ኢትዮጵያና እንግሊዝ ለሥራ ፈጠራና ለታክስ ሕግ ማሻሻያ የሚውል የ115 ሚልዮን እርዳታ ተፈራረሙ
ሚኒስትር አብርሃም ተኸስተና ለዓለም አቀፍ ልማት የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በኢትዮጵያ አዲስ አበባ እርዳታው ሲፈራረሙ፡፡ ፎቶ፡ መስፍን ሰለሞን/ ዘ ሪፖርተር
የእንግሊዝ መንግሥት በኢትዮጵያ 100,000 ሥራዎች ለመፍጠርና የአገሪቱ የታክስ ሕግ ለማሻሻል የ115 ሚልዮን GBP እርዳታ ተፈራረሙ፡፡
ለዓለም አቀፍ ልማት የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ ፔኒ ሞርዳንትና የፋይናንስና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር አብርሃም ተኸስተ በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ተግዳሮት ለመፍታትና የቀረበ ግንኙነት ለማድረግ፣ ስምምነቱ በ8 ኦገስት 2018 ተፈራረሙ፡፡
የእርዳታው በአብዛኛው 70% የሚውለው ለሁለቱም የአገር ውስጥና በምሥራቅ አገሮች አፍሪካ ለሚኖሩ ስደተኞች ሆኖ በኢትዮጵያ ጆብስ ኮምፓክት ፕሮግራም በኩል ነው፡፡ ዓላማውም 100,000 ሥራዎች 30,000 ሥራዎች ለስደተኞች ጭምር ለመፍጠር ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያ በጠረፎቿ እስከ 900,000 ኤርትራውያን፣ ደቡብ ሱዳኖች፣ ሱዳኖች፣ የመናውያንና ሶማሊያዎች ስደተኞች በማስተናገድ ከአፍሪካ ሁለተኛ አገር ናት፡፡ የቀረው 35 ሚልዮን GBP የታክስ ሕግ ፕሮግራምን በማሻሻል ረገድ ይውላል፡፡
ምንም እንኳ ኢትዮጵያ ከ1981 ጀምሮ በ GDP የ5.85% አማካይ እድገት ብታሳይ፣ ኢትዮጵያ ገና የሥራ አጥነት ፍጥነት ለመቀነስ በመታገል ላይ ትገኛለች፡፡ በአብዛኛው የወጣቶቿ አንድ አራተኛ ከሥራ ውጭ ነው፡፡
ለዓለም አቀፍ ልማት የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ ፔኒ ሞርዳንት የእንግሊዝ መንግሥት በጣም የተጎዱት ኢትዮጵያውያንና ስደተኞች ሥራ እንዲያገኙና ኑሮአቸውን ለማሻሻል ዝግጁ መሆኑን አረጋግጧል ብለዋል፡፡
በመስከረም2016 በስደተኞች በኒዮርክ የመሪዎች ስብሰባ ኢትዮጵያ ላይ በዘጠኝ ጉዳዮች ቃል ገብታለች፡፡ ከዚያ በኋላ አገሪቷ በሥርዓት የጀመረችው ፖስደተኞችን ለማዋሃድና በኢትዮጵያ ጥገኝነት በሚጠይቁ ስደተኞችን ለመርዳት የሚጠቅም ፖሊሲ የሚወጣ አገሪቷ ዘ ኮምፕረሄንሲቭ ሬፉጂ ሬስፖንስ ፍሬምዎርክ (CRRF) አውጥታለች፡፡
CRRF የሚያጠቃልለው ከካምፕ/ሰፈር ውጭ ፖሊሲ፣ ለስደተኞች የሥራ ፍቃድ መስጠት፣ በሦስቱም የትምህርት ደረጃዎች የሚመዘገቡት ተማሪዎች ቁጥረ ከፍ ማድረግ፣ ሰብል ለማምረት የሚያስችል የመስኖ እርሻ ማስፋፋት፣ በጣም ረጅም መፈናቀል በሚያጋጥምበት ወቅት አካባቢውን ለማዋሃሃድ ማመቻቸት፣ በኢንዳስትሪያል ፓርኮቹ ለስደተኞች የሚሆን ሥራ በመቶኛ ለይቶ ማስቀመጥና በጣም አስፈላጊ ለሆኑት የማህበራዊ አገልግለቶችና ዋና ዋና ክስተቶች በሚገባ መመዝገብ፡፡
እነዚሁ ለማስፈጸምከአውሮፓ ኢንቬስትሜንት ባንክ የተሰጠው ብድርና ከእንግሊዝ መንግሥትና ከዓለም ባንክ እስከ $500m (£385m) የሚሆን እርዳታ በኢትዮጵያ ለሁለቱ ኢንዳስትሪያል ፓርኮች ማሰሪያ ገንዘብ ይከፈላል፡፡
TMP – 25/08/2018
ፅሑፉን ያካፍሉ