ህገ ወጥ ስደትን ለመቆጣጠር የምያስችል አዲስ የአውሮፓ ህብረት ስምምነት

የአውሮፓ ህብረት ረጅም ግዜ ከወሰደው የብራስለሱ ስብሰባ በሁዋላ ህገ ወጥ ስደትን ለመከላከል የምያስችል ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተገለፀ፡፡

ዘጠኝ ሰዐታትን የፈጀ ጥልቅ ውይይቱ ጁን 27 ከጥዋቱ 4፡30 ላይ አልቆ መሪዎቹ የጋራ የስምምነት አቋም አውጥተዋል፡፡ በስምምነታቸው መሰረት የአውሮፓ ህብረት ህገ ወጥ ስደት በአውሮፓ ሀገራት እያደረሰው ያለ ችግር ለመቅረፍ የምያስችል አዲስ አሰራር ለመተግበር ወስነዋል፡፡

እንደ መሪዎቹ ስምምነት ከሆነ አባል ሀገራቱ ጣልያን የተሸከመችውን ሀላፊነት ለመካፈል እንዲሁም የአሳይለም ሂደቱ ለማፋጠን የምያስችሉ በተለያዩ አከባቢዎች ማእከላት እንደሚከፈቱ ተገልፀዋል፡፡ እነዚህ ማእከላት ስደተኞች እና በጥቅም የሚመጡትን አካላት ለመለየት በማስቻል “ ፈጣንና ድህንነቱ የተጠበቀ አሰራር” እንዲኖር የምያደርጉ ናቸው፡፡ ይህ አዲስ አሰራር “ስደተኞች የመቀበልን ተአማኒነት የምያረጋግጡ” እንቅስቃሴዎች እንዲኖሩ ያደርጋል ተብለዋል፡፡ የአሳይለም ጥያቄአቸው ተቀባይነት ያላገኙ ስደተኞች ከማእከላቱ በቀጥታ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱም ይደረጋል፡፡ በተያያዥነትም እነዚህ ማእከላት ስደተኞችን ለማገዝ የሚፈልጉ ሀገራት ከዛ ማእከል እንዲወስድዋቸው ዕድል የሚፈጥሩ ናቸው፡፡

“ሀላፊነትን በመወጣት እና በተአማኒነት መካከል ያለ ሚዛን ለመጠበቅ የምያስችል ትክክለኛ ውሳኔ ወስደናል” ብለዋል የፈረንሳዩ ፕረዚደንት ኢማኑኤል ማርኮን፡፡

ከአሁን በፊት የአውሮፓ ህብረት አባል ሃገራት ስደተኞችን በመቀበል እና በመያ ዙርያ ልዩነት የነበራቸው ሲሆን ከዛም አልፈው አንቀበልም የሚሉ የነበሩ ሲሆን በዚህ ውይይት መሰረት ግን ሀቀኛ ጥገኝነት ፈላጊ ስደተኞችን በበጎ ፈቃደኝነት ለመቀበል በአባል ሀገራቱ ዘንድ በስምምነት ላይ ተደርሰዋል፡፡

ጁን 28 ላይ በመሪዎቹ ስብሰባ የወጣ የአቋም መግለጫ እንደምያሳየው እንደ ጀርመን ያሉ ሀገራት የተሸከሙትን ሀላፊነት ለማቃለል ሲባል የአሳይለም ሂደቱ የምያልቀው በህብረቱ አባል ሀገራት ነው ተብለዋል፡፡ በመድረኩ በተደረገው ስምምነት መሰረት ህገ ወጥ ስደተኞች የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት ድንበር ጥሰው እንዳይገቡ የምያስችል እንዲሁም የትኛው ሀገር ላይ ማረፍ እንደሚፈልጉ ለማወቅ የምያስችል አሰራር፤ “መንግስታቱ ህጋዊ እና አስተዳደራዊ እርምጃዎች” እንደሚወስዱ ታውቀዋል፡፡

በተለይ ከአፍሪካ ሀገራት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች የሚያርፉባት ጣያልያ ይሄንን ስምምነት እኛ ደስተኞች ነን” በማለት ተቀብለዋች፡፡

ቱርኪ ከሲርያ ለምትቀበላቸው ስደተኞች ተጨማሪ €3 ቢልዮን ድጋፍ ከአውሮፓ ህብረት ይሰጣታል፡፡ ይህ ፈንድ €1.2 ቢልዮኑ አውሮፓ ህብረት በአፍሪካ የግል ኢንቨስትመንት ለማበረታታት ብሎ ከወሰነውን ተቀንሶ እየተሰጠ ያለ ነው፡፡

መሪዎቹ በውይይታቸው €500 ሚልዮን ገንዘብ ከአውሮፓ ህብረት ወደ አውሮፓን ህብረት ትረስት ፈንድ ፎር አፍሪካ ለመስጠት ተስማምተዋል፡፡ ይህ የገንዘብ ድጋፍ የተወሰነው ከአፍሪካ ወደ አውሮፓ ለሚሰደዱ ስደተኞች የስደታቸው ምንጭ ከስር መሰረቱ ለመፍታት እንዲቻል ተብሎ ነው፡፡

ከዚህም በተጨማሪ የአውሮፓ ህብረት “ዞን መሰረት ያደረጉ ስራዎች” ማለትም ሬጅናል ዲስኢምባርክሽን ፕላትፎርምን ለማቋቋም ተስማምተዋል፡፡ ይህ አሰራር ለምሳሌ በሰሜናዊ የአፍሪካ ክፍል ባሉ ሀገራት ውስጥ ስራ በመስራት ስደተኞቹ ሜዲትራያን ባህርን ከማቋረጣቸው በፊት እንዲመለሱ የምያደርግ ነው፡፡ ይሄንን በማድረግ በሰው ሽያጭ እና በህገ ወጥ የሰው ልጅ ንግድ የተሰማሩ ወንበዴዎችን ለማስቆም ይቻላል ተብለዋል፡፡

TMP – 03/08/2018

ብራስለስ, በልጄም ፤ ጁን. 28, 2018.፤ የአውስትራያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሰባትያን ኩርዝ ከአውሮፓ ህብረት ባለስልጣናት ጋር ለምያደርጉት ስብሰባ ሲሄዱ