ቱኒዝያ የሚገኘው የስደተኞች ማቆያ ማእከል ባለው አስከፊ ገፅታ ስደተኞች ራሳቸውን ለማጥፋት እየሞከሩ ነው።

የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳዮች ኤጀንሲ ዩኤንኤችሲአር ባቋቋማቸው የስደተኞች ማእከላት በቱንዝያ የሚገኙ በርከት ያለ ቁጥር ያላቸው ስደተኞች በማቆያ ማእከላቱ እያጋጠመ ባለ መጥፎ የኑሮ ሁኔታ ራሳቸውን ለማጥፋት እየሞከሩ መሆናቸው ተሰምተዋል።

ማርች 11 ቀን 2019 አንድ 16 ዕድሜ ኤርትራዊ ስደተኛ አሲድ በመጠጣቱ ምክንያት ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል። በማእከሉ አቅራብያ በሚገኘው ሆስፒታል ህክምናዊ ድጋፍ ካገኘ በኋላ ይረጋጋ ዘንድ የስነ ልቦና ምክር ወደምያገኝበት የህክምና ማእከልም ተወስደዋል። ሪፓብሊካ የተባለ የሚድያ አውታር እንደዘገበው ከሆነ ልጁጥሩ ስሜት እየተሰማኝ አይደለም። ወደዚህ ለምን እንዳመጡኝም አላቅም። የኔን ቋንቋ መናገርና መስማት የሚችል አንድም ሰው የለም። የመገለል ስሜትም እየተሰማኝ ነው።ብለዋል።

የተስፋ መቁረጥ ስሜትና ጫፍ የረገጠ ጭንቀት በአብዛኛው በስደተኞች ማእከላቱ የሚኖሩ ስደተኞች የሚስተዋል ችግር ነው። በቅርቡ ሌላ ኤርትራዊ ሴት ስደተኛ ከመጠን ያለፈ የማነቃቅያ መድሀኒት በመውሰድዋ ምክንያት ታማ በሀኪም ድጋፍ ድናለች።

መድኒን የተባለውን የቱኒዝያ የስደተኛ ማቆያ ማእከል በመቶዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች እና አሳይለም ጠያቂዎች ይኖሩበታል። አብዛኛዎቹ ከሊብያ ወጥተው ወደ ቱኒዝያ የገቡ ናቸው። እነዚህ ስደተኞች አቅም የሌላቸው፣ ህፃናትና ሴቶች፣ ቤተ ሰብ ሆነው የተሰደዱ ወዘተ ሲሆኑ አብዛኛዎቹ ኤርትራውያን ናቸው። ጥቂት የማይባሉም ከአፍሪካ ቀንድ ሀገራት በተለይም ከኢትዮጵያ እና ሱዳን የመጡ ይገኙበታል።

ጃንዋሪ 2019 የቱኒዝያ የኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ፍትህ ፎረም በቱኒዝያ እየታየ ያለ አስቸጋሪ የስደተኞች የኑሮ ሁኔታ በተመለከተ አንድ ዘገባ አውጥቶ ነበር። ትልቁም ትንሹም ፅዳቱ ባልጠበቀ እና በጋራ ነው፡ የገላ መታጠብያ እና ሽንት ቤት የሚጠቀሙት። ክረምት ሲሆን በቂ የብርድ ልብስ አይሰጣቸውም፤ ሲመጣም በግዜው ስለማይመጣ በአስፈላጊው ጊዜ ሳይጠቀሙበት ይቀራል።  በሞቃታ ግዜም ከፍተኛ የውሃ እጥረት ስላለ የችግሩ ሌላ ገፅታ ያጋጥማል። ስደተኞቹ በሳምንት 7 ዶላር በታች ስለሚሰጣቸው በዚህ ገንዘብ ምግብ ከመግዛት አልፈው ለሌላ አስፈላጊ ነገሮች የምያውሉት አቅም የላቸውም።

በዚሁ የስደተኞች ማእከል ያሉ ሴቶች ነፃነት አጥተው የሚኖሩ ሲሆን ከዛም ባለፈ በየሻወሩ ወሲባዊ ጥቃት እንደሚደርስባቸው ታውቀዋል። ብዙ የማእከሉ ስደተኞች የመገለል ስሜት እንዳላቸው እና ከቤተሰቦቻቸው የመገናኘት ዕድል እንደተነፈጉ ይናገራሉ።

ወደ ሊብያ የሚጓዙ ስደተኞች በስተመጨረሻ ራሳቸውን የምያገኙት በሊብያ የስደተኞች ማእከል ውስጥ ነው። በማእከሉ የቆየ አንድ ኤርትራዊ ስደተኛከአንድ አመት በላይ እዚሁ ሊብያ ውስጥ ቆይተናል። ሚስቴ በቶርቸር ምክንያት የአካል ጉዳት ደርሶባታል። ጓደኞቼ ራሴ ቀብሬአቸዋለሁ። ተሽጠናል። ተገፍተናል። ከዛ ሁሉ ሲኦል ወጥተን አሁን እዚህ ደረጃ ላይ ደርሰናል። አሁንም ግን ሀኪም ፍለጋ የሀው እየተማፀንን ነው። እስካሁን ግን ያየን አንድም አካል የለም።ብለዋል።

እነዚህ ስደተኞች ይህ አደገኛ የህይወት ሁኔታ እየተቃወሙ መጥተዋል። በቅርቡ ወደ 350 የሚጠጉ በዋናነት ከኤርትራ፣ ሱዳን እና ሶማልያ የሆኑት  ስደተኞች እና አሳይለም ጠያቂዎች የህክምና ድጋፍ እና በአጠቃላይ የተሻለ ህይወት እንፈልጋለን፤ እንደ ሰው ክብር ያስፈልገናል ብለው ከማእከሉ ውጪ ሰለማዊ ሰልፍ አድርገዋል። ይዘውት ከወጡ መፎክሮች አንዱከሊብያ ነው የመጣነው። እስር ይብቃ። ነፃ መውጣትን እንሻለን።ይላል።

 TMP – 9/04/2019

ፎቶ: ሳራ ክሬታ / ትዊተር. ስደተኞች እና ኣሰይለም ጠያቂዎች ዩኤንኤችሲአር ባቋቀመው መድኒን የስደተኞች ማእከል ውስጥ ድምፃቸው ሲያሰሙ