2018፡ ለስደተኞች ፈታኙ አመት
አሳይለም የሚጠይቁ ሆነ ሌሎች ስደተኞች የተሻለውን ዓለም የማግኘት ፍላጎት እና ጥረት በጣም ፈታኝ የሆነበት አመት ነበር፤ 2018።
ከተለያዩ የኤስያ፣ አፍሪካ እና ላቲን ኣሜሪካ ሃገራት ወደ አውሮፓ፣ ሰሜናዊ አሜሪካ እና አውስትራልያ ሃገራት ለመድረስ የሚጓዙ ስደተኞች በ 2018 ከማነኛውም አመት በላይ ከባድ አመት ነበር ተብለዋል። ይህ የሆነበት ምክንያትም በቅርቡ እየወጣ ያለ ስደተኞችን የሚከለክል ጠንካራ ደንብ እና እየተመረጡ ያሉ ህዝበኛ አመለካከት ያላቸው ፖለቲካዊ ሀይሎች በፈጠሩት ጫና ነው ተብለዋል።
ባለፈው አመት ጣልያን በሜዲትራንያን ባህር ስትሰራ የነበረችው የግብረ ሰናይ ተቋም የህይወት አድን መርከብ አባርራለች። በዚህ ሳያበቃ ስደተኞች ከባህሩ ወደ ሊብያ ለመመለስ የምያስችል ስልጠና ለሊብያ ሰጥታለች። ይህ ሁነት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ኤጀንሲ አውግዞታል። በቅርቡ ደግሞ ስደተኞች ቤት አልባ እና ተጋላጭ እንዲሆኑ የምያደርግ ሳልቪኒ ዴክሬ” የተባለ ፖሊሲ አፅድቃለች።
የአፍሪካ መሪዎች እና የአውሮፓ ህብረት ሚኒስትሮች ቬና ላይ ስደትን በተመለከተ ባደረጉት ስብሰባ የአውስትርያ እና የጣልያን የሀገር ውስጥ ሚኒስትሮች ስደተኞች በጀልባ እንዴት ከሜዲትራንያን ባህር መመለስ እንደሚቻል የምያሳይ መነሻ ሀሳብ ይዘው ቀርበዋል። ስደተኞቹ አንዴ እግራቸው ካረፈ ለመመለስ ከባድ እና ብዙ ኪሳራ የሚጠይቅ ነው።” ብለዋል የአውስትራይው የሀገር ውስጥ ሚኒስትር ሀርበርት ኪክል።
እንደነዚህ አይነቶቹ ውሳኔዎች እና ፖሊሲዎች በአጠቃላይ የስደተኞቹን ቁጥር የቀነሰ ቢሆንም የስደተኞች ሞት ግን በንፅፅር ጭማሪ አሳይተዋል። በዚህ አመት ብቻ በሜዲትራንያን ባህር ከ 2,200 በላይ ሰዎች ሞተዋል። ይህ ቁጥር መንገዱ የአለማችን ከፍተኛ የስደተኞች ሞት የሚታይበት ቦታ ሆኖ እንዲመዘገብ አድርጎታል። አብዛኛዎቹ ሟቾች ከፍተኛ ድህነት ያላቸው እና ተጋላጭነታቸው ከፍተኛ እንደሆኑ ከሚነገርላቸው ሊብያ አልያም ሞሮኮ በመነሳት የሚሂዱ መሆናቸው ተነግረዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ 2018 መልካም ነገሮችም የታዩበት አመት ነበር ማለት ይቻላል። በአንዳንድ የተመጠነ የህዝብ ብዛት ያላቸው ሃገራት በተለይ ወጣቱ የህብረተሰብ ክፍል የስራ ዕድል እንዲፈጠርለት እየተደረገ ያለ ስራ እንደ መልካም ስራ የሚወሳ ነው። ይህ ስራ ቢዝነስ ለመጀመር ያምያስችል ብድር መስጠት እና ተግባራዊ ስልጠናዎችን ያካትታል። እንዲሁም ቢዝነስ ማስተዳደር የምያስችል አቅም እንድያጎለብቱ የምያስችሉ እግዛዎች ይገኙበታል።
የአውሮፓ ህብረትም ይሄንን የስራ ሁኔታ የማመቻቸት ስራ ደግፈዋል። በኦገስት 2018 እንግሊዝ 115 ሚልዮን የጂቢፒ ግራንት ፈርመዋል። ይህ የፈረመው ለኢትዮጵያ ሲሆን ዓላማው ለ100,000 የምያህል የስራ ዕድል ለመፍጠር ነው። ጀርመን እንዳለቸውም ከስደት ተመላሾችን መልሶ ለመቋቋም የምያስችል የ አራት አመት ፕሮግራም በምብራቅ አፍሪካ ለመተግበር ተዘጋጅታለች። ኖቨምበር 2018 ላይ የአውሮፓ ህብረት ልኡካን ቡድን ወደ ጋምብያ ባደረጉት ይፋዊ የስራ ጉብኝት እንዳሉት ስራ፣ ክህሎት እና ፋይናንስ ለሴቶች እና ወጣቶች ፕሮግራም (ጄኤስኤፍ) በጋምብያ 3 ሺ የምያህሉ የስራ ዕድሎች ለመፍጠር በዝግጅት ላይ ነው።
በስደት መንገድ ላይ የነበሩ ስደተኞች ለመመለስ፣ መልሶ ለማቋቋም ወይም ደግሞ ወደ ነበሩበት ለመመስ የአለም አቀፉ የስደተኞች ተቋም እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ተቋም እንደምያግዙ ታውቀዋል። የተባበሩት መንግስታት ባወጣው የመልሶ ማቋቋም ፕሮግራም መሰረት በሊብያ ተዘግተው የነበሩ ስደተኞችን ወደ ኒጀር በመውሰድ እዛ እንዲቆዩ ተደርገዋል።
በስተመጨረሻም የዓለማችን ታሪካዊ ውሳኔ! ግሎባል ኮምፓክት በተባለው ኮንፈረንስ የተሻለ፣ የተመራ እና ሬጉላር የስደት ሁነት እንዲኖር ከ10-11 ዴሰምበር ማራካሽ ላይ በነበረው ቆይታ ከ193 ሃገራት 164ቱ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አባል ሃገራት በ23 ስትራተጂክ አለማዎች ላይ ከስምምነት ደርሰዋል። ይህ ስምምነት ከያዘቸው ዓላመዎች አንዱ ከስደት ተመላሾችን ማቋቋም፣ ድምብር ዘለል የስደት ጉዞ እንዲቆም ማድረግ፣ የስደተኞች መብት መጠበቅ ከብዙዎቹ ጥቂቶች ናቸው።
ስለሆነም በ2018 ለስደተኞች ከፍተኛ ውጥረት የነበረው ዓመት ቢሆንም ለኢኮኖሚክ ስደተኞች ግን መልካም ነገር የታየበት አመት ነው። ምክያቱም የስራ ዕድሎች በመክፈት ረገድ ጥሩ የሚባሉ እርምጃዎች የተወሰዱበት ዓመት ነውና። ቢያንስ 164 የዓለማችን ሃገራት ለስደተኞች የተሻለ ዓለም እንድትኖር ከስምምነት ደርሰዋል።
TMP – 31/12/2018
ፎቶ: ኦገስት 13, 2018; ቢሃክ, ሰርብይ. ተቃዋሚ ፖስተር ይዘዋል። ፖስተሩ ላይ “ስደተኞች፤ ቤታችሁ ሂዱ!” የሚል ፅሁፍ ተፅፎበታል።
ፅሑፉን ያካፍሉ