10,000 ስደተኞች ከግሪክ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

ዐለም አቀፍ የስደተኞች ተቋም (IOM) እና የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኤጀንሲ በበጎ ፈቃዳቸው ወደየሀገራቸው ይመለሱ ዘንድ ድጋፍ በማድረግ በምንቀሳቀሳቸው ምክንያት ከ 10 ሺ በላይ ስደተኞች ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል። እነዚህ ከግሪክ የተመለሱ ስደተኞች በተጠቀሱት ዐለም አቀፍ ተቋማቱ ድጋፍ እና በአውሮፓ ህብረት እንዲሁም ግሪክ ላይ ማእከሉ ባደረገ የስደተኞች አስመላሽ ተቋም (AVRR) ነው።

በዚህ እንቅስቃሴ 10, 576 ስደተኞች በበጎ ፈቃዳቸው ከግሪክ ወደ 84 የተለያዩ ሀገራት ተመልሰዋል። ይህ የሆነው ከ ሰኔ 2016 እስካ ግንቦት 2018 ባለው ጊዜ ውስጥ ሲሆን ከእነዚህ ተመላሽ ስደተኞች 2500 ስደተኞች የፋይናንስ ድጋፍ ተደርጎላቸው ነው የተመለሱት።

የዐለም አቀፍ የስድተኞች ተቋም (IOM) ሰራተኞች የዚህ እንቅስቃሴ ተጠቃሚ የሆኑ ስደተኞችን በጥናት መልክ ለመያዝ ችለዋል። በመሆኑም እንደዚህ ዐይነት ፕሮግራም ያስፈልጋቸው እንደሆነ ብዙ ስደተኞች ተጠይቀዋል። ግሪክ ላይ ሊቆዩባቸው የሚችሉ ህጋዊ ማዕቀፎች፣ የፋይናንስ ድጎማ እና የህክምና ሁኔታን ጨምሮ በብዙ ጉዳዮች ላይም ተወያይተዋል።

ከስደተኞቹ ጋር የተደረገ ውይይት መሰረት በማድረግ በየሀገራቸው ያሉ ነባራዊ ሁኔታዎች ከግምት ውስጥ በማስገባት የማጣመር (reintegration) ስራ እንደሚሰራ እና ስደተኞች በየሀገራቸው ሂደው ሰርተው የሚኖሩበት ሁኔታ ማመቻቸት እንደሚገባም ተብራርተዋል።

ከ2,487 ስደተኞች 2, 261 የሚሆኑ በምክክሩ እና የማጣመር ፕሮግራሙ መሰረት ተስማምተው በየሀገራቸው ጥቃቅን እና አነስተኛ ቢዝነስ ማእከላት በመክፈት ለራሳቸው ጠቅመው ለህዝባቸው እና ሀገራቸው ሊተርፉ በሚችሉባቸው ነጥቦች ተስማምተዋል። በዚህ ፐሮግራም ከተጠቀሙ ከስደት ተመላሾች አንዱ ሞሮካዊው ፋዲል ነው። ፋዲል ማራከች በተባለች ከተማ ስጋ ቤት ከፍቶ ራሱን ችሎ በጥሩ ሁኔታ ላይ ይገኛል።

ፋዲል “የዐለም አቀፍ የስደተኞች ተቋም ሰራተኛ በቅርቡ ወደ ስራዬ መጥቶ የምሰራውን ጎብኝተዋል። የስራ ቦታዬ ንፁህ እና ማራኪ ሆኖ ነበር የቆየው። በዛም በጣም ኮርቻለሁ።” ብለዋል። ፋዲል እንዳለው “ከከተማው አስተዳደር የፅዳት ፈቃድም አግኝቻለሁ። በአከባቢው ሌላ ተመሳሳይ የንግድ ዐይነት ባለመኖሩ ቢዝነሴን በጣም በጥሩ ሁኔታ እየሄደ ነው።” ሲል ገልፀዋል።

ዐለም አቀፉ የስደተኞች ተቋም ለተመላሽ ስደተኞች ከ500 እስከ 1500 ዩሮ ይሰጣል። በዚህም በሀገር ቤት የራሳቸው ቢዝነስ በመክፍት አዲስ የህይወት ምዕራፍ እንዲጀምሩ ይመከራል።

ይህ በተመላሽ ስደተኞች ዙርያ የሚሰራ ግሪክ ማእከሉ ያደረገ ተቋም (AVRR) በዋናነት የሚሰራው ስራ ግሪክ ላይ መቆየት በማይችሉ ስደቶችን ዙርያ ነው። ተቋሙ ጥገኝነት ጠይቀው ያልተመለሰላቸው፣ ተቀባይነት ያላገኙ እንዲሁም ወደ ሀገራቸው መመለስ በሚፈልጉ ስደተኞች ላይ ያተኩራል።

ባጠቃላይ አውሮፓ ውስጥ ሊቆዩበት የሚያስችል ተስፋ የሌላቸው እንዲሁም የህግ ክፍተት ያሰጋቸው ማለትም ከቆዩ አደጋ ሊደርስባቸው የሚችሉ ስደተኞች ናቸው አሁን የዕደሉ ተጠቃሚ ሆነው ያሉት።

ግሪክ በ2016 “የቁጥጥር ፖሊሲ (containment policy) ያፀደቀች ስትሆን የፖሊሲው ዋና ዐላማ ስደተኞች የግሪክ ዋና መሬት ሳይረግጡ በአስቸጋሪ የሀገሪቱ ኣግናን የተባለ የባህር ጠረፍ እንድያልፉ የሚደነግግ ነው።

በዚህ ዐመት መጋቢት ወር የሰብአዊ መብት ተሟጓች (HRW) ያወጣው አንድ መረጃ እንደምያሳየው በሽዎች የሚቆጠሩ ጥገኝነት ጠያቂ ስደተኞች አስቸጋሪ መልክአ ምድር ባላቸው የግሪክ የባህር ጠረፍ ቦታዎች አሳር መካራቸው ስያዩ ከርመዋል።

ጥገኝነት ጠያቂ ስደተኞች በእነዚህ አስቸጋሪ ቦታዎች ላይ ተዘግዘተው የሚቆዩበት አሰራር በ2016 የአውሮፓ ህብረት የቱርኪ ስምምነት ውጤት መሆኑ ይታወቃል። በዚህ ስምምነተ መሰረት የጥቀኝነት ጥያቄአቸው መልስ እስከምያገኝ በእነዚህ ቦታዎች እንዲቆዩ የሚደነግግ ነው። በድንጋጌው መሰረት ሁሉም ወደ ግሪክ የሚሄዱ ስደተኞች በቱርክ እንድያልፉም ያዝዛል።

 

ከግሪክ የተመለሱ ስደተኞች በኮስኢስላንድ፤ መስከረም 28/2015

TMP – 12/06/2018