በሊብያ ታግተው ያሉ ስደተኞች በሀገሪቱ እየተካሄደ ባለው ጦርነት ምክንያት የምግብ ዋጋ ጭማሪ ገጥሞዋቸዋል።

በሊብያ ትሪፖሊ ከተማ በተላለዩ የስደተኛ ማቆያ ማእከላት ውስጥ እየኖሩ ያሉ ስደተኞች  በሀገሪቱ እየቀጠለ ባለ ግጭት ምክንያት ከፍተኛ የሆነ የምግብ የዋጋ ጭማሬ ተከስቶባቸዋል። እንደ አልጀዚራ ዘገባ ከሆነ ስደተኞቹ ይሄንን ችግር ተቋቁመው ለመኖር ከፍተኛ ትግል እያደረጉ ነው።

አቡ ሰሊም በሚባል የስደተኞች ማቆያ ማእከል ያሉ ስደተኞች እንደገለፁት ግጭቱ ከጀመረበት አፕሪል 4 ቀን 2019 ጀምሮ እስካሁን የምግብ ዋጋ በዕጥፍ መጨመሩ ይገልፃሉ። በአሁን ሰዓት ወደ 30 የሚጠጉ ህፃናት ጨምሮ 400 በላይ ሰዎች በደቡባዊ ትሪፖሊ ከተማ በሚገኝ የስደተኞች ማቆያ ማእከል ይኖራሉ።

የሊብያ መንግስት አግቶ የያዛቸው ስደተኞችን የምግብ አቅርቦት የሟሟላት ሀላፊነት ቢኖርበትም ላለፉት ስድስት ወራት ስደተኞቹ ራሳቸው ምግብ እየገዙ እየበሉ መሆናቸው ነው የተነገረው። የሚገዙበት ገንዘብ ደግሞ ወይም ይሰራሉ ወይም ደግሞ ከቤተሰቦቻቸው ይላክላቸዋል። ለምሳሌ ከኤርትራ፣ ከሰማልያ እና ሱዳን የሚላክላቸው አሉ።

ይህ በሊብያ እየተካሄደ ያለ የእርስበርስ ጦርነት ከቤተሰቦቻቸው ገንዘብ የምያገኙበት ዕድልም እያጠበበው መምጣቱ ይነገራል።በአሁን ጦርነቱ እየተጋጋለ እየመጣ ባለ ሰዓት ከቤተሰቦቻችን ገንዘብ የምናገኝበት መንገድ እየተዘጋ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው። ትራንስፖርቴሽን የሚባል ነገር የለም። በጦርነቱ ምክንያት ከውጭ ምግብ ገዝቶ መግባት የሚታሰብ አይደለም።ብለዋል በማእከላቱ የሚገኝ አንድ ታዳጊ። አክሎምከማነኛውም በጎ አድራጊ ድርጅት የሚገኝ ምንም አይነት ምግብ የለንም። እንደኔ ያሉ ደግሞ ገንዘብ የሚባል ነገር የላቸውምበጣም ከባድ ነው።ሲል ሀሳቡ ሰጥተዋል።

በአቡ ሳሊም የስደተኞች ማቆማ ማእከል ያለ የረሃብ መጠን ሁሉንም በእኩል እየገደላቸው ነው። በተለይም ደግሞ የቲቢ በሽተኞቹ ክፉኛ እየጎዳቸው ይገኛል።

ረሀብ ለምደነዋል […] ተቀብለነዋል።ያለው ደግሞ ኤርትራዊ ታዳጊ ስደተማ ነው። “[ስለምግብ እጥረት ሀሳብ ገብቶብን አያቅም] እየጨነቀን ያለው ስለህይወታችን ነው። ከዚህች አደገኛ ምድር እንዴት መውጣት እንደምንችል ነው እያሰብን ያለነው። ከዚህ አደገኛ ቦታ ወደ ተሻለ ቦታ በማዘዋወር ሂደት ላይ እባካችሁ የሚቻላችሁን ሁሉ አድርጉልን። 

እንደ የአልጀዚራ ዘገባ ከሆነ ወደ 3,000 በሊብያ ባለስልጣናት በተቋቋሙ የስደተኛ ማቆያ ማእከላት አሉ።   ዶክተርስ ዊዝ ኣውት ቦርደርስ የሚበላውን በጎ አድራጊ ተቋም በቃል አቀባዩ ሲራጅ ከኒዝ አማካኝነት ለአልጀዚራ እንዳለው ጦርነቱ ከተጀመረ ግዜ ወዲህ የምግብ ጉዳይ አሳሳቢ የስደተኞች ጥያቄ ሆነዋል።ስደተኞች ወደ ሊብያ እንዲመለሱ ያደረገ የተባበሩት መንግስታት አካል እነዚህ ስደተኞች በቂ እና ጥራቱ የጠበቀ የምግብ አቅርቦት እንድያሟላላቸው በተደጋጋሚ ጠይቀናል።ብለዋል።

የድጋፍ ኤጀንሲዎች በሊብያ በጦርነት መሀል እየተሰቃዩ ላለዩ ስደተኞች እርዳታ እንዲሰጡ ተጠይቀዋል።  እየሰሩም ነው። መይ 1 ቀን 2019 ላይ ዩኤንኤችሲአር እና የአለም አቀፉ የስደተኞች ተቋም፤ አይኦኤም በጋራ   325 ኤርትራውያን  ሱዳናውያን እና ናይጀርያውያን ስደተኞች ከቃሳር ቤን ጋሽር የተባለ ማእከል ወደ በምዕራባዊ የሊብያ ክፍል የሚገኘው አዛዋያ ማቆያ ማእከል እንዲዘዋወሩ አድርገዋል። ይህ የተደረገበት ምክንያትየስጋር መጠኑ የቀነሰ ነው።በሚል ነው።

TMP – 13/05/2019

Photo credit: ኮልድኖቭ / ሻተርስቶክ

Photo caption: በሽቦ የታጠረ የማቆያ ማእከል