የፈረንሳይ ከተማ ከንቲባዎች ተጨማሪ ለስደተኞች የሚሆን አቅርቦት ጠየቁ
13 የፈረንሳይ የተለያዩ ከተማ ከንቲባዎች ለአሳይለም ጥያቂዎች የሚሆን አቅርቦት እንዲሟላላቸው ለሀገሪቱ መንግስት ይፋዊ ደብዳቤ ፅፈዋል።
አፕሪል 23 ቀን 2019 ላይ የተፃፈውን ይሄንን ደብዳቤ “እኛ ከንቲባዎች በየግዜው እየጨመረ እየመጣ ባለው የስደተኞች ቁጥር እና እየባሰ እየሄደ ያለ የስደተኞች የኑሮ ሁኔታ ክፉኛ አሳስቦናል።” ብለዋል። ባለፈው ወር የሰሜናዊ ኢል ዲ ፍራንስ ሪጅን መሪ የሆኑትን ሚኪኤል ካዶት እንደገለፁት አዲስ የስደተኛ ማቆያ ማእከል ፓሪስ ውስጥ ይከፈታል። ይህ አዲስ ማቆያ እስከ 100 ስደተኞች የመያዝ አቅም ይኖረዋል።
ይሁንና ደብዳቤ የፃፉት የከተማው ከንቲባ አነ ሂዳልጎ ችግሩ ለማቃለል አሁንም ተጨማሪ አቅርቦት እንደምያስፈልግ ነው የገለፁት።
በርካታ ቤተ ሰብ ያላቸው እና ልጆች የያዙ ስደተኞች እየተበራከቱ መምጣታቸው በፈረንሳይ ችግሩ አሳሳቢ እንዲሆን እያደረገው ነው። አደጋው አስጊ እንዲሆን የምያደርገው ያለ ደግሞ በካምፕ የሚኖሩ አቅም የሌላቸው ስደተኞች እየተበራከቱ መምጣታቸው ነው ተብለዋል።
ደብዳቤው እንደሚለው “በመተዎች የሚቆጠሩ ወንዶች፣ ሴቶች እና ህፃናት በከተሞቻችን እምብርት ላይ ድንኳን ሰርተው እየኖሩ ነው ያሉት።”
ከንቲባዎቹ እንደገለፁት የሀገሪቱ ፖለቲካዊ ድርጅቶችም በጉዳዩ ላይ ተወያይተው መፍትሄ እንድያበጁ ጥሪ አቅርበዋል።
በ2018 ጁን ወር ላይ የፈረንሳይ መንግስት ለአሳይለም ጠያቂዎች የሚሰጥ ድጋፍ መጨመሩ የሚታወቅ ሆኖ ኤዲኤ (ADA) ተብሎ ከሚታወቅ የስደተኞች ድጋፍ በተጨማሪ መሆኑ ለማወቅ ተችለዋል። በአዲሱ ህግ መሰረት አንድ አሳይለም ጠያቂ ማመልከቻ ካስገባበት ግዜ ጀምሮ በየቀኑ 7.40 ዩሮ ይሰጠዋል።
ከቅርብ ግዜ ወዲህ በፈረንሳይ አሳይለም የሚጠይቁ የስደተኞች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ ይነገራል። በ2017 ከ 100, 000 በላይ ስደተኞች በፈረንሳይ አሳይለም ጠይቀዋል፤ እንደ ፈረንሳይ የስደተኞች እና ሀገር አልባ ጉዳዮች ፅ/ቤት (OFPRA) ዘገባ።
TMP – 14/05/2019
Photo credit: ሎይስ ቬንስ / ኤኤፍፒ
Photo caption: አንድ ስደተኛ በምዕራባዊ ፍራንስ በቀድሞ ላይሲ ጃኒ–በርናንድ አከባቢ ከእንቅልፉ ሲነሳ ይታያል። ማርች 28 ቀን 2019
ፅሑፉን ያካፍሉ