ፈረንሳይ በካልያስ አከባቢ የሚገኘው የስደተኞች ካምፕ አፈረሰች

ማርች 12 ቀን 2019 ፖሊስ ህገ ወጥ የስደተኞች ካምፖች ለማፍረስ እየተንቀሳቀሰ ቆይቶ በካሊስ አከባቢ የነበረ ወደ 200 የሚጠጉ ስደተኞች የሚኖሩበት ካምፕ ማፍረሱን ተሰማ።  

ይህ ቮሮተይርስ ወይም ቸሚን ዱ ፖንት ትሩሊ በመባል ሲጠራ የነበረ ካምፕ በቦታው ታላቁ ካምፕ ነበር። ካምፑ  ወደ 200 የሚጠጉ ስደተኞች ይኖሩበት የነበረ ሲሆን አብዛኛዎቹ አፍጋኒስታውያን፣ ኢራናውያን፣ ኤርትራውያን እና ሱዳናውያን ናቸው።   

ካምፑ እንደሚፈርስ ቀድሞ ሲነገር የነበረ ነው። እንደ አበርግ ደስ ማይግራንትስ የተባለ ድርጅት ገለፃ ከሆነ ካምፑ በሚፈርስበት ጊዜ 50 ሰዎች ብቻ በቦታው ነበሩ።   

ለዚሁ ድርጅት ቃላቸው የሰጡ ዲየጎ “ሁሉም ስደተኞች የማፍረስ ስራ እንደሚከናወን ያውቃሉ። ከፊሎቹ የተሻለ ማቆያ ፍለጋ ቀድመው ከቦታው ለቀዋል። አንዳንዶቹ ለመደበቅ ሞክረዋል አልያም በአከባቢው ወደሚገኙ ሌሎች ትናንሽ ካምፖች ሄደዋል።” ብለዋል።

ከመፍረሱ በፊት “ስደተኞቹ ወደ ተሻለና በመንግስት ወደ ተዘጋጀ የስደተኛ ማቆያ ማእከላት እንደሚወሰዱ” ተነግሮዋቸው ተፈራርመው ነበር።    እንደ 20 ሚኒትስ የተባለ ሚድያ አገላለፅ ከሆነ 46 ካምፖች ውስጥ የነበሩ ስደተኞች ዕድሉን ተቀብለው በባስ ወደ ማቆያ ማእከላት መሄድ ችለዋል።   

ይህ ካምፖች የማፍረስ ውሳነ የመጣው ኢንድስ በቡሎጊን ሱር መር ፍርድ ቀርቦ አሸናፊ ሆኖ መውጣቱን ተከትሎ ነው ተብለዋል።  የኤሌክትሪክሲቲ ካምፓኒው ስደተኞች የሚኖሩበት ሰፊው ክፍል የሚሸፍን ነበር። ካምፓኒው ታድያ አገልግሎት በሚሰጥበት አከባቢ ስደተኞች ካምፕ  እንዳይሰሩ የምያስችል አጥር ሊገነባ ነው።

የአከባቢው ባለስልጣናት እንደገለፁት ካምፖቹ “የአከባቢው የኢኮኖሚ ቀውስ ከማስከተሉ በላይ የአንዳንድ ካምፓኒዎች እንድቅስቃሴም  እያበላሹ” መሆናቸውን ገልፀዋል።  እነዚህ ካምፖች “የፀጥታ፣ የጤናና የንፅህና ስጋት እንዲሁም የሰው ልጅ ክብር” ላይ አሉታዊ ሚና ይጫወታሉ የሚሉ ድምዳሜዎች አሉ። ከፍተኛ የሆነ የኤሌክትሪክ አቅርቦት እንደሚፈልጉና መንገዶች እያጣበቡ ህይወት በአከባቢው ደስ የማይል እንዲሆን ያደርጋሉ የሚል ስጋት አለ።  

ከቅርብ አመታት ወዲህ   የእንግሊዝን ቻናል በማቋረጥ  ወደ እንግሊዝ ሀገር ለመድረስ ተስፋ ያነገረቡ ህገ ወጥ ስደተኞች በሰሜናዊ የፈረንሳይ ክፍል ካምፕ እየሰሩ ይኖራሉ።  የፈረንሳይ የፖሊስ ሀይል   በተደጋጋሚ ካምፖቹን ለማፈራረስ    የሞከረ ቢሆንም ስደተኞቹ ወድያው ወድያው ሌላ ካምፕ ይሰራሉ።   

ፈረንሳይ እና እንግሊዝ ህገ ወጥ ስደተኞች ላለማስገባት ጥብቅ አሰራር ውስጥ እየገቡ መሆናቸውን ተከትሎ ስደተኞች በችግር ውስጥ አሉ፤ እነዚህ ስደተኞች   ወደ ፈረንሳይ   እንዲመለሱ ተደርጓል።

TMP – 25/03/2019


ፎቶ: ህዩማን ራይትስ አብሶርቨርስ/ትዊተር. በካሊስ አከባቢ ቨሮተሪስ በተባለ ቦታ ውስጥ