በፓሪስ የነበሩ ህገወጥ የስደተኛ ካምፖች በፖሊስ ተወገዱ

ፎቶ: ቶማስ ሳምሶን Samson / ኤኤፍፒ. ጃንዋሪ 13/2019 ላይ ስደተኞች ወደ ስሜናዊ የፓሪስ ክፍል ለመሄድ በ ፓርቲ ዲ ላ ቪላቴ እና ፖርቲ ዲ ላ ቻፕሌ መሀካል እያሉ ጉዞዎቻቸው ካከማቹበት ቦታ በፖሊስ ተይዘው መጠልያቸው ተወግደዋል። ይህ ሁነት በዚሁ አስር ቀን ውስጥ የተደገረ አራተኛው  ኦፕሬሽን ሲሆን 800 የሚሆኑ ስደተኛች የተሻለ መጠለያ እንድያገኙ ያስቻለ ነው።   ይህ ኦፕሬሽን ግዝያዊ መጠለያ ሰርተው የሚቀመጡ ስደተኞችን የተሻለ ነገር እንድያገኙ በማስቻል ረገድ ጥሩ እርምጃ መሆኑን የፈረንሳይ መንግስት ገልጸዋል።

እንደ አጀንስ ፍራንስ ፕሬስ (ኤኤፍፒ) ዘገባ ከሆነ የፈረንሳይ ፖሊስ ባለፉት 10 ቀናት ውስጥ በሰሜናዊ የፓሪስ ከተማ  ብቻ በአራት ቦታዎች ህገወጥ መጠልያ ሰርተው ይኖሩ የነበሩ ከ1000 በላይ ስደተኞችን መጠልያቸው እንዲወገድ አድርገዋል።

በክሊግናኮርት፣ አቬኑ ዊልሰን፣ ፖርቴ ዶ ላ ቻፔለ እና በ ላ ቪለቴ የተባሉ አከባቢዎች በአራት ጣብያዎች ሲኖሩ የነበሩ ህገ ወጥ ስደተኞች በብዛት አፍጋኒስታውያን እና ከሌሎች የአፍሪካ ሃገራት የመጡ ስደተኞች መሆናቸውን ተነግረዋል።  

ከአራቱ ኦፕሬሽኖች አንደኛው የተካሄደው የፓሪስ ከተማን ከቦ በያዘው ከ “ፐርፈሪኩ” አጠገብ በሚገኘው ጎደና ላይ ነው። ወደ 300 የሚጠጉ ስደተኞች የተያዙት ጃንዋሪ 29/2019 ላይ ነው። የከተማው ባለስልጣናት እንዳሉት ከሆነ እነዚህ ስደተኞች በፈቃድ ከተማው ላይ ባሉ የስደተኛ ማቆያ ማእከላት እንዲቆዩ ተደርጓል። የባለስልጣናቱ ዘገባ እንደምያመለክተው የክረምቱ ወራት ውጭ ላይ ወድቀው እንዳይሳቃዩ በትንሹ ወደ ሚጠለሉበት ለመውሰድ ታስቦ የተደረገ እርምጃ ነው ብለዋል።  

የህክምና ድጋፍ እንድያገኙ ይደረጋል። ከዛ በኋላ አስተዳደራዊ መንገዶች ተከትለን እንሄድና በኋላ ላይ ወደ ማቆያ ማእከላት እንዲሄዱ ይደረጋል።” ብለዋል ብሩኖ አንድሬ የተባሉ ባለስልጣን። “ላለፉት ሳምንታት ባለማቋረጥ ስደተኞችን ወደ ማእከላት የመውሰድ ስራ ላይ ነው ተጠምደን የከረምነው። እነዚህ ስደተኞች ወደ ፖሊስ እንዲሄዱ ይደረጋል፡ ዛሬ 299 ስደተኞች በፖሊስ ፊት ቀርበው ቃል ለመስጠት ፈቃደኛ ሆነዋል።” ብለዋል ሀላፊው።

ፈረንሳይ ካለፉት አራት አስርት ዓመታት የበለጠ የስደተኛ ቁጥር እየተቀበለች ባለችበት በአሁኑ ሰዓት ስደተኞች የአሳይለም ጥያቄ አቅርበው መልስ ለማግኘት የሚወስድባቸው ጊዜ ግን ወደ ሁለት ወር ዝቅ እንዲል አድርጋለች። ይሁንና ወደ 64 በመቶ የሚሆን የስደተኞች የአሳይለም ጥያቄ ውድቅ ተደርጓል። ጥያቄአቸው ውድቅ የተደረገባቸው ስደተኞች አውሮፓን ለቀው እንዲወጡ ይገደዳሉ፡ አልያም መጀመርያ ወደገቡበት የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገር እንዲለመሱ ይደረጋል።

ፈረንሳይ በፓሪስ እና በሀገሪቱ ሰሜናዊ ጠረፍ አከባቢ የነበሩ የስደተኛ ህጋዊ ያልሆኑ ካምፖች ስታስወግድ ቆይታለች። ይህ የሆነውም በእንግሊዝ ቻናል በኩል ወደ እንግሊዝ ሀገር ለመሄድ የሚንቀሳቀሱ የስደተኞች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ ነው። የፈረንሳይ እና የእንግሊዝ መንግስታት እየጨመረ በመምጣት ያለ የስደተኞች ቁጥር በጥብቅ በመቆጣጠር ሰዎች ከአደገኛው ጉዞ ራሳቸውን እንዲጠብቁ በማድረግ ላይ መሆናቸው ተገልጸዋል። የእንግሊዝ መንግስት  ስደተኞችን ከእንግሊዝ ወደ ፈረንሳይ የመመለስ ስራ   መጀመሩን ተነግረዋል።  

TMP – 06/02/2019