ካልተሳካ የስደት ሙከራ በኃላ አሁንም ቢሆን በሕገ ወጥ የሰው ልጅ አዘዋሪዎች ባለዕዳ ሆኖ የሚገኝ ስደተኛ

አሕመድ ጎራን የካርድሽ ስደተኛ ሲሆን የተሻለ ህይወት በጀርመን ለማግኘት ሲል የሚስቱንና ሁለት ልጆችን በኢራቅ ኩርዲስታን በመተው አሰቸጋሪ ውሳኔ ላይ ደርሰዋል። አሕመድ ስለ ውድ ገንዘብ የከፈለበትና ፍሬ ቢስ ሙከራ ለስደተኞች ፕሮጀክት ተናግረዋል።

”የነበረህን ፀጋ እስክታጣ ድረስ ያለህን ፀጋ በፍፁም አታውቀውም። ይህም ሰዎች እንድያውቁት እፈልጋለሁኝ” በማለት ስለኣጋጠመው መከራ ይናገራል። እዚህ ሁሉም ነገር ነበረኝ  ፍፁም ግን አልነበረም ሆኖም ግን ህይወት ነበረኝ ነገር እስከሚጠፋ ድረስ አላደነቅኩትም በማለት አሕመድ ይናገራል።

አሕመድ እንደ አብዛኞቹ ስደተኞች ጀርመን አገር ለመድረስ በአስጊና አደገኛ መንገድ ተጉዛል ፡፡ ለሕገ ወጥ የሰው ልጅ ግሪክ፣ መቆዶንያ፣ ሰርቢያ፣ሀንጋሪ ፡ ቦሲንያን ክሮኤሽያ በኩል ለመጓዝ ገንዘብ ከፍለዋል፡፡

ሕገ ወጥ የሰው ልጅ አዘዋዋሪወች አንድ እንቀፋት ሲገኝ ገንዘብ በማለት በተደጋጋሚ ይጠይቃሉ ።ይላል አሕመድ፡፡

”በአንድ ቦታ ስንያዝ በሌላ መንገድ የተሻለ መሆኑን ተስፋ ይሰጡናል፡፡ በዚህ ምክንያት ከአንድ አገር ወደ ሌላ አገር ስንጓዝ እንደገና በመያዝ ፣ በመደብደ ፣ በማስፋራራት በመጨረሻም ሳይሳካልን ይቀራል”፡፡

ሕገ ወጥ የሰው ልጅ አዘዋዋሪዎች በመጀመሪያ ጉዞ የመሓመድ መታወቂያ ወረቀቱና ሰነድ ወስደውበታል፡፡

”ምንም ሰነዶች የሉንም ከ32 ሰዓታት በላይ በእግር ተጓዝኩ ከአንድ ሕገ ወጥ የሰው ልጅ አዘዋዋሪ ወደ ሌላ ተሽጠናል ።ለብዙ ቀናት በጫካ አሳልፈን አንዳንድ ጊዜ እንበላለን በሌላኛው ቀን የሚጠጣ ውሃ እንካን አልነበረንም በማለት ተናግረዋል፡፡

ሕገ ወጥ የሰው ልጅ አዘዋዋሪዎች ወደ አውሮፓለማሻገር 70000 የአሜሪካን ዶላር እንዲከፍል ጠየቁት አከፋፈሉም ግማሹ በቅድሚያ የተቀረው ጀርመን አገር ከገባን በኃላ እንደሆነ ገለፁለት፡፡ ምንም እንካን በፍቃደኝነቱ ወደ አገሩ ለመመለስ ቢወስንም አሁንም ቢሆን ለህገ ወጥ የሰው ልጅ አዘዋዋሪዎች የሚከፈል 1800 የአሜሪካን ዶላር እዳ አለበት፡፡

ከብዙ ያልተሳኩ የስደት ሙከራዎች በላይ አሕመድ ወደ አገሩ እንዲመለስ ወስነዋል፡፡ አሕመድ ከ6 ወራት በሕገ ወጥ መንገድ አውሮፓን የመሻገር መኩራ በኃላ በዓለም አቀፍ የስደተኞች በፍቃደኝነት የመመለስ ፕሮግራም በመታገዝ ከሰርቢያ ወደ ኤብሪል ተመልሳል፡፡

እስከ 2015 እ.ኤ.አ በጀርመን ይኖሩ የነበሩትን 9000 ኢራቃውያን በዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት በፍቃደኝነት የመታገዝ ፕሮግራም በመታገዝ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ተደርጋል፡፡

አሁን አሕመድ በዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት (IOM) በመታገዝ ምንም እንካን ጊዚያዊ ቢሆንም በኤብሪል የመንጃ ፍቃድ ትምህርት ቤት ውስጥ ከወንድሙ ጋር እየሰራ ይገኛል፡፡

በስደተኞች ፕሮጀክት በህገ ወጥ መንገድ ወደ አውሮፓ ለመሻገር የሚሞክር እንደሆነ ሲጠየቅ በፍፁም እንደገና አላደርገውም ቤተሰቦቼም ቢሆኑ እንደዚህ አይነት ስህተት እንዳይፈፅሙ አድርጌአለሁ በማለት ተናግራል፡፡

ህጋዊና ዋስትና ባለው አማራጭ ወደ አውሮፓ ለመደረስ እንደሚፈልግ በማናገር ወደ አውሮፓ ለመሄድ እፈልጋለሁኝ። እኔ እና ቤተሰቦቼ ቪዛ እንድነገኝ ማመልከቻ አስገብቼሁ፡፡  ስለዚህ ሕገ ወጥ የሰው ልጅ አዘዋዋሪዎችን ከማመን ይልቅ ቪዛ መጠበቅ ዋስትና ያለው መሆኑን ገልፀዋል፡፡

TMP – 03/03/2019

ፍቶ ክሬዲት

ሕጋዊ ሰነድ የሌላቸው እያሉ ሕጋዊ ባልሆነ ኣገባብ ወደ ኣውሮፓ ለመግባት የሚሞክሩ ስደተኞች በኣገሪቱ ባለስልጣኖች ሊታሰሩ ይችላሉ

Personal Visit and interview – ቃለ መጠይቁን ያካሄደው ፋሒም ዳቫቶዛክሪን