ጣልያን ስደተኞችን የጫነች መርከብ ወደ ሊብያ እንዲመለሱ በማድረግዋ እየተወቀሰች ነው።
ጣልያን 108 ስደተኞችን ይዛ ወደ ሊብያ በመመለስዋ ምክንያት ( rescued 108 migrants and returned them to Libya.) ዓለም አቀፍ ህግን እየጣሰች ነው ተብላለች።
የስፔኑ የሁማኒተርያን ተቋሙ “ፕሮአክቲቭ ኦፕን አርምስ” ኦሶ 28 የተባለችውን ጀልባ ከጥፋት ያዳነው ጁላይ 30 ላይ ነው። አዳኙ መርከብ ለስደተኞች የማትመች መሆንዋን ወዲሚነገርላት ሊብያ እንዲደርሱም አድርገዋል።
የአውሮፓ ኮምሽን እንደገለፀው ይህ ሁነት እንዴት እንደተፈጠረ ከሮማ ባለ ስልጣናት ጋር በውይይት ላይ ናቸው።
የኮምሽኑ ቃል አቀባይ ናታሻ በርቱድ እንዳሉት “ሊብያ ድህንነቱ የተጠበቀ የስደተኞች አከባቢ አይደለም፤ በመሆኑም ይህ ድርጊት የአለም አቀፍ ህግ ጥሰት ነው።” ብለዋል። ኮምሽነሩ ጨምረው እንደገለፁት በምን ምክንያት እና በምን ሁኔታ ውስጥ ሆነው የወሰኑት መሆኑን ለማወቅ በጥናት ላይ ነን” ብለዋል።
የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኤጀንሲ ጁላይ 31 ላይ ባወጣው መግለጫ እንደገለፀው “108 ስደተኞች ከሜዲትራንያን ባህር ወደ ሊብያ ስለመለሰች አይሶ ቨንተቶ የተባለችውን ጀልባ በተመለከተ አስፈላጊ መረጃዎችን በማሰባሰብ ላይ ነን” ብለዋል።
እንደ ኦፕን አርምስ ገለፃ ከሆነ የእነዚህ ስደተኞች ህይወት ለማዳን ላይ ታች በሚሉበት ወቅት የራድዮ ኮሙኒኬሽን ሲግናል አግኝተዋል። ሲግናሉ በጣልያን እና ሊብያ ባለስልጣናት መካከል የሚደረግ ኮሙኒኬሽን የሚገልፅ ነበር ነው ያሉት። በንግግራቸው ይሄንን ችግር የተፈጠረው በሜዲትራንያን ባህር ላይ መሆኑ ተስማምተዋል። ይህ ድምዳሜ በጣልያኑ የ“የፍሪ ኤንድ ኢኳል ፓርቲ” ባሌቤት የሆኑት ፖለቲከኛ ኒኮላ ፍራትያኒ ድጋፍ አግኝተዋል።
የጣልያኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማቲው ሳሊቪኒ በፌስቡክ ገፃቸው እንደገለፁት “ጉዳዩ ከአንዳንድ ኤንጅኦ እና ሌፍቲስት ኤምፒ የሚወጣ ሀሰተኛ መረጃ እንደምያሳዩት አይደለም፤ የጣልያን የባህር ጠረፍ ጠባቂዎች በእነዚህ ኦፕሬሽኖች ላይ እጁ የለበትም።” ብለዋል።
በሌላው ራስ በራሱ የሚጋጭ የቲዊተር ፅሑፋቸው ደግሞ፤ ሳሊቪኒ “ እነዚህ የኤንጅኦ ዓማፅያን እና ( NGOs protest ) ህገ ወጥ ደላሎች ግን ስራ አጥተዋል? መልካም! በዚህ መንገድ እኛም እንቀጥልበታለን!” ብለዋል።
የጣልያኑ የትራንስፖርት ሚኒስትር ዳኒሎ ቶኒነሊ እንደዚህ አይነት ተግባር በሀገራቸው እጅ እንዳልተፈፀመ የገለፁ ሲሆን “ማለት የምችለው ነገር ቢኖር የጣልያን ግብረ ሀይል በዚህ ኦፕሬሽን ውስጥ አልተሳተፈምም፤ የተሰጠው አቅጣጫም የለም።” ብለዋል። በመሆኑም በጣልያን የተጣሰ አለም አቀፍ ህግ የለም” ሲሉ አክለዋል።
የጣልያን የባህር ላይ ጠባቂዎች እንደሚሉት “ኦፕሬሽኑ የተፈፀመው በሊብያ የባህር ጠረፍ ጠባቂዎች አማካኝነት ነው።” በኋላ ላይ የተገኘው መረጃ እንደምያመላክተውም ኦፕሬሽኑ የተካሄደው “ሰርች ኤንድ ረስክዩ” በተባለው የሊብያ ቦታ ላይ ነው። ይህ ቦታ በተጨባጭ የትኛው አከባቢ ነው የሚል ጥያቄ መልስ ባይገኝበትም ከ ሊብያ ባህር ግዛቶች ራቅ ብሎ የሚገኝ መሆኑን ይነገራል።
የአይሶ 28 ባለንብረቶች እንዳረጋገጡት ኦፕሬሽኑ የተፈፀመው በሊብያ የባህር ጠረፍ ጠባቂዎች መሆኑ እና የድረሱልን ጥሪ ተከትላ የመጣችው መርከብም 2.5 ኪሎ ሜትር ራቅ ብሎ ከሚገኝ የጋዝ ጣብያ መሆኑ ተናግረዋል።
ይሁን እንጂ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ኤጀንሲ አይኦኤም ቃል አቀባይ እንደገለፀው መጀመርያ የተነገረው “ባልታወቀ ቨስል” ሲሆን በኋላ ግን “የሊብያ ነው” ወደሚል ተቀይረዋል ነው የሚለው።
ይህ አይሶ 28 የተሰኘውን መርከብ አሁን በሊብያ ትሪፖሊ ከተማ በቁጥጥር ስር ይገኛል።
TMP – 03/09/2018
ፅሑፉን ያካፍሉ