በሊብያ የስደተኞች ማእከል ውስጥ በተከሰተ ተቃውሞ ለብዙ ስደተኞች መጎዳት ምክንያት ሆነዋል

ፌቡራሪ 26 ላይ በሊብያ ትሪፖሊ ከተማ ውስጥ በሚገኝ አንድ የስደተኞች ማእከል በተከሰተ የስደተኞች እና አሳይለም ጠያቂዎች ተቃውሞ የፀጥታ አካላት ተቃውሞውን ለማርገብ ባካሄዱት እንቅስቃሴ 50 ሰዎችን ጉዳት ደረሳቸው።  

እንደ የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኤጀንሲ ድርጅት ከሆነ በትሪፖሊ ከተማ አልሲካ የስደተኞች ማእከል ውስጥ የተካሄደው ተቃውሞ በማእከሉ እያጋጠማቸው ያለ መልካም ያልሆነ የኑሮ ሁኔታ እና መፍትሄ ፍለጋ በሚል የተቀሰቀሰ ነው። ከእነዚህ ጉዳተኞች ሁለቱ ክፉኛ ስለተጎዱ ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል። ከፀጥታ አስከባሪዎችም የተጎዱ እንዳሉ ተገልፀዋል።  

ይህ ተቃውሞ በተካሄደበት ወቅት ወደ 400 የሚጠጉ ስደተኞች በስደተኛ ማቆያ ማእከሉ እንደነበሩ ታውቀዋል። የስደተኞች ኤጀንሲው እንዳብራራው ብዙዎቹ ኤርትራውያን ሲሆኑ የኢትዮጵያ፣ ሶማልያና ሱዳን ስደተኞችም ነበሩ። በተቃውሞው ምክንያት 120 ስደተኞች ወደ ሌላ የስደተኛ ማእከል እንዲዘዋወሩ ሆነዋል።      

አለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት የኦፕሬሽን እና ስደት ጉዳዮች ዳይሬክተር የሆኑት ሞሐመድ አቢከድር “መልካም ያልሆነ የስደተኞች ማእከላት አያያዝ እና የመብት ጥሰት እንቃወማለን። ከማእከሉ የተገፉም  አፋጣኝ ድጋፍ እንዲደረግላቸውም ጥሪ እናቀርባለን።” ብለዋል።  

በሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች ሊብያ ላይ ሰብአዊነት በጎደላቸው፣ የፅዳት ችግር በሌላቸው  ማእከላት ውስጥ ይኖራሉ።  ስደተኞች የምግብ፣ የፅዳትና የህክምና መጓደሎች ይገጥማቸዋል።  ከአሁን በፊትም   ከጥበቃ አካላት ጋር ተጋጭተው ለመውጣት ተቃውሞ  አድርገው፤ እሱ ብቻ ሳይሆን    ራሳቸው ያጠፉ እንደነበሩም ይታወቃል።

አለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት IOM ሌላ የስደተኞች ማእከል እንዲኖር ጥሪ እያቀረበ ነው። ሌሎች አዳዲስ ህገ ወጥ ስደተኞች እያመጡ መጨመር ተጋላጭነታቸው  እያባባሰው ነው። ሁኔታው በተለይ ለሴቶች እና ህፃናት አስቸጋሪ እየሆነ ነው።” ብለዋል የድርጅቱ ቃል አቀባይ አብዲከር።  የስደተኞች ህይወት መበላሸት እና መብት መጣስ በምንም መልኩ ምክንያት ሊሰጠው የሚችል አይደለም።” ሲሉም አክለዋል ቃል አቀባዩ።

በአሁን ሰዓት 5,700 ስደተኞች ሊብያ ውስጥ ባሉ የስደተኞች ማእከላት እንዳሉ ይገለፃል። በያዝነው የፈረንጆች አመት (2019) የሊብያ የባህር ጠረፍ ሰራተኞች 778 ስደተኞችን ከባህር በመመለስ ሊብያ ውስጥ ባሉ ማእከላት እንዲቆዩ አድርገዋል።

የተባበሩት መንግስታት ከ2017 የፈረንጆች አመት ጀምሮ በጣም የተጎዱ ስደተኞች ከሊብያ የስደተኛ ማእከላት እያነሳ ኒጀር እና ሮማንያ ወደየሚገኙ  የትራንዚት ማእከላት እየወሰደ ቆይተዋል።  የተባበሩት መንግስታት እንደገለፀው ድርጅቱ ማርች 4/2019 ላይ ያደረገው ወደ ትራንዚት ማእከላት የማዘዋወር የቅርቡ ጊዜ ኦፕሬሽን   128 ስደተኞች ወደ ኒጀር    ያዘዋወረ ሲሆን ይህ ኦፕሬሽን የተዘዋዋሪ ስደተኞች ቁጥር ወደ  3,303 እንዲያሻቅብ አድርጎታል።

በአሁን ሰዓት  56,484 የተመዘገቡ ህገ ወጥ ስደተኞች በሊብያ ምድር ውስጥ ያሉ ሲሆን አብዛኛዎቹ ወደ ሀገራቸው መመለስም ሆነ ሜዲትራንያን ባህር አልፈው ወደ አውሮፓ መሄድ የማይችሉ ናቸው። የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኤጀንሲ እንደሚገምተው ደግሞ በአሁን ከ 400,000 በላይ ስደተኞች በሊብያ ይገኛሉ።  

TMP – 16/03/2019

ፎቶ: አንጆ ካን/ሻተርስቶክ. ሜዲትራንያን ባህር አቋርጠው ለመሄድ ስደተኞች ሲጠቀሙባት የነበረች  ጀልባ ወድቃ ትታያለች