በፓሪስ ከተማ ስደተኞች ከዩነቨርስቲ ተባረሩ
ስደተኞች ከፈረንሳይዋ መዲና የማባረር አንዱ አካል ነው፤ ይህ በፓሪስ ከተማ በአንድ ዩኒቪረስቲ ውስጥ የተወሰደ እርምጃ። የፈረንሳይ ፖሊስ ጁን 26 ላይ 200 ስደተኞች ካለፈው ጃንዋሪ ጀምረው ይኖሩበት የነበረ አንድ ዩኒቨርስቲ ህንፃ በመፈተሽ እንዲባረሩ አድርገዋል።
የማባረር ኦፕሬሽኑ was launched የተወሰነው የፓሪስ-8 ዩኒቨርስቲ ፕረዚደንት አሊክ ኣላጊረ ባቀረቡት አቤቱታ መሆኑ ታውቀዋል። ፕረዚደንቱ አቤቱታው ያቀረቡበት ምክንያት እነዚህ ስደተኞች ዩኒቨርሲቲው 800, 000 ዩሮ ተጨማሪ ወጪ እንድያወጣ ምክንያት ስለሆኑ ነው። ከዛም ባለፈ ስደተኞቹ የፀጥታ ችግር ይፈጥራሉ እንዲሁም ይሰርቃሉ ብለዋል።
“የፓሪስ 8 ዩኒቨርስቲ ፕረዚደንት አቤቱታ መሰረት በማድረግ ሲነ ሳይንት ደኒስ የከተማው ፖሊስ ከጃንዋሪ 30 ጀምረው በስደተኞች ተይዘው የነበሩ ህንጻዎች ነጻ እንዲሆኑ አዘዋል።” ይላል ፖሊስ ያወጣው ዘገባ።
“የፀጥታ አካሉ 194 ስደቶች ላይ እርምጃ እንደወሰደ” እና ሌሎች 160 ስደተኞች “ህጋዊ ያልሆኑ የህንፃው ሰፋሪዎች እንዲባረሩ ሆኖዋል።” ሲል ፖሊስ ያወጣው መግለጫ አክሎ ገልፀዋል።
ፖሊስ ወደ ዩኒቨርስቲው ሲገባ ወደ 70 የሚጠጉ ውሳኔው አስቀድመው ያወቁ አክቲቪስቶች እና የዩቨርስቲው ተማሪዎች አናስገባም በማለት ግርግር የፈጠሩ ሲሆን ፖሊስ አስለቃሽ ጋዝ ተጠቅመዋል።
የአፍሪካ በተለይም ደግሞ የምዕራብ እና የሱዳን እና ኤርትራ ጨምሮ የምስራቅ አፍሪካ ስደተኞች የሚተኙበት ክፍል አጥተው ከጃንዋሪ ወር ጀምረው በዩኒቨርስቲው ግቢ ውስጥ እየተኙ ነበር።
በተላለዩ የፓሪስ ከተማ ቦታዎች ማለትም በውስጥ ለውስጥ መንገዶች፣ በሜትሮ ላይንስ እና በተለያዩ የከተማ ጥጋጥግ መንገዶች ላይ ሲኖሩ የነበሩ ስደተኞች ባለፉት ሶስት ዐመታት ውስጥ እንዲባረሩ እየተደረገ መምጣታቸው ይታወቃል።
ከፊሎቹ በ2016 ላይ ካሊስ ጃንግልን ነፃ ለማዉጣት በተደገረ ኦፕሬሽን ሳብያ ወደ ፓሪስ የመጡ ናቸው።
TMP – 27/07/2018
ፓሪስ – ሜይ 5, 2017: በፓሪስ ደቡባዊ ምስራቅ አከባቢ ባሉ ጎደናዎች አንዱ ላይ ቤት አልባው ስደተኛ ጥርሱ እየፋቀ
ፅሑፉን ያካፍሉ