የቼክ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሕገ – ወጥ ስደትን በስፋት ለመዋጋት ለአውሮፓ ጥሪ አቀረቡ

የቼክ ጠቅላይ ሚኒስቴር፣ አንድሬጅ ባቢዝ ሕገ-ወጥ ስደትን ለማስቆም የአውሮፓ አጠቃላይ የድርጊት ፕላን እንዲወጣ ጥሪ አቀረቡ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የቼክ መንግሥት ተግባራዊ የሆነ መፍትሔ እስኪገኝለት ድረስ ሁሉም ሕገ – ወጥ ስደተኞች ወደ አውሮፓ እንዳይገቡ ለማገድ አቋም እንዳለው ከማረጋገጣቸውም በላይ፤ ኔቶ የአውሮፓን ጠረፎች እንዲያስተዳድር ሥልጣን ሊሰጠው እንደሚገባ ሀሳብ አቅርበዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አውሮፓን የሚያነሳሳ ኃይለኛ፣ ግልፅና አንድ የሚያደርግ መልእክት ሲያስተላልፉ የሚከተለው ብለዋል፡ እኔ የስደተኞች መብዛት ችግር ለመፍታት አውሮፓ አጠቃላይ የሆነ ፐላን ማውጣት እንዳለባት ተረድቻለሁ፡፡ ከመሬት ተነስተን ስለ ኮታ/ድርሻ ስንከራከር 4 ዓመት አጥፍተናል፡፡ ባጭሩ የማስተላልፈው ያለሁት መልእክት አውሮፓ ክፍት መሆኗን ነው…

አውሮፓ ለስደተኞች የምታስተላለፈው መልእክት እንደሚከተለው መገለፅ አለበት በየአገራችሁ ቆዩና፣ እኛም እዛው እያላችሁ እንረዳችኋለንበማለት በተጨማሪ አሳስበዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ጣልያንና ማልታ የሥራ ጉብኝት ለማድረግ ከመነሳታቸው በፊት ለአገር ውስጥ ጋዜጠኖች ሲናገሩ፣ እርሳቸው እንደሚያምኑት አብዛኛዎቹ ሕገ – ወጥ ስደተኞች ከግጭት ለመሸሽ ብለው ደህንነት ያለበት ወደብ ፍለጋ እንደሚመጡ ሳይሆን፤ አውሮፓን ለውጭ ሰዎች ክፍት ማድረግ የሚለው ፖሊሲ ምክንያት በማድረግ እጅግ በበለፀጉት የአውሮፓ አገሮች የተሸለ ኑሮ ፍለጋ ነው የሚመጡት ብለዋል፡፡

60 መቶኛ የሕዝቧ ቍጥር አውሮፓን ለውጭ ሰዎች ክፍት ማድረግ የሚለው ፖሊሲ የሚቃወም ህዝብ ያላት የቼክ ሬፓብሊክ ባለፉት ሦስት ዓመታት እጅግ በጣም ጥቂት ስደተኞችን ከተቀበሉት የአውሮፓ አገሮች አንዷ ናት፡፡ አገሪቱ በፖላንድ፣ ሃንጋሪና ስሎቫኪያ ዳርቻ በኩል የአውሮፓ ሕብረት የስደተኞች ኮታ/ድርሻ የሚለው ፖሊሲ አሁንም ትቃወማለች፡፡

የአውሮፓ ሕብረት የስደተኞች ኮታ/ድርሻ ፖሊሲ የተመሰረተው በ2015 ዓ.ም ወደ ግሪስና ጣልያን ለገቡት ስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎች የተሰጠ መልስ ነው፡፡ በዚሁ አስገዳጅ ፖሊሲ እያንዳንዱ የአውሮፓ ሕብረት አባል አገር ከእነዚሁ 160,000 ስደተኞችን የመቀበል ግዴታ ነበረበት፡፡ ነገር ግን በህዳር 2017 ዓ.ም 32,000 ስደተኞች ብቻ እንዲቀመጡ ተደርጓል፡፡  

TMP – 03/09/2018

የቼክ ጠቅላይ ሚኒስቴር፣ እንድሬጅ ባቢዝ፡፡ ፎቶ፡ ቢዝነስ ኢንሳይደር