ሊብያ ውስጥ ስደተኞች ለትርፍ ሲባል ታግቷል ከባህር ውስጥ ይልቅ በየብስ ጉዞ ህይወታቸው የሚያልፉ ስደተኞች ይበዛሉ። በሁለቱም አገሮች መካከል ያለው ድንበር የተዘጋ ቢሆንም ኤርትራውያን አሁንም ወደ ኢትዮጵያ መሸሻቸውን አላቋረጡም ጣልያን ፤- በባህር ላይ ተገኝተው ወደ ሊብያ እንዲመለሱ በሚገደዱ ስደተኞች ላይ ከሊብያ ጋር የነበራት ስምምነት አድሳለች ኢትዮጵያ ፤ ለስደተኞችና ለዜጋዋ እኩል እድል የተረጋገጠባት አገር

ጣልያን እተዘዋወሩ የሚጠብቁ ጀልባዎች ለሊብያ ልትሰጥ ነው

የሊብያ የጠረፍ ጠባቂ ጀልባ፡፡ፎቶ፡ ማቲያስ ሞንሮይ/ በአውሮፓ ሕብረት የደህንነት አዋቂና የፖሊስ ግብረ አበር  

ሊብያ ወደ አውሮፓ የሚመጡት ሕገወጥ ስደተኞችን ለመግታት ከኢጣልያ 10 የጠረፍ ጠባቂ ጀልባዎችና 2 መርከቦች ልትቀበል ነው፡፡ መግለጫው የወጣው የተሰጠው እርዳታ የኢጣልያ ፓርላማ በሰኞ 6 ኦገስት 2018 ከፈቀደ በኋላ ነው፡፡

በዚሁ በሚሰጠው እርዳታ መሰረት ሊብያ ጠረፏን የሚጠብቁ የጦር መርከቦቿ ቍጥር በእጥፍ ያሳድገዋል፡፡ በተጨማሪም የኢጣሊያ መንግሥት መርከቦቹን ለመጠገንና ለጠረፍ ጠባቂዎችና የባህር ኃይል ኣባሎችን ዓመቱን በሙሉ ሥልጠና በመስጠት ረገድ ለመተባበር ቃል ገብቷል፡፡

ሮም  አውሮፓን በሙሉ ሕገ-ወጥ ስደተኞች የሜዲቴራንያን ባህርን ከመሻገር ለመከላከል የሊብያ የጠረፍ ጠባቂዎችን በማጠናከር ረገድ ለመተባበር ዝግጁ መሆኗን ገልፃለች፡፡ ጣልያን የማዳን ሥራን ከሊብያ ኃይሎች በትብብር አብሮ የሚሠራና ሕገወጥ ስደተኞችን አሳፍረው የሚጓዙትን ጀልባዎች የሚያስቆም የማስተባበርያ ማእከል በትሪፖሊ አቋቁማለች፡፡ በተጨማሪም ሮም ወደቦቿ ከአደጋ የተረፉትን ሕገ – ወጥ ስደተኞችን ይዘው የሚመጡትን መረከቦች እንዳያስቆሙ ዘግታለች፡፡ ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM)፣ በሰጠው ሪፖርት መሰረት በዚህ ዓመት ብቻ የሊብያ የጠረፍ ጠባቂዎች 12000 ስደተኞች መያዙን ገልጿል፡፡

ባላፈው ሳምንት የኢጣልያ የአገር ውስጥ ሚኒስትር፣ ማቴኦ ሳልቪኒ የኢጣልያ መንግሥት የሊብያ የጠረፍ ጠባቂዎች እየተዘዋወሩ የሚጠብቁት ጠረፍ ለማስፋትና ከሊብያ ስደተኞችን የሚወስዱ ጀልባዎች ለማስቆም የሚያስችል አዲስ ዘዴ ማውጣቱን ተናግሮአል፡፡ የአውሮፓ ሕብረት አገሮችም ከኢጣልያ መንግሥት ለሊብያ ጠረፍ ጠባቂዎች የወታደራዊ ንብረት፣ ገንዘብና የሰው ኃይል ለመስጠት በቅርበት እየሠራ ነው፡፡

TMP – 23/08/2018