ስድተኛው ልጅ በአውሮፓ ፍርድ ቤት ተፈረደለት

ፈረንሳይ ብቻውን ለሚኖረው አፍጋናዊ ስድተኛ  ልጅ  15000.00 ዩሮ እንዲከፍል የአውሮፓ ህብረት ሰብአዊ መብቶች ፍርድ ቤት ብይን ሰጠ።  ይህ ቅጣት የተላለፈው በካሬስ ፈረንሳይ በግዝያዊ የስድተኞች ካምፕ ለሚኖረው 12 ዓመት ልጅ አስፈላጊውን ጥበቃ ባለመድረጉ ምክንያት ነው።

የፈረንሳይ መንግስት ጀሚል ክሃን ለተባለ ልጅ የሚችለውን ሁሉ ጥበቃና እንክብካቤ አድርጓል የሚል እምነት እንደሌለው በስትራስቦርግ  የሚገኘው ፍርድ ቤት አስታውቋል። ባለስልጣኖች ሰብኣዊና ክብርን የሚነካ አያያዝ የሚከለክለው የአውሮፓ ሰብኣዊ መብቶች ስምምነትን በመጣሳቸው ፍርድ ቤቱ ይህንን ውሳኔ ሰጥቷል።

ምንም እንኳን ለክሃን ጉዳይ ይህን ውሳኔ ቢሰጥም እንዲህ ዓይነቱ ሁኔታ በፈረንሳይ ለሚኖሩት ልጆች ያልተለመደ ነገር አይደለም። የአፍጋኑ ስደተኛ ብቻቸውን ከሚኖሩት ብዙ ልጆች ጋር በመሆን ለስድስት ወራት በቆሻሻ ካምፕ በሰሜናዊ ፈረንሳይ ግዜውን አሳልፈዋል። አሁን ክሃን በብርሚንግሃም ዩናይትድ ኪንግዶም ውስጥ እየኖረ ይገኛል።

በፈረንሳይ 2015 እና ባለፈ አመት ዕድሜአቸው 18 አመት በታች የሆኑትን ኦፊሳላዊ በሆነ  መንገድ የታወቁት ስደተኞች ቁጥር በሰዎስት እጥፍ የጨመረ ሲሆን ይህም ለማህበራዊ ዋስትና አሰራር ወይም ስርአት አስቸጋሪ ሁኔታን ፈጥረዋል።  በአሁኑ ግዜ 17000 በላይ ለአካል መጠን ያልደረሱና ጥገኝነት ጠያቂዎች ስደተኞች በፈረንሳይ እንደሚገኙ አሶሴትድ ፕረስ ዘግቧል።  ሆኖም ግን የፈረንሳይ የአገር ውስጥ ሚኒስተር አብዛኞዎቹ  ጎልማሶች እንደሆኑና የተለየ እርዳታና መጠልያ ለማግኘት ሲሉ ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆች  መሆናቸውን ይናገራሉ ሲል ገልፀዋል።

የሰብአዊ መብት ተማጓቶች ግን በዚህ ጉዳይ አይሰማሙም። በጥቅምት 2018  እንደ ሎተሪ  በፓሪስ ብቻቸውን ለሚኖሩት ስድተኞች የሚደረግ ግድ የለሽ አያያዝ በማለት ባቀረበው ዘገባ የፈረንሳይ ባለስልጣኖችልጆችን ለመለየት የሚያደርጉትን አሰራር ነቅፈዋል።

ቡዱኑባለስልጣኖችን ለሚመለከተው አካል ተገቢውን አገልግሎት ለመስጠት ዝርዝር የዕድሜ ጥናት እንደሚያደርጉና ይህም ዓለም አቀፋዊ መመዘኛ የፈረንሳይ ህግ ደምብ የሚጥስ መሆኑንና  በዚህም ምክንያት ልጆች ማግኘት ያላቸውን አስፈላጊ  ጥቅሞች እንደ መጠልያ፣ትምህርትና የጤና አገልግሎቶችን  እንዲያገኙ  ያደርጋል። እስከዛውም በጎደናዎች  ማደር አለባቸውበማለት ይናገራሉ።

እነዚህ ልጆች ለማመን የሚከብድ ሁኔታና አደገኛ ጉዞዎች ውስጥ ተሳቃይተዋል። ይህም ሆኖ ማግኘት የሚገባቸውን ጥበቃና እንክብካቤ አላገኙምበማለት የፈረንሳይ የሰብኣዊ መብቶች ተሟጓቶች ዴረክተር በነዲክት ዣንሮድ ይናገራሉ።

ትክክልኛውን ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆች ዕድሜ ለመወሰን የስድተኞች አገር አቀፍ ዳታ ቤዝ ዝርዝር መረጃዎች የሚገኙበት የጣት አሸራዎችን ፎቶዎችን በማዳራጀት ላይ እንደሚገኙ የፈረንሳይ የአገር ውስጥ ሚኒስተር ተናግሯል። ሆኖም ግን የተባበሩት መንግስታት የህፃናት ጉዳይ ወኪል ድርጅት ዩኒሴፍ በፈረንሳይ ላይ ያለውን ቅሬታ ገልፀዋል። የህፃናት መብቶች ተሟጓቶች ይህ አዲስ የሆነውን መረጃ የግለሰብ መብቶችን የማያከብርና ባለስልጣኖች ወጣት ስድተኞችን ለማባረር እንዲችሉ ያበረታታል። እንዲሁም ብቻቸውን የሆኑት ልጆች ተገቢውን ድጋፍ ወይም እርዳታ እንዲያገኙ ያደርጋል በማለት ተናግረዋል።

TMP – 13/03/2019

ፍቶ  ሲምባዮት ሻተርስቶክ የአውሮፓ ሰብአዊ መብቶች ፍርድ ቤት ህንፃ