል።
የአለም አቀፍ ልማት ትብብር ባለ ስልጣን /ኮሚሽነር ነቨንሚምካ ይህ ከ4 ሚልዮን ዩሮ በላይ የሚያወጣውን አዲስ ፕሮግራም ዝቅተኛ ገቢ ላለቸው አገሮች የሚገኙትን ለአዳዲስ የቢዝነስ /የስራ ፈጠራዎች ፋይናንሳዊ ምንጭ ለማግኘት የሚጥሩ ሴቶች ፣ወጣት ስራ ፈጣሪዎች ወይም ትናንሽ/ጥቃቅን ቢዝነሶች እውነተኛ ለውጥ እንዲያመጡ ያደርጋል። ለ50 ሺ አንስተኛ ቢዝነሶች እስከ 200 ሺ ስራዎችን ለመፍጠር ያስችላል ብለን እንጠብቃለን በማለት ተናግረዋል።
ለአፍሪካ ወጣቶች ኤርትራውያንን ጭምር አደገኛ ሕገወጥ ጉዞ በማድረግ ወደ አውሮፓ ለመሄድ የሚያስገድዷቸው ዋናው ምክንያት ስራ አጥነት ነው። የአለም ባንክ 60% የአፍሪካ ወጣቶች ስራ አጥ መሆናቸውን ዘግቧል።
አውሮፓ ወጣት አፍሪካውያን በአገራቸው ውስጥ ሆነው የሚፈልጉትን ሙያ በመስጠት ብቁ በማድረግ ወጣቶች እንዳይሰደዱ በማገዝ ላይ ትገኛለች። ለምሳሌ በነሓሴ 2018 እ.ኤ.አ የዩናይትድ ኪንግደም ለኢትዮጵያውያንና በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚገኙ ስደተኞች ለማገዝ 100 ሺ ስራዎችን ለመፍጠር የሚያስችል የ115 ሚልዮን ፓውንድ ለመስጠት የሚያስችል ስምምነት ተፈራርማለች። በነሓሴ 2018 እ.ኤ.አ ጣልያን ከሰሜን አሜሪካ አገሮች በኩል የሚደረገውን ስደት ለማስቆም 1 ቢልዮን ዩሮ መመደቧን አስታውቃለች። ሰሜን አሜሪካ ወደ አውሮፓ የሚያመሩት ህገወጥ ስደተኞች ዋናው የማሸጋገሪያ ቦታ ነው።
የአውሮፓ ህብረት በታህሳስ 2018 እ.ኤ.አ ለአደጋ ተጋላጭ ለሆኑት ስደተኞች ለመርዳት ፣ ህጋዊ/ሙያዊ የስራ ስደት ለማበረታትና ወደ አውሮፓ የሚደረገውን ህገወጥ ስደት ለመቀነስ የአውሮፓ ህብርት አስቸኳይ እርዳታ ለአፍሪካ (EU Emergency Trust Fund for Africa) ማቋቋሙን አስታውቋል። ከ2015 ጀምሮ የአውሮፓ ህብረት ፈንድ ከስደት ጋር በተያያዙትን የአፍሪካ ችገሮች ለመፍታት ለሚተገበሩ 23 እቅዶች/ፕሮግራሞች 582.2 ሚልዮን ዩሮ መድቧል።
TMP 25/04/2019
ፎቶ ክሪዲት፦ ዥን ወስትን/ሹተርስቶክ
በምዕራብ ኬንያ አርንጓዴ ሻይ ቅጠል በመስብሰብ ላይ ያለች/የምትገኝ ሴት
ፅሑፉን ያካፍሉ