ሊብያ ውስጥ ስደተኞች ለትርፍ ሲባል ታግቷል ከባህር ውስጥ ይልቅ በየብስ ጉዞ ህይወታቸው የሚያልፉ ስደተኞች ይበዛሉ። በሁለቱም አገሮች መካከል ያለው ድንበር የተዘጋ ቢሆንም ኤርትራውያን አሁንም ወደ ኢትዮጵያ መሸሻቸውን አላቋረጡም ጣልያን ፤- በባህር ላይ ተገኝተው ወደ ሊብያ እንዲመለሱ በሚገደዱ ስደተኞች ላይ ከሊብያ ጋር የነበራት ስምምነት አድሳለች ኢትዮጵያ ፤ ለስደተኞችና ለዜጋዋ እኩል እድል የተረጋገጠባት አገር

በሜዲቴራንያን ባህር ብዛታቸው 10,000 የሚሆኑ ስደተኞች የጫኑ ጀልባዎች በ2018 ዓ.ም ጉዞኣቸው እንዲቋረጥ ተደርገው ወደ ሊቢያ ተመልሰዋል፡፡

እስከ አሁን ድረስ በ2018 ዓ.ም፣ የሊቢያ የጠረፍ ጠባቂዎች በሜዲቴራንያን ባህር በኩል ወደ አውሮፓ ጠረፎች ለመሻገር ያሰቡት 10,000 ስደተኞችን ከአደጋ በማዳን ጉዞኣቸውን በማቋረጥ ወደ ሊቢያ እንዲመለሱ አድርገዋል፡፡ የቁጥሩ መረጃ ጥናት የተገለፀው ከአንድ የፖለቲካ ፓርቲ በተጠየቀው መሠረት በመስከረም 18 በጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ነው፡፡

የሊቢያ ጠረፍ ተባቂዎች በእነዚህ የማዳን ጥረቶች በጥቂት የአውሮፓ አባል አገሮች ባደረጉላው እገዛ ነው፡፡ በሓምሌ 2018፣ የጣልያን መንግሥት ወደ ሊቢያ ሲሻገሩ የመርከብ መስጠም ወይም አደጋ በሚያጋጥማቸው ስደተኞች ለማዳን ከሊቢያ ጠረፍ ጠባቂዎች ጋር ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡ ይህንኑ የፍለጋና የማዳን ጥረቶች ለመደገፍ የጣልያን መንግሥት የጥበቃ ጀልባዎች በማቅረብ፣ መካከለኛ መርከብ በማቅረብና ሥልጠና በመስጠት ረገድ የሊቢያ የጠረፍ ጥበቃ የጦር መርከቦችን አቅም ከፍ አድርጓል፡፡

ባለፈው ሓምሌ የጣልያን የመከላከያ ሚኒስቴር፣ ኤሊዛቤታ ትሬንታ ለስካይ 24 ጋዜጠኛ፣ የሊቢያ የጠረፍ ጥበቃ ክፍል ይህ ኃላፍነት ወስዶታል፡፡ የጠረፍ ጥበቃው ክፍል የሠለጠነው በራሳችን የጠረፍ ጥበቃው ክፍል፣ ሲሆን ኃላፍነቱም ለመወጣት በቂ አቅም አለው” ብለው ተናግረዋል፡፡

አብዛኛው ጊዜ ወደ ሊቢያ በመመለስ የተላለፉት ስደተኞች ወደ እስር ቤቶች ነው የሚላኩት፡፡ የእነዚህ እስር ቤቶች ሁኔታ በተባበሩት መንግሥታትና በመብቶች ጥበቃ ቡድን በጣም አስከፊ የኑሮ ሁኔታ እንዳላቸው፣ በተጨማሪም “አጭቆ በማሰርና መሠረታዊ የኑሮ ደረጃ በሌለበት እንደሚያስሩ ተነቅፈዋል፡፡ የተባበሩት መንግሥታት እንዳለው በሊቢያ መንግሥት የሚተዳደሩ 20 እስር ቤቶች አሉ፡፡ የተባበሩት መንግሥታት በእነዚሁ እስር ቤቶች ከ8,000-10,000 እስረኞችው  መኖራቸው ይገምታል፡፡

ሊቢያ የዓረብ ስፐሪንግ በ2011 በወቅቱ የነበሩት መሪ ሙዓመር ጋዳፊን ከጣለች ወዲህ በተለዋዋጭ የፖለቲካ ሁኔታ ቆይታለች፡፡  

በቅርቡ በሊቢያ በ17 መስከረም በትሪፖሊ የተነሳው ውጊያ፣ ከሁለት ሳምንት በፊት በተባበሩት መንግሥታት የተደረገው የተኵስ ማቆም ስምምነት እንዲቋረጥ ምክንያት ሆኗል፡፡ ባለፉት ጥቂት ወራት የተካሄዱት የጎዳና ጦርነቶች ምክንያት ከሶማሊያ፣ ከኢትዮጵያና ከኤርትራ የሄዱት ስደተኞች ከተለያዩ የእስር ቤቶች ከተፈቱ በኋላ እንደገና ተከብበው ወደ ሌላ እስር ቤት ሲገቡ በኣል ጄዚራ ታይቷል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት በነሓሴ 2018 የሚከተለው ብሏል፣ “በዚሁ ምክንያት በእስር ቤቶች ውስጥ የሚገኙት ጥገኞች ላለው ቀፋፊ የኑሮ ሁኔታ እንዲሻሻልላቸው በመጠየቅ አመፅና የረሃብ አድማ እያደረጉ ነው፡፡”  

TMP – 25/09/2018

ፎቶ፡ www.alaraby.co.uk  የስእሉ መግለጫ፡ ብዙ ስደተኞች በሊብያ ጠረፍ ጠባቂዎች ጉዞኣቸው እንዲቋረጥ ተደርጓል፡፡